January 16, 2019
2 mins read

በምዕራብ ኢትዮጵያ ህገ ወጥ ትጥቅ ታጥቀው የህዝቡን ሰላም ሲያውኩ የነበሩ 835 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የምእራብ ኢትዮጵያ ኮማንድ ፖስት አስታወቀ

93745

በምዕራብ ኢትዮጵያ ህገ ወጥ ትጥቅ ታጥቀው የህዝቡን ሰላም ሲያውኩ የነበሩ 835 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የምእራብ ኢትዮጵያ ኮማንድ ፖስት አስታወቀ።

https://www.youtube.com/watch?v=epx_GOJUaUQ
የምዕራብ ኢትዮጵያ ኮማንድ ፖስት ለኢቢሲ በላከው ሳምንታዊ መግለጫው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልና በምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢዎች የተሰጠውን ሰላም የማስፈን ተግባር አጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቋል፡፡
በዚህም መሰረት ህገ ወጥ ትጥቅ ታጥቀው የአካባቢውን ሰላም ሲያውኩ የነበሩ 835 ግለሰቦችን ኮማንድ ፖስቱ በሰራው ብርቱ ስራ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻ ለኢቢሲ በላከው መግለጫ አመላክቷል።
ኮማንድ ፖስቱ ሳምንታዊ የስራ አፈጻጸሙን ሲገመግም ከለያቸው መረጃዎች መካከል ከአካባቢው ፖሊስ፣ ከሚሊሻና ከዕቃ ግምጃ ቤት፣ከተለያዩ የመንግስት ቢሮዎችና የግለሰብ ሃብቶችን ፀረ ሰላም ሀይሉ ሲገለገልባቸው የነበሩ ንብረቶች የተመለሱና በምርኮ የገቡ አሃዛዊ መረጃዎች በመግለጫው ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሰረት 4 ብሬን ፣ 61 ክላሽ ፣ 105 ኋላ ቀር የጦር መሳሪያዎች ፣ 8 ሽጉጥ ፣ 1 ሺህ 5 የብሬን ጥይት ፣ 71 የክላሽ ጥይት ፣ 42 የሽጉጥ ጥይት ፣ 1 የሞርተር ጥይት ፣ 17 የአድማ ብተና መሳሪያ በቁጥጥር ስር አውሏል።
ለጠላት አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ 7 FSR መኪና ፣ 2 አይሱዙ ፣ 2 አምቡላንስ ፣ 5 ሚኒባስ መኪናዎችና 26 ሞተር ሳይክሎች እንዲሁም በ20 በርሜል 6 ሺህ ሊትር ቤንዚን ፣ 19 የሞባይል ቀፎ ፣ 5 ሺህ 910 የሞባይል ካርድ ፣ 2 የወገብ ትጥቅ ፣ 1 ኮምፒውተር ከነ ፕሪንተሩ በቁጥጥር ስር አውሏል።

1 Comment

Comments are closed.

93742
Previous Story

አዲስ አበባ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተጠለሉ ተፈናቃዮች ግቢውን እንዲለቁ ተጠየቁ

93748
Next Story

የቀድሞ ጠ/ሚ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop