ዛሬ ለንባብ የበቃው በረራ ጋዜጣ ከኮ/ል ጌታቸው ብርሌ ጋር ቃለ መጠይቅ አድርጓል፡፡
https://youtu.be/epx_GOJUaUQ
ኮ/ል ጌታቸው በ2001 አ.ም. በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ከታሰሩት ውስጥ አንዱ ሲሆኑ ከዘጠኝ አመት እስር በኋላ የዶክተር አብይን ወደስልጣን መምጣት ተከትሎ የተፈቱ ናቸው፡፡ እስከታሰሩበት ጊዜ የ25ተኛው ክፍለ ጦር አዛዥ የነበሩት ኮ/ሉ የህወሃት አገዛዝ ሲፈፅመው የነበረውን በደል ለጋዜጣው አስረድተዋል፡፡ በተለይም በሰራዊቱ ውስጥ በሰባት ዙር የአማራ ተወላጆች እንዲባረሩ መደረጉን የተናገሩት ኮ/ል ጌታቸው የእሳቸውን መታሰር ተከትሎም ከእሳቸው ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የተጠረጠሩ በርካታ አመራሮች በ2002 መባረራቸውንም አስታውሰዋል፡፡ አሁን ከተፈቱ በኋላ ያለውን የሰራዊቱን እንቅስቃሴ እንዴት እንደታዘቡት ተጠይቀው ሲመልሱ ‹‹አሁን የህወሃት ሰራዊት አኩርፏል፡፡ ስራ በማበላሸት ላይ ናቸው፡፡ ጅግጅጋ ላይ የተከሰተው እነኳርተርም ያሉበት ነው፡፡ አሁንም አስኳሉ አልፈረሰም›› ብለዋል፡፡ ጨምረውም ‹‹አሁን ላለው የፀጥታ ችግር አለመተማመን አንደኛው ምክንያት ነው፡፡ ያለመተማመን ያመጣው እንጂ ከሰራዊቱ አቅም በላይ ሆኖ አይደለም፡፡ ከፖሊስ አቅም በላይ ሆኖም አይደለም›› በማለት አስረድተዋል፡፡ በብአዲን ላይ እምነት እንደሌላቸው የተናገሩት ኮ/ል ጌታቸው ሲገልፁ ‹‹ብአዲን ራሱን እያጠፋ እያጠፋ መጥቶ ባሪያ፣ ተላላኪ ወደ መሆን ደርሷል፡፡ ህወሀት ሲመራው የነበረው አሁ ደግሞ ሌላ መልክ የያዘ ይመስለኛል›› ሲሉ ለበረራ ጋዜጣ አስረድተዋል፡፡