አጭጭር ዜናዎች

በአሶሳ ዩንቨርስቲ የተማሪዎች ዶርሚተሪ የተከሰተ ቃጠሎ በቁጥጥር ስር ዋለ። ከቀናት በፊት በዚሁ ዩንቨርስቲ በተፈጠረ ግጭት የሶስት ተማሪዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል። ግጭቱን ሲያስፈጽም ነበር ተብሎ የተጠረጠረ ግለሰብም በትናንትናው ዕለት በመካለከያው መያዙን ዘግበናል:: በአሶሳ ዩንቨርስቲ የተማሪዎች ዶርሚተሪ የተከሰተ ቃጠሎ መነሻ ምን እንደሆነ ለማወቅ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም:: በሌላ በኩል ግን የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ተከስቶ በነበረው ግጭት ተቋርጦ የነበረውን የመማር ማስተማር ሥራ ለመጀመር እየሠራ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ረሺድ መሀመድ መግለጻቸውን ሰምተናል::

በደብረ ማርቆስ ከተማ አንድ ግለሰብ ዛፍ ላይ ወጥቶ አልወርድም ካለ ከ24 ሰዓት በኋላ መውረዱ ታወቀ

በደብረ ማርቆስ ከተማ ቀበሌ 03፣ ሰፈር አንድ፣ ድብዛ አካባቢ ከህዳሴ ጤና ጣቢያ ዝቅ ብሎ በሚገኝ ዛፍ ላይ የወጣ አንድ ግለሰብ አልወርድም ብሎ ከቆየ ከ24 ሰዓት በኋላ በራሱ ፈቃድ መውረዱን የቀበሌው ስራ አስኪያጅ አቶ አወቀ አዛዥ ለቢቢሲ ተናገሩ፡፡

በትናንትናው ዕለት የአካባቢው ሰዎች ስንት ሰዓት ላይ ዛፉ ላይ እንደወጣ ባያዩትም ከ4 ሰአት ጀምሮ ግን ዛፉ ላይ ወጥቶ መመልከታቸውን እንደነገሯቸው ለቢቢሲ ጨምረው አስረድተዋል።

ዛሬ ምሳ ሰአት አካባቢ ያለምንም ረዳት ከዛፉ ላይ እንደወረደ የሚናገሩት ስራ አስኪያጁ ለምን ዛፉ ላይ እንደወጣ ለመናገር ፈቃደኛ አልሆነም ብለዋል።

ከዛፉ ላይ እንደወረደ የአካባቢው ሰዎች የሚጠጣው ውሃና ያላቸውን ገንዘብ አዋጥተው እንደሰጡት ጨምረው ነግረውናል።

ግለሰቡ በአሁኑ ሰአት በከተማው ፖሊስ እጅ እንደሚገኝም ጨምረው አስረድተዋል።

የቀበሌው ስራ አስኪያጅ እንደሚሉት ግለሰቡ የወጣበት ዛፍ የሚገኝበት አካባቢ ገደላማ ሲሆን በተለምዶ የግምጭ ወንዝ የሚባለው የሚገኝበት ነው። ይህም ግለሰቡን ለማውረድ የሚደረገውን ጥረት ፍሬ አልባ አድርጎት ቆይቶ ነበር ብለውናል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የወያኔ ራዕይ ቅዠት ሆኖ የሚቀረው ሥርአቱን ተረክቦ የሚያስቀጥል ትውልድ ስለማያገኝ ነው | ከይገርማል

ዛፍ ላይ ወጥቶ አልወርድም ያለው ግለሰብ ዕድሜው ከ35 እስከ 45 የሚገመት ሲሆን የቆሸሸ ልብስ መልበሱን ክራንችም ከዛፉ ስር ወድቆ መገኘቱን ጨምረው ነግረውናል። እርሳቸውም አንድ እግሩና እጁ ላይ ጉዳት እንዳለበት መመልከታቸውን እና የአካል ጉዳተኛ እንደሆነ ተናግረዋል።

የደብረማርቆስ ከተማ ኮሚዩኑኬሽን የዜናና ሕትመት ባለሙያ ወ/ሮ ሐረጓ አበበ የወጣበት ዛፍ ትልቅ መሆኑን ተናግረው ለማውረድ በተሞከረ ቁጥር እርሱ ወደ ላይ ስለሚወጣ ተቸግረው ነበር።

የከተማው ኮሙዩኑኬሽን ባልደረቦች ዛሬ ማለዳ ሄደው እንዳዩት የሚናገሩት ወ/ሮ ሐረጓ ለማነጋገር ቢሞከርም ምላሽ እንደማይሰጥ ያስረዳሉ።

የወጣበት ባህር ዛፍ ትልቅ ቢሆንም እርሱ ግን ጫፍ ላይ የሚገኝ ቅርንጫፍ ላይ መውጣቱን ማየታቸውን ጨምረው አስረድተዋል።

ፖሊስ በአካባቢው ተገኝቶ እንደነበር የሚናገሩት የኮሙዩኑኬሽን ባለሙያ እንዲወርድ ለማድረግ የተለያዩ ሙከራቸውን ማድረጋቸውንም ተናግረዋል።

ግለሰቡ ደብረማርቆስ ቦሌ ኮንዶሚኒየም አካባቢ በጫማ ማሳመር ስራ ላይ ተሰማርቶ እንደነበር መረጃ ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

ኤርሚያስ ጌታቸው የተባለ ወጣት በህንድ እና ማሌዢያን በመሳሰሉ ሃገራት እየተተገበረ ያለና የትራፊክ አደጋን በከፍተኛ መጠን ለመቀነስ የሚጠቅም የ3D ዜብራ ቴክኖሎጂ የበቾ ወረዳ ዋና ከተማ በሆነችው ቱሉቦሎ ከተማ መስራቱን  በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ አንብበናል::

ኡርጂ ጋዜጣ ከ20 አመት በኋላ ወደህትመት ተመለሰች፡፡ ታህሳስ 1986 ተመስርታ በግሉ ሚዲያ ዘርፍ ተሰማርታ የነበረችውና በተለይም በኦሮሞ ጉዳዮች ላይ ልዩ ትኩረት የምትሰጠው ኡርጂ ጋዜጣ በ1990 ህትመቷን አቋርጣ ነበር፡፡ በነበረው አፋኝ ስርአት የተነሳ ህትመቷን ለማቋረጥ እንደተገደደች የገለፀችው ኡርጂ በዚሁ የተነሳ የጋዜጣዋ አዘጋጆች አገር ጥለው እንደተሰደዱም አውስታለች፡፡ ህዳር 13 በድጋሚ ለንባብ የበቃችው ኡርጂ ስምንት ገፆች ያሏት ሲሆን ከ20 አመት በኋላ በድጋሚ ለህትመት ስትበቃም እንደድሮው በኦሮሞ ጉዳዮች ላይ ያተኮረች ሆና መጥታለች፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ከአገር እንዳይወጡ ታገዱ

የህዘብ ተወካዮች ምክር ቤት በነገ መደበኛ ስብሰባው በያዝነው አመት ለሚካሄደው የህዝብና ቤት ቆጠራ፤ የኮሚሽን አባላትን ለመመደብ የቀረበ የውሳኔ ሀሳብን መርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

የሕዝብና የቤቶች ቆጠራ ከህዳር 2010 ዓ.ም ወደ የካቲት 2010 ዓ.ም እንዲራዘም ከተደረገ በኅላ፣ በሀገሪቱ በነበረው አለመረጋጋትና የዜጎች መፈናቀል ምክንያት እንደገና በአንድ አመት እንዲራዘም መወሰኑ ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በነገው ዕለት ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ለሚያደርጉት ውይይት የፓርቲ አመራሮች በድጋሚ እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀረበ:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሃገር ውስጥ ካሉትም ከውጭ ሃገር በቅርቡ ከገቡት የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ውይይት የሚያደርጉት በጽህፈት ቤታቸው ሲሆን ጽህፈት ቤታቸው ተፎካካሪ ፓርቲዎች በድጋሚ ለዚህ ስብሰባ እንዲመዘገቡ ጥሪውን በማህበራዊ ሚድያዎች አቅርቧል::

በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በቀጣይ ቀናት ሰላም የራቃትን የድሬዳዋ ከተማን ይጎበኛሉ። በቆይታቸው ከነዋሪዎች ጋር የሚወያዩ ሲሆን የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክን እንደሚመርቁ ይጠበቃል።

በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ከሱዳን ወደ ኢትዮዽያ በመግባት ላይ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በተደረገ ፍተሻ 5 ብሬን ከ3500 ጥይቶች ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉን የአካባቢው ፖሊስ አስታወቀ።

ዋልታ ቴሌቪዥን በትግራይ ክልል ከተሞች የተካሄዱ ሰልፎችን በትክክል ስላልዘገበ የትግራይን ህዝብ ይቅርታ እንዲጠይቅ የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አሳሰበ፡፡

የትግራይ ህዝብ ንብረት እንደሆነ የሚነገረው EFFORT ኩባንያ በዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ከ20 በመቶ በላይ የባለቤትነት ድርሻ እንዳለው ይታወቃል።

የሰለሜው ጌታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ሴሌሜ ሴሌሜ በሚለው ዘፈን ከፍተኛ ዝናን የተጎናፀፈው አርቲስት አቡሎ ጥሞሮ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  Hiber Radio: ፕ/ት ኦባማ ኢህአዴግና አማጽያኑን እንዲሸመግሉ መጠየቁ፣ አምንስቲ እንግሊዝ ለኢትዮጵያው አገዛዝ አፈና መጠንከርን ተጠቃሽ አደረገ፣ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ጦርነት መክፈት የፈጠረው መነቃቃት፣ እስራኤላዊው ትውልደ ኢትዮጵያዊው በሐማስ እጅ መውደቅ የፈጠረው ተቃውሞ፣ የጋዜጠኛ ርዮት ዓለሙ እና ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል ቃለ መጠይቅ፣ የመን ሰንዓ ኤምባሲ ፊት ለፊት የወደቁ ኢትዮጵያውያን ያሉበት ስቃይ እና ሎሎችም

ሙዚቀኛው አቡሎ ጥሞሮ በሀዲይኛ ቋንቋ ዜማዎችን ከአርባ ዓመታት በላይ የተጫወተ ሲሆን፤ ከእነዚህም በከፍተኛ ዘንድ ተወዳጅነትን ያገኘው “ሴሌሜ፣ሴሌሜ ቦያ ሴሌሜ” ተወዳጅና በህዝብ ዘንድ እውቅናን ከፍ ያደረገለት ሙዚቃው ነው።

https://www.youtube.com/watch?v=Qd-gjrRllUA&t=385s

Share