በነቀምት ሆስፒታል 10 እናቶች በወሊድ ምክንያት ህይወታቸው አለፈ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በነቀምት ሆስፒታል በቅርቡ 10 እናቶች በወሊድ ምክንያት መሞታቸውን እና ፤ አንድ ሊትር ደም እስከ ሶስት ሺህ ብር መሸጡም ተጠቁሟል፡፡ በሆስፒታሉ ችግሩ እየከፋ በመሄዱ ወላድ እናቶች እና ታካሚዎች ተገቢውን የህክምና አገልግሎት ባለማግኘታቸው በዚሁ ሆስፒታል 10 እናቶች ህይወታቸው ማለፉ ተጠቁሟል፡፡

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትም ጉዳዩን አውቆት በስብሰባ መድረክ ያነሳው ቢሆንም እስካሁን የተወሰደ እርምጃ ባለመኖሩ የሆስፒታሉ ተገልጋዮች ቅሬታ እንዳደረባቸው ኢቲዮ ምህዳር ጋዜጣ በዛሬው ዘገባ አስታውቋል፡፡ የፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አንድም እናት በወሊድ ምክንያት አትሞትም እያለ መፈክር ቢያስነግርም በተግባር ግን የነፍሰጡር እናቶች ህልፈት እየተባባሰ እንደሚገኝ መረጃዎች ጠቁማሉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኤርሚያስ አመልጋ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በላኩት ደብዳቤ ዘመን ባንክን ቦይኮት አድርጉ ብለዋል (በቪዲዮ የቀረበ)

3 Comments

  1. abet wushet abet wushet…..eskahun ewunet yemitaweru mesilogn sanebachihu neber….ahun gin teyazachihu….ere God ewunet Nafeken,ye ETV wushet,ye esat wushet,ye zehabesha wushet,ye addiss zemen wushet…wushet wushet wushet….

  2. በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን ጋንዲ የእናቶችና ህፃናት ህክምና ሆስፒታል ምጥ ጠንቶባት የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ሚስት፣ እህት ወይም ማንኛዋንም ሴት ተከትላችሁ የመሄድ እድሉ አጋጥሟችሁ የምታውቁ ካላችሁ የሆስፒታሉ ባለሙያዎች ዋልጌነት ምን ያህል ስር የሰደደ እንደሆነ በተረዳችሁ ነበር። መፈክሩ እንድም እናት በወሊድ እንዳትሞት ሳይሆን አንድም እናት እንዳትተርፍ የተባለ ይመስላል።

  3. be neqemt hosoital yetasert dr.mann zor blooo ayacheew yehew teferdobacheew aluuu ke 20 ameet belaay be muyaaw yeseruu yasaznaal hegerituu ekoo et. naat

Comments are closed.

Share