የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርሰቲያን ምዕመናን ዘንድ በድምቀት ተከበረ

የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርሰቲያን ምዕመናን ዘንድ በድምቀት ተከበረ::

https://www.youtube.com/watch?v=I4V8VygwOuk&t=204s

በተለይም በዓሉ በአዲስ አበባ ጃንሜዳ ባህረ ጥምቀት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ  መርቆሬዎስ ፓትሪያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያና ፓትሪያሪክ አቡነ ማቲያስን ጨምሮ የተለያዩ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ምዕመናንና የውጭ ሀገር ጎብኝዎች በተገኙበት እንዲሁም በካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ዘንድም በድምቀት ተከብሮ ዋለ::

 

በጃንሜዳ በተከናወነ ስነ ስርዓት ላይ ለምዕመናኑ የ2011ዓ.ም የጥምቀት በዓል እንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ  “እኛ ኢትዮጵያውያን የተፈጥሮ ሀብቶቻችን ልንገለገልባቸው፤ አካባቢያዊ ክልሎችን ልንተዳደርባቸው እንጂ ልንጋጭባቸው አይገባም” ብለዋል።

“መለያየት፣ ጠማማነትና የተመሰቃቀለ ማህበራዊ ህይወት ሀገራችንን ብሎም ዓለምን እየተፈታታነ እንደሆነ ግልጽ ነው:: ሰው በመሆናችን ብቻ ተስማምተን፣ ተጋግዘን፣ ተዋደን፣ በአንድነትና በእኩልነት በመኖር ፋንታ በዘር፣ በጎሳ፣ በቋንቋና በመልክዓ ምድር እየተከፋፈልን እርስ በርሳችን እንዳንጎዳዳ መጠንቀቅ ይገባናል” ያሉት ፓትሪያርኩ “ሰው ከሰው የበለጠ ማንነት እንደሌለው ለማስረዳት እግዚአብሄር ሁላችንም ሰው ተብለን እንድንጠራ አድርጓል:: በዛሬው እለት በመላ ሀገሪቱ የተከበረው በዓል ድምቀትም የኢትዮጵያውያን መተባበር፣ መከባበርና መደጋገፍ  ያሳያል:: ይህም ተለያይቶና ተጣልቶ ድምቀትም ውበትም የሌለ መሆኑን ነው” ብለዋል::

” የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ታዋቂ ሰዎች በየአካባቢያቸው የሚሳሳቱን፥ በተለይም ወጣቶችን በመገሰፅና በመምከር ከልዩነት ይልቅ አንድነትን ማጠናከር እንዳለባቸው ያሳሰቡት አቡነ ማቲያስ  ወጣቶችም የመደማመጥ፣ የመታዘዝና ርህራሄ ባህላቸውን እንዲያሳድጉ መክረዋል።

የጥምቀት በዓል ከአዲስ አበባ ውጪ በርካታ ምዕመናንና ምዕመናት እንዲሁም፥ የውጭ ሀገር ጎብኚዎች በተገኙበት በጎንደር፣ ላሊበላ፣ አክሱም; አሰላ; አዳማ; ጅማ, ሐረር, ሐዋሳ, እና በሌሎች አካባቢዎች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነትተከታዮች፣ አድባራትና ገዳማት በድምቀት ተክብሯል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  “በዓለም ላይ ያሉ አሸባሪዎች የሚረሽኑት ሰዎችን ነው፤ ህወሓት ግን ሰዎችን ረሽኗል፤ እንስሳትን ረሽኗል፤ እጽዋትንም ረሽኗል” - ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

በሌላ በኩል ጥምቀት በአስመራ ከተማም በተመሳሳይ ሁኔታ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል:

Share