አብዲ እሌ የፖሊስ አባልን አንቀው ከ እስር ቤት ሊያመልጡ እንደነበር ፖሊስ ተናገረ

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልልን ሲመሩ ቆይተው በክልሉ ለተፈጸሙ ግድያዎችና ማሰቃየቶች ተጠያቂ ናቸው በሚል ተ endihum ከሐምሌ 26-30 ቀን 2010 ዓ.ም በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ ሳቢያ teጠርጥረው የታሰሩት አብዲ መሀመድ (አብዲ ኢሌ) የፖሊስ አባል አንቀው ከእስር ቤት ሊያመልጡ ሲሉ መያዛቸውን ፖሊስ ለፍርድ ቤት አስረዳ::

አቶ አብዲ ዛሬ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀጠሮ ችሎት በቀረቡበት ወቅት መርማሪ ፖሊስ እንደገለጸው አቶ አብዲ መሐመድ ለደህንነታቸውና ለጤናቸው ሲባል የፖሊስ ቢሮ ውስጥ ታስረው ነበር።
ይሁንና አቶ አብዲ የታሰሩበትን ቢሮ መስታወት በመስበርና አንድ የጥበቃ አባልን ጉሮሮ በማነቅ ለማምለጥ ሙከራ አድርገዋል ብሏል።
አቶ አብዲ መሐመድ በበኩላቸው ድርጊቱ ሆን ብሎ ስሜን ለማጥፋትና እኔን ለመምታት የተደረገ ሴራ ነው ብለዋል።
ድርጊቱን ፈጽመዋል መባሉ ውሸት መሆኑንና በእርሳቸው ላይም ከፍተኛ ጫና እየተደረገባቸው እንደሆነ ተናግረዋል።
ምቹ ባልሆነ እስር ቤት መታሰራቸውን፣ የአዕምሮ ህመምተኛ የሆነ ታሳሪ የታሰሩበትን ክፍል በር ገንጥሎ በመግባት ሁለት ቀን ጉዳት ሊያደርስባቸው እንደሞከረና ይህም በደህንነታቸው ላይ ስጋት እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል።
በአንድ አጋጣሚም አንድ አስረኛ የሽንት ቤት በር ገንጥሎ እሳቸው ላይ በመጣል ጉዳት ሊያደርስ መሞከሩንም ተናግረዋል።
የታሰሩበት እስር ቤት የማይመችና በጤናቸው ላይም እክል እንደፈጠረባቸውም ነው አቶ አብዲ የተናገሩት።
መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ አቶ አብዲ መሐመድ ማንኛውም እስረኛ በሚቆይበት እስር ቤት እንደታሰሩ ገልጸው በእርሳቸው ላይ ምንም አይነት የተለየ ጫና እየተደረገ እንዳልሆነ አስታውቋል።
በተጨማሪም ፖሊስ ከእርሳቸው ጋር ውይይት ባደረገበት ወቅት ለግጭቱ መቀስቀስ ተጠያቂ መሆናቸውንና በዚህም ተጸጽተው ይቅርታ መጠያቃቸውን ገልጿል።
ፖሊስ በአብዲ መሐመድ የክስ መዝገብ ተጨማሪ መረጃ ለማሰባሰብ የ10 ቀን የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።
ፍርድ ቤቱ ምርመራውን እያካሄደ ያለው ፖሊስ የምርመራውን ውጤት ለጥቅምት 19 ቀን 2011 ዓ.ም ይዞ እንዲቀርብ በማሳሰብ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ባለፈው ሳምንት አብዲ ኢሌ የ እስር ቤቱን በር ለመስበር በመሞከራቸው እና ከግድግዳ ጋር ራሳቸውን እያጋጩ በማስቸገራቸው ፖሊስ ካሰራቸው የቭአይፒ ክፍል ቀይሮ ከሌሎች እስረኞች ጋር እንደቀላቀላቸውና እንደተለመደው በየቀኑ እንዳይጠየቁ; ከዚህ በፊት እንደነበረው ከቤተሰብ ጋር ቁጭ ብለው ምግብ እንዳይበሉ መደረጉን ዘ-ሐበሻ ዘግቦ ነበር::
https://www.youtube.com/watch?v=mH0UhciQumI

ተጨማሪ ያንብቡ:  ለማ መገርሳ በመደመር ፍልስፍና እንደማይስማሙ ገለፁ
Share