ፓርላማው በሙስና/ሌብነት የተጠረጠሩ አባላቱን ያለመከሰስ መብት ሊያነሳ ነው

(ዘ-ሐበሻ) ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ እርምጃ አልወሰዱም ተብለው ከሚተቹባቸው ምክንያቶች አንዱ በሌብነት የበሰበሱ ባለስልጣናት ላይ እርምጃ አለመወሰዳቸው ይጠቀሳል:: በሌብነት ተጨማልቀዋል ተብለው ከተጠረጠሩት መካከል ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ስጣልን ከመጡ ወዲህ ስም ካላቸው ባለስልጣናት መካከል በሌብነት የተጥርጦ ባለፈው ሰኔ የታሰረው ሕወሓቱ የቀድሞ ኢንሳ ም/ዳይሬክተር ቢኒያም ተወልደ ሲሆን ሌሎች ባለስልጣናት ሳይነኩ መቅረታቸው አነጋጋሪ ሆኖ ቆይቷል::

በዚህም መሰረት ኢህአዴግ 100% የሚቆጣጠረው የተወካዮች ምክር ቤት በቀናት ውስጥ በሚያከናውነው ስብሰባው በከፍተኛ ሙስና የተጠረጠሩ አባላቱን ያለመከሰስ መብት እንደሚያነሳ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልጸዋል::

የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንዳሉት ያለመከሰስ መብታቸው ከሚነሳው ባለስልጣን የፓርላማው አባላት ውስጥ ውስጥ ባለፈው 27 አመታት በከፍተኛ ስልጣን ላይ የቆዩ ይገኙበታል፡፡

ዘ-ሐበሻ ከ3 ቀን በፊት በዜና እወጃው ፌዴራል ፖሊስና አቃቤ ሕግ በ33 ትላላቅ ኩባንያዎች ላይ ምርመራ እያደረገ መሆኑንና ከግማሽ በላይ የሆኑት ምርመራ መጠናቀቁ መዘገቡ ይታወሳል:: በዚህ ምርመራ ላይም ቢሊዮን ብሮች የሚቆጠሩ ወንጀሎችን እንዳገኘ ዘግበናል:: ይህ ምርመራ ያለመከሰሰ መብታቸው ከሚነሳባቸው ባለስልጣናት ጋር የሚያያዘው ነገር እንዳለ ዘ-ሐበሻ ምንጮቹን ጠይቆ በቂ ምላሽ ባያገኝም በምርመራው የበርካታ ባለስልጣናት እጆች እንደተጨማለቁ ገልጸውልናል::
https://www.youtube.com/watch?v=NaLy5pGAFTc

ተጨማሪ ያንብቡ:  ETHIOPIA-SUDAN: Over 4,000 Ethiopian troops for Abyei peace mission

1 Comment

Comments are closed.

Share