October 20, 2018
3 mins read

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስምምነት ከተደረገባቸው አገራት ውጪ የሚደረግ ሕገወጥ ጉዞ መቆም እንዲቆም ማሳሰቢያ ሰጡ

92062

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ባለድርሻ አካላት ኢትዮጵያ ስምምነት ካደረገችባቸው 3ቱ የአረብ ሀገራት የውጭ ሀገር ጉዞ ውጪ የሚደረገውን ሕገወጥ ጉዞ በማስቆም የድርሻቸውን እንዲወጡ ማሳሰቢያ ሰጡ::

ም/ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን በመከላከል ኃላፊነት ለተሰጣቸው የፌዴራል ፖሊስ፣ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ ኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳዮች መምሪያ፣ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣንና ኢትዮጵያ አየር መንገድ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡
አቶ ደመቀ መንግሥት መስራት ለሚችሉ ዜጎች በሀገር ውስጥ ምቹ የሥራ ዕድሎች የሚስፋፊበት ሁኔታ ለመፍጠር የሚያደርገው ጥረት እንደተጠበቀ ሆኖ ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ ለመሥራት ፍላጎት ያላቸው ኢትዮጵያውያን መብታቸው ደህንነታቸው እና ክብራቸው ተጠብቆ ባላቸው ችሎታና አቅም ሰርተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል የኢትዮጵያ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት አዋጅ ቁጥር 923/2ዐዐ8 ማውጣቱን ለተቋማቱ በፃፉት ደብዳቤ አመልክተዋል፡፡

በዚሁ መሠረት አሁን ላይ የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈርሞ ሰራተኞችን ለመላክ ቅድመ ዝግጅት የተደረገባቸው ሀገራት ሳዑዲ አረቢያ፣ ኳታር እና ጆርዳን ብቻ መሆናቸውንም በደብዳቤያቸው ተጠቅሷል፡፡

ሆኖም ግን የሁለትዮሽ ስምምነት ካልተደረገባቸው ሀገራት መካከልም ኩዌት፣ ባህሪን፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ፣ ቤይሩት እና ኦማን በተለያዩ የቪዛ አይነቶች ማለትም በቱሪስት በዘመድ ጥየቃ፣ በጉብኝት፣ በንግድ በመሳሰሉት ምከንያቶች ከሀገር እየወጡ ሕገወጥ የሥራ ስምሪት የሚያደርጉ ግለሰቦች እንዲሁም በዚህ መልኩ ዜጎችን ወደ ውጭ የሚልኩ ኤጀንሲዎች መኖራቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

በመሆኑም በዜጎች ላይ የሚደርሰውን የመብት ጥሰት ለመታደግ የሁለትዮሽ ስምምነት ወዳልተደረገባቸው ሀገራት በተለያዩ የቪዛ አይነቶች ለሥራ የሚሄዱ ዜጎች እና በዚህ ሁኔታ ዜጎችን የሚልኩ ኤጀንሲዎች ድርጊታቸው ሕጋዊ መሠረት የሌለው መሆኑ ታውቆ ጉዳዩ የሚመለከታቸው እነዚህ ተቋማት በሙሉ ሀገራዊ የሥራ ስምሪቱ በይፋ ከተከፈተበት ከመስከረም 30/2011 ጀምሮ ሕገወጥ አሠራሩ በአስቸኳይ እንዲቆም ጥብቅ ቁጥጥር እና ክትትል እንዲያደርጉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል::
https://www.youtube.com/watch?v=mH0UhciQumI&t=788s

92055
Previous Story

አብዲ እሌ የፖሊስ አባልን አንቀው ከ እስር ቤት ሊያመልጡ እንደነበር ፖሊስ ተናገረ

Next Story

ብሔራዊ የእርቅ ጉባኤ አሁኑኑ!!!!! – ጌድዮን በቀለ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop