November 14, 2018
4 mins read

ኦነግ እና መንግስት ተስማሙ

92534

አቶ ለማ መገርሳና አቶ ዳውዲ ኢብሳ በዛሬው እለት እንደተስማሙ አስታውቀዋል፡፡ የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ በሰጡት መግለጫ ድርጅታቸው ከኦሮሚያ ክልልና ከፌዴራል መንግስት ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ እንደደረሰ ተናግረዋል፡፡

ኦነግ ከመንግስት ጋር ስምምነት ላይ የደረሰው በቀጣይ ሊታዩ የሚገባቸው ጉዳዮች ላይ በመነጋገር ለአገር እድገት በጋራ ለመስራት እንደሆነ ያስረዱት አቶ ዳውድ የኦነግ ሰራዊትም በሰላማዊ መንገድ ከመንግስት ጋር በአንድነት እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ በበኩላቸው ‹‹ለሃገር ሰላም፣ ልማትና ዕድገት ከዚህ በኋላ በመደማመጥ በጋራ እንሰራለን›› ያሉ ሲሆን ‹‹ቄሮ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሆኑ አክቲቪስቶች የተገኘውን የፖለቲካ ድል በመደማመጥና በመደጋገፍ ከዳር ሊያደርሱት ይገባል›› በማለትም አስረድተዋል፡፡

አቶ ለማ ጨምረውም በሃገርና ህዝብ ላይ ጉዳት ሲያደርሱ የነበሩ ወገኖች ለህግ እንዲቀርቡና የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ህዝቡ ለመንግስት ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባም ገልፀዋል።

አቶ ዳኡድ አክለውም “ኦነግ ከኦሮሚያ ክልልና ከፌደራሉ መንግስት ጋር አብሮ ለመስራትና በቀጣይ ሊታዩ በሚገቡ ጉዳዮች ላይ በመነጋገር ለሃገር እድገት አብረው ለመስራት ተሰማምቷል:: ኦነግና የኦነግ ሰራዊትም በሰላማዊ መንገድ በመንቀሳቀስ ከመንግስት ጋር አንድ በመሆን ይሰራልም” ብለዋል:::

በሌላ በኩል የዶ/ር አብይ አህመድ መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር እየወሰደ ያለውን እርምጃ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አደነቀ። የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ዛሬ ባወጣው መግለጫው፥ leባ መቼም ቢሆን ከህዝብ አይን እና ጆሮ ማምለጥ አይችለም:: የኢፌዴሪ መንግስት በሰው ልጅ ላይ አሰቃቂ ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ እና በሀገሪቱ ላይ ከባድ የሙስና የወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል የህግ የበላይነት አንዲከበር እየሰራ ያለው ስራ የሚደነቅ ነው ካለ በኋላ የዶ/ር አብይ የፌዴራል መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር እየወሰደ ያለውን እርምጃ በከፍተኛ ሁኔታ ያደንቃል ያለው መግለጫው፤ የሚጠበቅበትን ድጋፍ ለመወጣት ዝግጁ መሆኑንም አስታውቋል።
https://www.youtube.com/watch?v=DWNBg4WLnI0&t=540s

2 Comments

  1. በጣም ጥሩ ዜና ነው ቃሉን ከጠበቀ፡፡ ሌላ አማራጭ የለውም አብሮ ከመስራት በስተቀር፡፡ ኢብሳ አገር ውስጥ ገና ሲገባ ከኤርፓርት እየተቅለሰለሰ እየፎገረን ደህና አድርጎ ነበር የሰጠን፡፡
    ስምምነቱን ያዝልቅልን ብለናል!

  2. ኦነግ ኦነግ ኦነግ
    የህዝባችን ፈለግ
    የተሳሳ ኣንድ ለማድረግ
    ችግር ፈጣሪን ለመታደግ
    ካልሆነም ለማስደግደግ
    የለም ማፈግፈግ

Comments are closed.

92531
Previous Story

ማናቸውም ብሔር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እንዳይፈፀም የትግራይ ህዝብ በከፍተኛ ኃላፊነት እንዲታገለው የትግራይ ክልል መንግስት ጥሪ አቀረበ

92537
Next Story

ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው የሰው እጅ እንዳላይ መንግስት ጠበቃ ያቁምልኝ አሉ | ወንድማቸውና የቀድሞዋ የETV ጋዜጠኛ ታሰሩ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop