ጀነራሎች እና ስመጥር ባለሃብቶች እየተዝናኑ የሚደራደሩበት ጎልፍ ክለብ ጭር ማለቱ ተሰማ

በመከላከታ ሠራዊት ፋውንዴሽን ሥር የተቋቋመውና ጀነራሎች እና ነጋዴዎች የሙስና ድርድር ያደረጉበታል የሚባለው ጎልፍ ክለብ መዝናኛ ከወትሮው በተለየ ጭር ብሎ መሰንበቱ ተገለጸ:: ትናንት በአዲስ አበባ ታትሞ በወጣው ፍትህ ጋዜጣ ላይ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እንደገለጸው በተለይ ሮብ አርብ ቅዳሜ ክራማው የሚደምቀው ይህ ክለብ የለጋስ ከበርቴዎች እና የጀነራሎች በተለይም ጀነራል ሳሞራ የኑስ; ሜጀነራል ብርሃነ ነጋሽ; ሜጀር ጀነራል መሃሪ ዘውዴ መዝናኛ እንደሆነ ተናግሯል::

“የጀነራል መኮንኖች መዝናኛ ጎልፍ ክለብ የተጋነነ ካፒታል ባይኖረውም ከባባድ የንግድ ስምምነቶች ሲካሄዱበት መቆየቱ ይነገርለታል:: ስመ ጥር ባለሃበቶች ከውጭ ሃገር የሚያስገቧቸውን እቃዎች በፋውንዴሽኑ በኩል ያለቀረጥ ለማሳለፍ ይደራደሩበታል:: ጀነራሎቹ ለድርጅታቸውም ሆነ ለግል ጉዳያቸው የሚሸምቱትን በክለቡ ስብ ሳያስቀርጡ ለማስገባታቸው ጥቆማዎች አሉ” ያለው ተመስገን በአሁኑ ወቅት የግቢው መንፈስ ተቀይሯል ይላል::

Watch
https://www.youtube.com/watch?v=-q8i19IEiLA&t=491s

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሰላማዊ ትግላችንን ከፍ አድርገን እንቀጥላለን!!!
Share