የእነአብዲ ኢሌ የዛሬ የፍርድ ቤት ቀረቡ | ፖሊስ 50 አስከሬን አውጥቶ እንዳስመረመረ ገለጸ

የቀድሞው የኢትዮ ሱማሊ ክልል ፕሬዚደንት አብዲ ኢሌ ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ጉዳያቸውም ለህዳር 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ተቀጥሯል፡፡ በዛሬው ችሎት ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ እስካሁን የደረሰበትን የምርመራ ውጤት አስረድቷል፡:

፡ በዚህም መሰረት በተጠርጣሪዎቹ አማካኝነት በጅግጅጋና አካባቢው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ በደረሰው ጉዳት 300 ሚሊየን ብር የሚገመት የንብረት ውድመት እንዳጋጠመ ተናግሯል፡፡

እንዲሁም ከሃምሌ 26 እስከ ሃምሌ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. በዘርና በሃይማኖት እየተለዩ ሰዎች መገደላቸውንና በጅምላ መቀበራቸውን አስረድቶ ይህን በተመለከተም በፎቶግራፍ የተደገፈ ማስረጃ ለፍርድ ቤቱ አሳይቷል፡፡ በአጠቃላይ ከ2004 ጀምሮ የክልሉን አስተዳደር በተቃወሙ 200 ግለሰቦች ላይ ግድያ እንደተፈፀመ የገለፀው ፖሊስ ለዚህም ተጠርጣሪዎቹን ተጠያቂ አድርጓል፡፡ ከ2004-2010ዓም ድረስ በሶማሌ ክልል የፍትህ ጥያቄ ያነሱ 200 ሰዎች ፀረ ሰላም ሀይሎች እየተባሉ በግፍ በአደባባይ በጠራራ ፀሀይ እየተረሸኑ በጅምላ ተቀብረዋል። እስካሁን 50 አስክሬን አስወጥተን እያስመረመርን ነው ሲልም ፖሊስ ለችሎቱ አስረድቷል::

ከአብዲ ኢሌ ጋር ሶስት ግለሰቦች በክሱ ላይ የተካተቱ ሲሆን የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች ደንበኞቻቸው እንዲለቀቁ ቢጠይቁም ፍርድ ቤቱ ሳይቀበላቸው ቀርቷል፡፡ ፖሊስ ተጨማሪ የተገደሉ ሰዎችን ቤተሰቦች እስካፈላልግ ጊዜ ይሰጠኝ በማለቱ መዝገቡ ለህዳር 27 ተቀጥሯል፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=W20KYng_SXM

ተጨማሪ ያንብቡ:  “ኢትዮጵያ የሚለውን የነጻነት ስም የማስጠበቅ የታሪክ አደራ አለብን!" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
Share