በጋምቤላ ውስጥ በሚገኘው የሱዳን ስደተኞች ካምፕ በተፈጠረ ግጭት ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ፡፡ የሞቱ ሰዎችም አሉ ተብሏል፡፡ የግጭቱ ምክንያት እስካሁን ባይታወቅም በቦታው በሰፈሩ የጋጃክና የጋጆይክ ጎሳዎች መካከል ከፍተኛ ፀብ እንደተፈጠረ የደቡብ ሱዳን ጋዜጣ የሆነው ኒያሚሊፒዲያ ዛሬ ዘግቧል፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=ncwpPfdrV3E&t=991s
አንድ ምንጭ ለጋዜጣው እንደተናገረው በተፈጠረው ግጭት የቆሰሉ በርካታ ከመሆናቸውም በላይ የሞቱም ያሉ ሲሆን ቁጥራቸው ግን አልታወቀም፡፡ ይህ ግጭት የተፈጠረው እሁድ እለት እንደነበርና የኢትዮጵያ ፖሊስ ጣልቃ ገብቶ ባያስቆመው የበለጠ ብዙ ሰው ይሞት እንደነበር ጋዜጣው አስረድቷል፡፡