November 14, 2018
3 mins read

ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው የሰው እጅ እንዳላይ መንግስት ጠበቃ ያቁምልኝ አሉ | ወንድማቸውና የቀድሞዋ የETV ጋዜጠኛ ታሰሩ

የቀድሞው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ወንድማቸው ኢሳያስ ዳኘውን እና ለሜቴክ ዘጋቢ ፊልም የሰራችው ጋዜጠኛ ፍጹም የሺጥላን ጨምሮ 8 ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ። ሁለቱም 10ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል::

የሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ወንድም አቶ ኢሳያስ ዳኘው የኢትዮቴሌኮም ከፍተኛ የስራ ኃላፊ ሆነው ሳሉ የግዢ ስርአቱን በጣሰ መልኩ ሜቴክ ጨረታ እንዲያሸንፍ በማድረግ ወንጀል ተጠርጥረው እንደታሰሩ በፍርድ ቤቱ ተገልጿል::
ተጠርጣሪው የማይገባ የጥቅም ትስስር በመፍጠር የህዝብና የመንግስት ሃብት አንዲባክን አድርገዋል ሲል ፖሊስ ገልጿል::
ጋዜጠኛ ፍጹም የሺጥላ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን 120 የተባለ ፕሮግራምን ጨምሮ በተለያዩ መዝናኛ ፕሮግራሞች ላይ አስተዋዋቂ ሆና ስትሰራ መቆየቷ ይታወሳል::

ከሁለት አመት በፊት ከሜቴክ በተሰጣት ከፍተኛ ብር “የብሩህ ኢትዮጵያ ልጆች» የሚል በተለይ የሜቴክን ዳይሬክተር ክንፈ ዳኘውንና ድርጅቱን እንዲሁም የሜቴክን ሥራ የሚያወድስ ዘጋቢ ፊልም ሠርታ ነበር:: ከሜቴክ አመራሮች ጋርም የቀረበ ግንኙነት እንደነበራት ይነገራል:: በቁጥጥር ሥር እያለችም በኋላ መኖሪያ ቤቷ ሲፈተሽ እንደነበር ተሰምቷል::

ዛሬ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት ጉዳያቸው እየተያ ያሉት ሁለቱ ወንድማማቾችና ጋዜጠኛ ፍጹም የሺጥላ አቅም ስለሌለን መንግስት ጠበቃ ያቁምልን ሲሉ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል። በተለይም ጀነራል ክንፈ ዳኘው ” ፖሊስ በጠየቀው የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ላይ ሀሳብ እንዲሠጡ ሲጠየቁ ““ወርሃዊ ገቢዬ በጡረታ የማገኘው 4 ሺህ ብር ብቻ በመሆኑ፥ አቅም ስለሌለኝና የዘመድ እጅ እንዳላይ መንግስት ተከላካይ ጠበቃ እንዲያቆምልኝ” በማለታቸው ተሰምቷል::

የጀነራል ክንፈዳኘውና የአምስት ቤተስቦቻቸው በተለያዩ ባምኮች ያሏቸው አካውንቶች መታገዱን ዘ-ሐበሻ ትንናት ዘገቦ ነበር::

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዶ/ር አብይ አህመድ መንግስት የሰብ አዊ መብት ጥሰት በፈጸሙና በሙሰኞች ላይ እየወሰደ ያለው የሚደነቅ ሆኖ ሳለ መደረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች የሕብር ራድዮ ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ ለዘ-ሐበሻ አጭር አስተያየት ሰጥቷል::
https://www.youtube.com/watch?v=DWNBg4WLnI0&t=540s

Go toTop