ፕሮፌሰር መረራ ‹‹የጠመንጃ ፖለቲካ ማብቃት አለበት›› አሉ

ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የጠመንጃ ፖለቲካ መብቃት እንዳለበት አሳሰቡ፡፡ ፕሮፌሰሩ ሲናገሩ ‹‹ይህ የጠመንጃ ፖለቲካ መብቃት አለበት፡፡ ደርግ 17 አመት በጠመንጃ ገዛ፣ የአንድ ትውልድ ልጆችን ገድሎ መጨረሻ ራሱም ተዋረደ፡፡ ኢህአዲግም በ27 አመታት ያንኑ ሞከረ፡፡ ህዝብን ዘላለም በጠመንጃ መግዛት አትችልም፡፡ ህዝብን የምትመራበት የተሸለ ልማትንና ብልፅግናን የምታመጣበት የተሻለ ህዝባዊ አስተዳደር የምታሰፍንበት መንገዶች አሉ፡፡ ውድድሩ ካለ እዚህ ላይ መወዳደር ነው፡፤ ይህንን ሁላችንም ጠንቅቀን ልናውቅ ይገባል›› ብለዋል፡፡
ፕ/ር መረራ ይህን የተናገሩት ትላንት በአዲስ አበባ ለንባብ የበቃው ‹አብይ ጉዳይ› መፅሄት ላይ ነበር፡፡ በዚሁ መፅሄት በኢትዮጵያ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ ፖለቲካችንን ማስተካከል እንደሆነ ያስረዱት ፕሮፌሰሩ፣ ፖለቲካው ከተስተካከለ ሀቀኛ የፍትህ ስርአት በኢትዮጵያ ምድር እንደሚፈጠር ተስፋቸውን ጠቁመዋል፡፡ አሁን በኢህአዲግ ውስጥ የተፈጠረውን ለውጥ በተመለከተ ሲያብራሩም ‹‹መሰረታዊ ለውጥን በሚያመጣ ደረጃ አልተከለሰም፡፡ ነገር ግን ተነካክቷል፡፡ ብዙ ቦታ የፍትህ ስርአቱም ሆነ ደህንነቱም ሚዲያውም ብዙ ተነክተዋል፡፡ ግን እነዚህ ሁሉ ተጠቃለው መሰረታዊ ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ ብሎ መደምደም ይቸግራል›› ብለዋል፡፡
አባባላቸውን በምሳሌ አጣቅሰው በመንግስትና በተቃዋሚዎች መሀከል ብሄራዊ ስምምነት እንደሌለ፣ ብሄራዊ መግባባት እንዳልተፈጠረ፣ ሁሉም በራሱ መንገድ እየሰራ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ ጨምረውም ‹‹መሰረታዊ በሆኑ የአገሪቱ ጉዳዮችላ ይ በተፎካካሪ እና በመንግስት መሀከል ምንም ስምምነት የለም›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ስለዚህም በጣም ወሳኝ የሆኑት ጥያቄዎች ባለመመለሳቸው ኢትዮጵያን ወደተፈለገው አቅጣጫ የሚወስዱ ጉዳዮች ገና እንደሆኑ ጠቅሰዋል፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=f9ZDJjIZNkI

ተጨማሪ ያንብቡ:  "ከንቲባዋ የአዲስ አበባ ባህል ማዕከልን ዳግም እስካልከፈቱ ድረስ ከኪነጥበቡ ዓለም ተለያይቻለሁ" አርቲስት ደበበ እሸቱ

3 Comments

 1. It is answered 1.Raya and Wolkait is in Tigray’s territory.
  2. Addis Ababa is it’s own territory belonging to all residents of Addis Ababa (any human beings including those with foreign citizenship) .
  3.Oromia will remain part of Ethiopia Oromos are allowed to reside anywhere in Ethiopia.
  4. Badme belongs to Eritrea.

  Right now many of those that promote the rifle politics got one foot in the diaspora and the other foot in Ethiopia. Those that got both foot in Ethiopia don’t promote violence.
  From nowon we Ethiopians will resort to rifle politics only to defend ourselves if we got invaded by neighboring countries or to defend our country from foreign invader.

 2. የማከብራችሁ አባቶቼ ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም እና መራራ ጉዲና የምሬን ነው እንደሕዝብ በዜግነቴ ልምከራችሁ፤
  ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድን ለሁለት ከምትቦጭቁት ራሳችሁ እስኪ ቁጭ በሉና፣ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም እና ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና አንድ ሃሳብ ይዛችሁ አማክሩት።
  በአንድ በኩል ፕሮፌሰር መስፍን ስለሠይፍ አስፈላጊነት በአግድም ሲተቹ፤በሌላ በኩል ደግሞ ፕሮፌሰር መራራ የጠመንጃ ፖለቲካን አላስፈላጊነት ይሰብካሉ።
  እኔን ብትጠይቁኝ ግን እንደተራ ዜጋ የምሰጠው ምክር ሁለታችሁም ተሳስታችኋል ነው የምለው፤ለምን ብትሉኝ ዶክተር ዐቢይ አህመድ አቶ አይደለም፤አቶ መለስ ዜናዊ ግን፣አቶ ነው።
  ሌላው ደግሞ እናንተ የነበራችሁ ጊዜ ባያልፍም ለዶክተር ዐቢይ ቅድሚያ ልትሰጡት የሚገባው ጣልቃ ባለመግባት ነው፤በግል ማማከር ተገቢ ስለሆነ ርግጠኛ ነኝ ምሁራዊ አመለካከት አለው።
  ስለዚህ በሩቁ”እሷን አትሹም”፣”መዋቅሩ የታለ?” “በጠመንጃ አይሆንም” እያሉ በተስፋ የቆሰለውን ሕዝብ ከማሳመም፤መቀራረብ የሕሊና-ዋጋ አለው እላለሁ።
  ስለሠይፍ አስፈላጊነት የውትድርና ሙያ ላለው ከማስረዳ፣ለፖለቲከኛው ብመክረው ይሻላል።በሌላ በኩል ገዳዮች ያለርህራዬ ድንገት ሕዝብ መሃል ገብተው ሰዎችን ሲያስገድሉ ሥነ-ስርዓት የሚባልበት ሁኔታ አለ ማለት በሰው ሕይወት መቀለድ ይሆናል።እናም ትዕግስትም ልክ አላት እንደሙሴ ተምሳሌት።

  የማከብራችሁ አባቶቼ።

 3. መረራ የጠመንጃ ፖለቲካ ኣያስፈልግም! ሲል፤ እኛ ደግሞ፤ ድርሻችን ምን መሆን ኣለበት ኣይባልም?? ድርቅ! ነውር ነው!! ስለ ባህል፤ ስለ ታሪክ……ትፈተፍታላችሁ። ህዝቡን ወደ ክልሉ ምሩት። ሃሳቢ መሳዮች። ከኔ ምን ይጠበቃል ኣይባልም? ነውረኞች!! የምናከብረውን የኣማራን ህዝብ በናንተ ፈጠጤዎች ኣታሰድቡን። ወደ ባህር ዳር ምሩት!

Comments are closed.

Share