December 28, 2018
2 mins read

በደብረማርቆስ በተደረገ አስቸኳይ ስብሰባ በመለስ ዜናዊ ስም ይጠራ የነበረ ፓርክ ስሙ እንዲቀየር ተወሰነ

93412

የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ዛሬ ጠዋት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ በመለስ ዜናዊ ይጠራ የነበረውን ፓርክ ስም ቀይሯል፡፡

በጉባኤው በተደጋጋሚ ከህዝብ የፓርኩን መጠሪያ አካባቢያችንን መሰረት ያደረገ ይሁን በሚል ሲጠየቅ እንደነበር ተነግሯል፡፡ በዚህ መሰረት የነዋሪውን ህዝብና በተለይ የወጣቱን ጥያቄ መመለስ ስለሚገባ ስያሜው እንዲለወጥ ጉባኤው ወስኗል፡፡ በመሆኑም ከዛሬ ጀምሮ ፓርኩ መንቆረር የወጣቶች መዝናኛ ማእከል ተብሎ እንዲጠራ በሙሉ ድምፅ ውሳኔ ማሳለፉን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ መንቆረር የደብረ ማርቆስ የቀድሞ መጠሪያ ነው፡፡ በተያያዘም ጉባኤው አዳዲስ ሹመቶችንም አፅድቋል፡፡

ከተጀመረው ለውጥ ጋር አብረው ይራመዳሉ በሚል አቶ ዳንኤል በላይን የከተማው ከንቲባ አድርጎ ሲመርጥ አቶ መርከብ የሻነውን የአስተዳደሩ አፈ ጉባኤ አድርጎ ሾሟል፡፡ በተጨማሪም ከ20 በላይ አዳዲስ አመራሮችን ሹመት ጉባኤው ካፀደቀ በኋላ አመራሮቹም የተሰጣቸዉን ሃላፊነት በቅንንት፤ በታታሪነትና እንዲያገለግሉ እና የህዝብን አንገብጋቢ ችግር በመፍታት በየዘርፉ ዉጤቶችን ለማስመዝገብ ጥረት እንደሚያደርጉ በቃለ መሃላቸዉ ገልፀዋል፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=KcPKUXGZAys&t=28s

93406
Previous Story

አባገዳዎች በሚቀጥለው ሳምንት ኦነግን ሊያነጋግሩ ነው

93418
Next Story

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የጦር መሳሪያ አያያዝና አጠቃቀም ህግ ሊወጣ ነው

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop