የቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት የስራ ባልደረባ አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ አዲስ ክስ ተጨመረ | ፖሊስ የሜ/ጀ ክንፈ ወንድም አቶ ኢሳያስ ዳኘው በባንክ ያላቸውን ገንዘብና ንብረታቸውን ማስረጃ አቅርቦ ዋስትና ራሳቸው ያቁሙ ሲል ጠየቀ

የቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት የስራ ባልደረባ አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ዛሬ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት ዛሬ ቀረቡ:: ፖሊስም ከሰኔ 16ቱ የቦምብ ፍንዳታ በተጨማሪነት አዲስ ክስ ይዞ በመምጣት በሰብዓዊ መብት ጥሰትና በሙስና ወንጀል ጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።

አቶ ተስፋዬ የደህንነት መምሪያ ሀላፊ ሆነው ሲሰሩ ሰዎችን በሽብር ተጠርጥራችኋል በሚል በስውር እስር ቤት በማሰርና በማሰቃየት፥ እርቃናቸውን በካቴና አስረው ቆሻሻ ገንዳ ውስጥ በማቆየት፣ ግለሰቦችን ባልተገባ መልኩ ለሽብር መልምለው ወደ ኤርትራ በመላክ እንደጠረጠራቸው ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አስረድቶ ከዚህ ባለፈም በሽብር ከተጠረጠሩ ሰዎች ላይ ገንዘብ በመቀበል እና በሀዋላ ከተጠርጣሪዎች ላይ ህገ ወጥ ገንዘብ በመቀበል በሰብዓዊ መብት ጥሰትና በሙስና ወንጀል ጠርጥሬያቸዋለሁም ያለው ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅም 14 ተጨማሪ የምርመራ ቀን ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

አቶ ተስፋዬ በሰጡት ምላሽ እርሳቸው የተጠረጠሩበት ጉዳይ በግልጽና በተናጠል እንዳልቀረበ በመግለጽ፥ እርሳቸውን ለመያዝ በቂና ዝርዝር ጉዳይ አለመኖሩን አስረድተዋል። በተጨማሪም ሀብት የመፍጠር ህገ መንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው ሃብት ማፍራታቸውንና ለአራት ወራት ፍርድ ቤት እየተመላለሱ መሆኑን በመጥቀስ፥ ሃብት ከማፍራት ጋር ተያይዞ ሀምሌ 5 ቀን 2010 ዓ.ም ቤታቸው መበርበሩንና ምርመራው በወቅቱ ማለቅ ነበረበት ብለዋል። አሁን ላይ መርማሪ ፖሊስ የጠየቀው ተጨማሪ ጊዜም ሊሰጥ አይገባም በማለት ተቃውመው ነበር። ችሎቱ ግን አቶ ተስፋዬ በተጨማሪነት የተጠረጠሩበት ወንጀል በተብራራ መልኩ እንዲቀርብ አዞ ፖሊስ የጠየቀውን 14 ቀን በመፍቀድ ለህዳር 24 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ይህ በ እንዲህ እንዳለ ባለፈው ሳምንት በሌብነት ተጠርጥረው የታሰሩት የሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው ወንድም አቶ ኢሳያስ ዳኘው “ገቢዬ አነስተኛ ነው; ጠበቃ መንግስት ያቁምልኝ” ያሉት ሀሰት መሆኑን ዛሬ ፖሊስ በማስረጃ ለችሎት አቅርቧል።
– G+1(2million የሚያወጣ) 6 ክፍል ያለው ቪላ
– ባለ 3 ክፍል የጋራ መኖሪያ
– ቶዮታ ኮሮላ ሎደር፣
– አምበሳ ባንክ አክሲዮን በተጨማሪም በዳሽን እና አዋሽ ባንክ ገንዘብ ስላለቸው በግላቸው ጠበቃ ያቁሙ ። ፍርድ ቤቱን በማሳሳታቸው አስተማሪ ቅጣት ይሰጥ ሲልም ፖሊስ ችሎቱን መጠየቁ ተሰምቷል::

ተጨማሪ ያንብቡ:  ተወዳጁ አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ የቀብር ሥነ ስርዓት ነገ መስከረም 19 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚፈጸም የቀብር ሥነ ስርዓቱን ለማስፈፀም የተቋቋመው ኮሚቴ አስታወቀ

“25 የአንበሳ ባንክ አክሲዮን፣ በንግድ ባንክ 40ሺ ብር፣ አምበሳ ባንክ 8000 ብር ዳሽን 11ሺ ብር ወዘተ በማለት ዳኛው በዝርዝር በፖሊስ የቀረበውን ማስረጃውን ካነበቡ በኋላ ችሎቱ በቂ ሀብት ያላቸው መሆኑን ስላረጋገጠ በመንግስት የተመደቡትን ጠበቆች አንስቷል በማለት ወስነዋል:: በዚህም መሰረት አቶ ኢሳያስ የራሳቸውን ጠበቃ አቁመው ይከራከራሉ ማለት ነው::
https://www.youtube.com/watch?v=pXfWMmUXIks

Share