ኮ/ል መንግስቱ ሃይለማርያም ዛሬ ልደታቸው ነው

(ሐበሻ) የቀድሞው የኢትዮጵያ ወታደራዊ መንግስት ፕሬዚዳንት ኮለኔል መንግስቱ ኃይለማርያም ዛሬ  የልደት በዓላቸውን እያከበሩ ነው::

ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለ ማርያም1966 እስከ 1983 .. 17 ዓመታት የኢትዮጵያ መሪ ነበሩ። ወደ ስልጣን የወጡት በደርግ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ንጉሠ ነገሥቱን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን በመገልበጥ ሲሆን ተቃናቃኝቻቸው የነበሩትን የቅርብ ጓደኞቻቸውንና የደርጉን መሥራቾች ባማስወገድ ብቸኛ የአብዮቱ መሪ ሆነው ቆይተዋል::

በአሁኑ ወቅት በዙምባቤዌ በጥገኝነት ኑሯቸውን እየገፉ ያሉት ኮለኔሉ ከሮበርት ሙጋቤ የስልጣን መውረድ ጋር ተያይዞ ባለፈው ዓመት ስማቸው በየሚዲያው ሲነሳ ነበር:: በቅርቡም አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር / ዓብይ አህመድምከፈለገ መንግስቱ ኃይለማርያምም ወደ ሃገሩ መመለስ ይችላልማለታቸው ከተዘገበ በኋላ እንዲሁ መነጋገሪያ ሆነው ቆይተዋል::

የኮለኔል መንግስቱ ኃይለማርያም ልጅ / ትእግስት መንግስቱ በፌስቡክ ገጿ ለአባቷ መልካም ልደት ተመኝታከብዙ አደጋ ጠብቆ ለዚህ ቀን ያበቃህ እግዚአብሄር ይተመሰገነ ይሁን :: እግዚአብሄር ይባርክህ:: እግዚአብሄር ኢትዮዽያን ይባርክስትል መልካም ምኞቷን ገልጻለች::

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኦነግ ጦር የደቡብ ዞን አዛዥ የሰላም ጥሪውን ተቀበለ

7 Comments

  1. Mengistu killed top-skilled Ethiopian Generals and Colonels and helped fascist Woyane & Shabia to take over Ethiopia.
    He doesn’t deserve to be remembered at all. Listen to what he did to his close friend Colonel Atnafu Abate. Mengistu was a cruel butcher.

    https://www.youtube.com/watch?v=5-NA9eyVC0g

  2. በርግጥ ይህን ብሏል??? “ኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር ዓብይ አህመድም “ከፈለገ መንግስቱ ኃይለማርያምም ወደ ሃገሩ መመለስ ይችላል” እድሜ ሰጥቶት በእጁ ላይ ያለውን የስንት ህዝብ ደም በፍርድ እንዲከፍል ምኞቴ ነው፡፡ ለኢትዮጵያ ውድቀት ዋንኛው ተጠያቂዎች መንግስቱና የመለሰ ወያኔ አስተዳደር ነው፡፡ ሁለቱም የአገር አሳፋሪዎች ናቸው፡፡

    ምን ይታወቃል መንግስቱንም ሆ ብለው ይቀበሉት ይሆናል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ የማስታወስ ርቀቱ አጭር መሆኑ የሚያሳዝነው ለመለሰ አይነት ጊዜ የሰጠው ዱርዪ ኢትዮጵያን ከፋፍሎ፤ የጫካ ግብረአበሮቹን የአገር አስተዳዳሪ አድርጎ በእፍረት ያሸማቀቀንን ዱርዪ ሲሞት በእንባ የተራጨ ግዜ ነው፡፡
    I hope they burn in hell!

  3. ኮለኔል መንግስቱና አባሮቻቸው ወጣቱንና የድሮ ባለስልጣኖችን ያለፍርድ በመጨፍጨፍ በታሪክም በህግም መጠየቅ ያለባቸው ግለሰብ ናቸው።

  4. I love Menge but he is the one responsible for the cuurent situatilon of the country.

Comments are closed.

Share