(አድማስ ራድዮ) በአሜሪካን አገር ቀድመው ከመጡ ኢትዮጵያውያን አንዱ የሆኑትና፣ በበርካታ የማህበራዊና የፖሊቲካ ጉዳዮች ንቁ ተሳታፊ የነበሩት አቶ ሰለሞን በቀለ ማረፋቸው ተሰማ። ቀድሞ አትላንታ፣ ከዚያም በሜሪላንድ የኖሩት አቶ ሰለሞን በቀለ የራሳቸው የታክሲ ኩባንያ በመመስረት ከቀዳሚ ኢትዮጵያውያን አንዱ ነበሩ።
https://www.youtube.com/watch?v=ncwpPfdrV3E&t=991s
የየሎ ካብ ታክሲ ኩባንያ ባለቤት የነበሩትና በኋላም በሽያጭ ያዛውሩት አቶ ሰለሞን፣ በሜሪላንድ የደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ቤተክርስርቲያን ህንጻ ሲገነባም ትልቅ አስተዋጾ ማድረጋቸውም ይታወሳል።
በርካታ ታክሲዎችና የኡበር ተሽከርካሪዎችን በደምበኝነት ያቀፈ የኢንሹራንስ ድርጅትም ነበራቸው።
የጸሎት ፕሮግራም በመጪው ጃንዋሪ 12 ቅዳሜ ጠዋት 9 ሰዓት ላይ በዚያው በሜሪላንድ ደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ቤተክርስቲያን የሚካሄድ ሲሆን፣ በተመሳሳይ ቀን 1 ፒ ኤም ላይ በፌር ፋክስ ሚሞሪያል መቀበሪያ ቦታ ቀብራቸው እንደሚፈጸም አድማስ ራድዮ ከአትላንታ ዘግቧል::
አቶ ሰለሞን በቀለ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወይ ተባበሩ አልያም ተሰባበሩ በሚል በዋሽንግተን ዲሲ ትልቅ ስብሰባ በማዘጋጀት ቅንጅት እንዲፈጠር ምክንያት ከሆኑት ወገኖች መካከል ስማቸው ይጠቀሳል::