በዛሬው እለት የተሾሙት ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የመጀመሪያ ስራ ይፋ ሆነ፡፡

ትላንት ህዳር 12 ቀን 2011 ከደቡብ ህዝቦች ምክር ቤት ጽ/ቤት የወጣው ደብዳቤ ለአዲሲቷ የምርጫ ኮሚሽን ሰብሳቢ የመጀመሪያ ስራ እንደሚሆን ለመረዳት ችለናል፡፡

ደብዳቤው በርዕሱ ‹‹ህዝበ ውሳኔ እንዲከናወን ስለመጠየቅ›› ይልና የተላከው ለምርጫ ቦርድ እንደሆነ ያሳያል፡፡ ደብዳቤው ሲዘረዝር ‹‹በክልላችን ካሉት 56 ብሄር ብሄረሰቦች አንዱ የሆው የሲዳማ ብሄር ራሱን ችሎ ክልል ሆኖ የመደራጀት ጥያቄ በቁጥር ም/ቤ/02/38/0034 በቀን 12/11/2010 አ.ም. በተፃፈ ደብዳቤ የዞኑ ምክር ቤት አባላት በኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 47/2 እና 3ሀ እንዲሁም በክልሉ ህገ መንግስት አንቀፅ 39/5 እና 9ሀ መሰረት በሙሉ ድምፅ የወሰኑትን ውሳኔ በቀን 13/11/2010 አ.ም. ለምክር ቤታችን አባሪ አድርገው በማቅረብ ጠይቀዋል›› ይላል፡፡ ደብዳቤው ጨምሮም ይህ ጥያቄ ጥቅምት 23 ቀን 2011 በተደረገው የምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤ ተፈፃሚ እንዲሆን አቅጣጫ መቀመጡን አውስቶ ምርጫ ቦርድ በአዋጅ ቁጥር 532/1999 አንቀፅ 32/2 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ህዝበ ውሳኔ እንዲያከናውን ጠይቋል፡፡ በክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሄለን ደበበ ወ/ጊዮርጊስ ፊርማ ትላንት የወጣው ደብዳቤ በግልባጭ ለጠ/ሚ/ር ዶክተር አብይ አህመድ፣ ለፓርላማው አፈ ጉባኤና ምክትል አፈ ጉባኤ፣ ለክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት፣ እንዲሁም ለሲዳማ ዞን ምክር ቤት እንዲደርስ መደረጉን ለማወቅ ችለናል፡፡ በመሆኑም የወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ቢሮ የመጀመሪያ ስራው ይህንን የሲዳማ ክልልነት ጥያቄ በህዝበ ውሳኔ ማስፈፀም ይሆናል፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=W20KYng_SXM

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢሳት Ethiopia - Esat Diro Ena Zendiro Feb 11,2023

1 Comment

  1. ታሪካዊና ትልቅ አሻራ ነው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ወ/ሮ ብርቱካንን ለምርጫ ቦርድ ሰብሳቢነት ማቅረብ፡፡ ትክክለኛ አካሄድ፡፡ Congra Birtukan!! እንደው ለመሆኑ የምክርቤት አባል መሆን Symbol ሆኖ መቀጠል እስከመቼ? እውነተኛ የፓርላማ አባላት ለማየት ህዝቡ ይመኛል፡፡ ዕጩዋን መቀበል ግድ ቢሆንም ከዚህ በፊት በነበረ አስተዳደር መቼ ጊዜ ነው ከማንኛውም የፓርቲ አባል ገለልተኛ የሆነ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ተሰይሞ የሚታወቀውና አሁን ብርቱካንን የመሰለ ለአገር የሚጠቅም እጩ ስትቀርብ እንደዘህ አይነት ጥያቄ የሚቀርበው፡፡ ለመሆኑ የፓርላማ አበል ተብዮዎች እንደው እስከመቼ ነው አለቅላቂ እንደሆኑ መቀጠል፡፡ ለማንኛውም ወደፊት ይህ ነገር ይቀራል ተብሎ ይገመታል፡፡

    Good news for Ethiopian people. W/ro Birtukan deserves for the post well though many challenges may face her in future. But for sure she can perform her job in a very professional way and do her best on putting a platform for democratic process. So she has to be smart enough on nominating her board members because her objectives can only attained when board members of her organization shall be selected seriously and assure that they can be free from an affiliate of any parties.

    Even it is too late to bring all opposition parties for dialogue, you should be quick for registering those legal formed parties and work to cancel those parties who can’t do in a legally way. You may also develop a legal framework for all opposition parties (including EPDRF) to act in a very peaceful way and they should be abide by rules & regulation.

    The present regime shall also support her in every way and safeguard her from any violent activities.

    Long live to Ethiopia!!

Comments are closed.

Share