የአዲስ አበባ ወጣቶች ክስ ወደሽብርተኝነት ተቀየረ

(ዘ-ሐበሻ) የኦነግ አቀባበልን ተከትሎ በቡራዩና አካባቢው የተፈጠረውን ችግር ምክንያት በማድረግ ከታፈሱት የአዲስ አበባ ወጣቶች አብዛኛዎቹ ቢለቀቁም ማስረጃ አግኝቼባቸዋለሁ ያላቸው 83 ያህሉ በፍርድ ቤት ክሳቸው እየታየ መሆኑ ይታወቃል፡፡ እነዚህ ወጣቶች በአራዳ ፍርድ ቤት ጉዳያቸው በጊዜ ቀጠሮ ሲታይ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን ከትላንት በስቲያ ምክሰኞ ልደታ በሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ከፍተኛ ውዝግብ አስነስቷል፡፡ በዚህ የተነሳም በታሳሪ ቤተሰቦችና በፀጥታ አካላት መሃከል ግጭት ተቀስቅሶ እንደነበር ምንጮቻችን ገልፀውልናል፡፡

እንደነዚህ ምንጮች ወጣቶቹ ቀደም ሲል አራዳ ፍርድ ቤት ይቀርቡ የነበረው የተጠረጠሩበት ወንጀል ነፍስ ግድያና አካል ማጉደል ስለነበረ ነው፡፡ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ግን ክሳቸው ወደሽብርተኝነት ተቀይሮባቸዋል፡፡ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የሽብርን ወንጀል የማየት ስልጣን የለኝም በሚል ነው ልደታ ወደሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት መዝገባቸው የተዘዋወረው፡፡ በሽብር የተጠረጠረ ሰው የዋስትና መብት የሚከለከል መሆኑ ይታወቃል፡፡

ጃዋር መሃመድ የኦነግን አቀባበል ተከትሎ በሳሪስና መርካቶ 43 ሰዎች ተገደለዋል::” ብሎ መናገሩ ይታወሳል:: የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽን ኮምሽነር ሜጀር ጀነራል ደግፌ በዲ በበኩላቸው “በኦነግ አቀባበልን ተከትሎም በአዲስ አበባ 28 ሰዎች ሞተዋል:: ከእነዚህም ውስጥ በፀጥታ ኃይል የተገደሉ 7 ብቻ ናቸው:” ማለታቸው ይታወሳል::

https://www.youtube.com/watch?v=NaLy5pGAFTc

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሜይ 1 2011 ሪፖርተር ጋዜጣ

2 Comments

  1. ይቀልዳሉ! አህያውን ፈርቶ ዳውላውን፡፡ አገሩን እያተራመሰ ያለው፣ ህዝብ እያፈናቀለ ያለው የዳዊት ኢብሳ ጀሌ መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ ለምን እነሱን ፍርድ ላይ አያቀርቡም? የጃዋር ቆርቆሮዎች ያደረጉትን አይተናል ቡራዮ ውስጥ ለምን እነሱን ፍርድ ላይ አያቀርብም? እረ ለመሆኑ ሰውን እየዘቀዘቁ እንደ በግ ዛፍ ላይ ለሰቀሉት ወንጀል የታሰረ አለ? ከታሰሩስ ጉዳያቸው ምን ደረሰ? አገር ውስጥ ህግ አለ ብሎ ለይስሙላ ለማሳየት እነዚህን ምስኪን ወጣቶች መጠቀሚያ አታድርጉ፡፡ ማፈሪያዎች!!

  2. Woyane-TPLF-District 1 imprisoned federal officials that went to Tigray, conquered Badme, steals billions of dollars public money through corruption with the help of business people of Addis.

    In Addis Ababa economy is controlled by TPLF, Merkato is mostly Tigre-woyane owned,Addis Ababa city administration key posts are taken by woyane-METEC. Now in a country where freedom of speech doesn’t exist the Addis Ababa youth shed a light on the lack of Justice by breaking some windows of Tigrayan woyane-METEC owned shops in Merkato. For that action they called them terrorists, while the corrupt shop owners steal Addis Ababa the law enforcement look the other way.Right now Addis Ababa is full of shit.Tigrayans shit allover Addis Ababa while others ethnicities that don’t get help from diaspora eat shit and die.The Addis Ababa youth that is not willing to eat shit and die is subjected to exile or imprisonment even in the so called change time if of the hiippies summer if love and forgiveness,EPRDF woyane-METEC trained double agent Abiy’s time. Abiy is a double agent that has the file of the added opposition selling it to TPLF business people .The youth is being detained in Addis Ababa so TPLF keeps bleeding Addis Ababa dry .Abiy and the new elected top law enforcement official should resign right now because they are incapable of facing TPLF head on.

Comments are closed.

Share