October 23, 2013
160 mins read

‘‘መላኩ ፈንታ ሥልጣናቸውን መከታ በማድረግ የሶስት ልጆች እናትን ከትዳሯ አፋተው አግብተዋል’’ – ዐቃቤ ሕግ

Melaku Fenta and Gebrewahid Woldegiorgis

በሰንደቅ ጋዜጣ ሪፖርተር

የፌዴራሉ የሥነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዐቃቤ ህግ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣናት እና ግብረ አበር ባለሀብቶች ላይ የመሰረተውን ክስ በፍርድ ቤት ማሰማት ጀምሯል። የኮሚሽኑ ዐቃቤ ህግ በተለይም በአንደኛው ተከሳሽ በአቶ መላኩ ፈንታ ላይ መዝገብ ቁጥር 14356 ስር ባለው 11ኛ ክስ ውስጥ ተከሳሹ በትዳር ያለችን ሴት አስኮብልለዋል የሚል ክስ መስርቶባቸዋል።
ትናንት በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ክሱ ሲነበብ፤ 1ኛው ተከሳሽ አቶ መላኩ ፈንታ የስራ ኃላፊነታቸውን በመጠቀም ለስራ ጉዳይ የመጣችን ሴት፤ ትዳሯን ፈታና በትዳር ውስጥ ያፈራቻቸውን ሦስት ልጆች በትና አብራቸው እንድትሆን አድርገዋል ሲል ስልጣንን ያለአግባብ የመጠቀም የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል ሲል ከሷቸዋል።

ወ/ሮ መቅደስ ለማ የተባሉት እኚሁ ሴት የቀድሞ ባለቤታቸውን ንብረት የሆነውን ሳንክቸሪ ኢንተርናሽናል ኃ/የተወሰነ የግል ማህበር በ2001 ዓ.ም የስራ ግብር ለመክፈል ወደገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሲሄዱ 144 ሺህ ብር እንዲከፍሉ በመጠየቃቸውና በዚህም ምክንያት አቤቱታ ለማቅረብ ወደ ምስራቅ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ለአንድ አመት ከ4 ወር መጉላላታቸውን ለማስረዳትና መፍትሄ ለማግኘት ወ/ሮ መቅደስ ለማ የአቤቱታ ደብዳቤ ይዘው ወደተከሳሹ ዘንድ በቀረቡበት ወቅት የፍቅር ግንኙነት መጀመራቸውን በክስ መዝገቡ ያትታል።
በዚህም መሠረት ተከሳሽ የነበረውን ስልጣን መከታ በማድረግ ባለጉዳዩዋ ቀደም ሲል ከከፈሉት ብር ውስጥ አንድ መቶ ሺህ ብር ተመላሽ እንዲሆን አድርጓል፤ በትዳር ውስጥ ያለችን ሴትም አማግጧል ሲል የሙስና ክስ መስርቷል።
ዐቃቤ ህግ በዚህ ክስ ዝርዝር ውስጥ በተጨማሪነትም ተከሳሽ በጋብቻ ውስጥ ያለችን ሴት በመንግስት ተሽከርካሪና ነዳጅ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ክብረ በዓል ላይ እንድትገኝ ከማድረጉም በላይ ቀኑ በውል ባልታወቀበት ዕለትም፤ በጋብቻ ውስጥ የነበረችው መቅደስ ለማን በግል ሾፌሩ አማካኝነት ወደ ባህርዳር ከተማ እንድትሄድ በማድረግ ሰመርላንድ ሆቴል ለአንድ ሳምንት አብረው እያደሩ እና በሾፌሩ አማካኝነት ከተማ ውስጥ ተዝናንታለች ሲል፤ የተፈፀመው ወንጀል መንግስትና ህዝብ የጣለበትን አደራ ያለአግባብ የመጠቀም ሙስና ሰርቷል ይላል። (በእነ መላኩ ፈንታ መዝገብ ሥር ያሉትን 24 ተከሳሾች የክስ ሙሉውን ጭብጥ እነሆ)

ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት
አዲስ አበባ

የፌ/ሥ/ፀ/ሙ/ኮ/መ/ቁ.
የዐ/ህ/መ/ቁ.
የከ/ፍ/ቤ/ወ/መ/ቁ/ 141352
ከሣሽ ………….. የፌደራል የሥነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮማሽን ዐቃቤ ሕግ
ተከሣሾች ……… 1ኛ/ አቶ መላኩ ፈንታ ቻይ
ሥራ፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋ/ዳይሬክተር
2ኛ. አቶ ገ/ዋህድ ወ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል
ሥራ፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የሕግ ማስከበር ዘርፍ ም/ዋ/ዳይሬክተር
3ኛ. አቶ በላቸው በየነ ገ/ጊዮርጊስ
ሥራ፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
4ኛ. አቶ ማርክነህ አለማየሁ ወዴቦ
ሥራ፡- ም/ዋና ዐ/ሕግ
5ኛ. አቶ እሸቱ ግረፍ አስታክል
ሥራ፡- ገ/ጉ/ባለሥልጣን አ.አ ቃሊቲ ቅርንጫፍ የሕግ ማስከበር ኃላፊ
6ኛ. አቶ አስፋው ስዩም ተፈራ
ሥራ፡- ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት የጣቢያ አስተባባሪ
7ኛ. አቶ ያዴሳ ሚዴቅሳ ዲባባ
ሥራ፡- የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አዳማ ቅ/ፅ/ቤት ሥራ አስኪያጅ
8ኛ. አቶ አስመላሽ ወ/ማርያም ገብሬ
ሥራ- የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት አፈፃፀም የሥራ ሂደት መሪ የነበረ
9ኛ. አቶ ነጋ ገ/እግዚአብሔር ደበበ
ሥራ፡- ነጋዴ
10ኛ. አቶ ከተማ ከበደ አስገልጥ
ሥራ፡- የግል ባለሀብት
11ኛ. አቶ ስማቸው ከበደ ካሳ
ሥራ፡- ነጋዴ
12ኛ. ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ ወርዶፋ
ሥራ፡- ሐኪም
13ኛ. ኮ/ል ኃይማኖት ተስፋዬ ገ/ስላሴ
ሥራ፡- የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ፌዴሬሽን ም/ስራ አስኪያጅ
14ኛ. አቶ ዳንኤል ገ/ኪዳን (ያልተያዘ)
ሥራ፡- የግብር አውሳሰንና ምርመራ ኦዲተር
15ኛ. አቶ አውግቸው ክብረት
ሥራ፡- ዐቃቤ ሕግ
16ኛ. አቶ ጌቱ ገለቴ (ያልተያዘ)
ሥራ፡- ነጋዴ
17ኛ. አቶ ገ/ስላሴ ገብረ ኃ/ማርያም
ሥራ፡- ነጋዴ
18ኛ. ኬኬ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
ሥራ፡- ጄ.ኤች.ሲሜክስ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
19ኛ. ጄ.ኤች ሲሜክስ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
20ኛ. ነፃ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
21ኛ. ጌታስ ኃ/የተ/የግ ማኅበር
22ኛ. ኮሜት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር
23ኛ. አቶ ፍፁም ገብረመድህን አብርሃ
ሥራ፡- ነጋዴ
24ኛ. አቶ ወልደስላሴ ወ/ሚካኤል
ሥራ፡- የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አማካሪ

1ኛ ክስ
በ1ኛ፣ 2ኛ እና 10ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)፣ 33፣ 411(1) (ሐ) እና 2 ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር
1ኛ እና 2ኛ ተከሣሾች እንደ ቅደም ተከተላቸው በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር እና ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ ሲሆኑ፤ ስልጣንና ኃላፊነታቸውን በመጠቀም የማይገባ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት በማሰብ፣ 10ኛ ተከሳሽም በመንግስት ሰራተኞች ብቻ በሚፈፀም የሙስና ወንጀል ልዩ ተካፋይ በመሆን፣
– 1ኛና 2ኛ ተከሳሾች በ2001 ዓ.ም በተካሄደው አራጣ አበዳሪዎችን ለሕግ የማቅረብ ተግባር በተጀመረበት ወቅት ለተከሳሹ በጥቆማ መልክ ከቀረቡት ዘጠኝ አራጣ አበዳሪዎች ስም ዝርዝር መካከል 10ኛ ተከሣሽ አራጣ አበዳሪ መሆኑን የሚያስረዱ ማስረጃዎች ቀርበውለት እያለ የተከሳሹ ጉዳይ በምርመራ ተጣርቶ ለሕግ እንዲቀርብ ማድረግ ሲገባው ከዚህ በተቃራኒው ከተከሣሹ ጋር በፈጠሩት ሥውር የጥቅም ግንኙነት ሌሎች አራጣ አበዳሪዎች ምርመራ ተጣርቶባቸው ለሕግ ሲቀርቡ ያለምንም ሕጋዊ ምክንያት 10ኛ ተከሳሽ ላይ ምርመራ እንዳይጣራና ሕግ ፊት ቀርቦ እንዳይጠየቅ በማድረጋቸው፣
– 10ኛ ተከሳሽ በበኩሉ ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ አራጣ አበዳሪነቱን የሚያስረዱ ማስረጃዎች ቀርቦበት እያለና ሌሎች አራጣ አበዳሪዎች ሕግ ፊት ቀርበው ሲከሰሱ ከ1ኛ እና 2ኛ ተከሣሾች ጋር በስውር በፈጠረው ሚስጥራዊ የጥቅም ግንኙት በአራጣ አበዳሪነቱ ምርመራ እንዳይጣራበትና ሕግ ፊት ቀርቦ እንዳይጠየቅ የ1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾችን ሽፋን አግኝቶ ሕገወጥ ተጠቃሚ በመሆኑ፣
በአጠቃላይ ሁሉም ተከሳሾች በሙሉ ፈቃዳቸውና ዕወቀታቸው የወንጀሉ ሙሉ ተካፋይ በመሆን በተሰጣቸው የመንግሥት ኃላፊነት ሊጠብቁትና ሊከላከሉት የሚገባውን የመንግስትና የሕዝብ ጥቅም በሚጎዳ አኳኃን በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት የመንግስት ስራን በማያመች አኳኃን መምራት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
2ኛ ክስ
በ1ኛ፣ 2ኛ፣ 3ኛ እና 11ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)፣ 33፣ 411(1) (ሐ) እና 2 ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር
1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ ተከሣሾች እንደ ቅደም ተከተላቸው በኢትዮጰያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ እና የኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሲሆኑ፣ ስልጣንና ኃላፊነታቸውን በመጠቀም የማይገባ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት በማሰብ፣ 11ኛ ተከሳሽም በመንግስት ሰራተኞች ብቻ በሚፈፀም የሙስና ወንጀል ልዩ ተካፋይ በመሆን፣
– 1ኛ ተከሣሽ በ2003 ዓ.ም ለሆቴል አገለግሎት የሚውሉ እቃዎችን ከቀረጥ ነፃ ያስገቡ ሆቴሎች ከቀረጥ ነፃ ያስገቡትን ዕቃ ከታለመለት ዓላማ ውጭ እየተገለገሉበት ስለመሆኑ መረጃ ደርሶት ጉዳዩ በባለሥልጣኑ የኢንተለጀንስ ክፍል ጥናት እንዲደረግ ተወስኖ ጥናትና የኦዲት ክትትል ከተደረገ በኋላ ጥናት ከተደረገባቸው ሆቴሎች መካከል አንዱ ጄ.ኤች ሲሜክስ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር (ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል) ሲሆን በተካሄደው ጥናትና የኦዲት ክትትል መሠረት ወንጀል መፈፀሙን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎች ቀርቦ እያለና ሌሎች ተመሣሣይ ድርጊት የፈፀሙ ሆቴሎች ምርመራ እንዲጣራባቸው ሲደረግ የ11ኛ ተከሣሽ ሆቴል ከቀረጥ ነፃ ያስገባቸውን ዕቃዎች ለተፈለገው ዓላማ አለማዋሉን በ26/11/2002 እና በ19/16/03 ዓ.ም በተደረገው ቆጠራ በማስረጃ ተረጋግጦ እያለ ከ11ኛ ተከሣሽ ጋር በስውር በመመሣጠር የተፈፀመው ሕገወጥ ድርጊት ምርመራው እንዳይጀመርና ተከሳሹ ለሕግ እንዳይቀርብ በማድረጉ፣
– 2ኛ ተከሣሽ በበኩሉ ከላይ በተ.ቁ. 1 በተጠቀሰው ጊዜና አኳሃን የ11ኛ ተከሣሽ ሆቴል ከቀረጥ ነፃ ያስገባቸውን ዕቃዎች ለተፈለገው ዓላማ አለማዋሉን በተካሄደው ቆጠራ ተረጋግጦና ሌሎች ተመሣሣይ ድርጊት የፈፀሙ ሆቴሎች ምርመራ እንዲጣራባቸው ሲያደርግ ከ11ኛ ተከሳሽ ጋር በስውር በመመሳጠር ከላይ በተጠቀሰው ሆቴል ላይ ምርመራው እንዳይጀመርና ለሕግ እንዳይቀርብ በማድረጉ፣
– 3ኛ ተከሣሽ በበኩሉ ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና አኳኃን የ11ኛ ተከሣሽ ሆቴል ከቀረጥ ነፃ ያስገባቸውን ዕቃዎች ለተፈለገው ዓላማ ማዋል አለማዋሉን ለማረጋገጥ ቡድን አቋቁሞ ወደ ሆቴሉ በመላክ በተደረገው ቆጠራ ብር 9‚981‚651.83 (ዘጠኝ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሰማንያ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ሃምሳ አንድ ብር ከ83/100) ከቀረጥ ነፃ ያስገባቸውን ዕቃዎች ለተፈለገው ዓላማ አለማዋሉን በቡድኑ ተረጋግጦ እያለ ተከሣሹ አቤቱታ እንዲያቀርብና ድጋሚ ቆጠራ እንዲደረግ ከማድረጉም በላይ በድጋሚ ቆጠራውም ብር 8‚716‚012.84 (ስምንት ሚሊዮን ሰባት መቶ አስራ ስድስት ሺህ አስራ ሁለት ብር ከ84 ሳንቲም) እንዲከፍል በመወሰን ድርጅቱ ምርመራ እንዳይጣራበትና በወንጀል እንዳይከሰስ ሁኔታዎችን በማመቻቸቱ፣
– 11ኛ ተከሳሽ በበኩሉ ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና አኳኃን ለድርጅቱ መገልገያ የሚሆኑ የሆቴል ዕቃዎች ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገባ ተፈቅዶለት አስገብቶ ለተፈቀደለት ዓላማ ማዋል ሲገባው ከተፈቀደለት ዓላማ ውጭ መጠቀሙን በገ/ጉ/ባለሥልጣን ባለሙያዎች ተረጋግጦ እያለ በፈፀመው ድርጊት በወንጀል መጠየቅ ሲገባው ከ1ኛ-3ኛ ከተጠቀሱት ተከሣሾች ጋር በጥቅም በመመሣጠር ከ1ኛ እስከ 3ኛ የተጠቀሱት ተከሳሾችን ሽፋን አግኝቶ በወንጀል እንዳይጠየቅ በማድረግ ሕገወጥ ተጠቃሚ በመሆኑ፣
በአጠቃላይ ሁሉም ተከሳሾች በሙሉ ፈቃደቸውና ዕውቀታቸው የወንጀሉ ሙሉ ተከፋይ በመሆን በተሰጣቸው የመንግሥት ኃለፊነት ሊጠብቁትና ሊከላከሉት የሚገባውን የመንግስትና የሕዝብ ጥቅም በሚጎዳ አኳኃን በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት የመንግስት ስራን በማያመች አኳሃን መምራት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።

3ኛ ክስ
በ1ኛ፣ 2ኛ፣ እና 12ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)፣ 33፣ 411(1) (ሐ) እና 2 ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር
1ኛ እና 2ኛ ተከሣሾች እንደ ቅደም ተከተላቸው በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር እና ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ ሲሆኑ፤ ስልጣንና ኃላፊነታቸውን በመጠቀም የማይገባ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት በማሰብ፣ 12ኛ ተከሳሽም በመንግስት ሰራተኞች ብቻ በሚፈፀም የሙስና ወንጀል ልዩ ተካፋይ በመሆን፣
– 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች 12ኛ ተከሳሽ ጥቅምት 20 ቀን 2003 ዓ.ም በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ከስዊድን ሀገር ወደ ኢትዮጵያ ምንም ዓይነት የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ያልተፈፀመባቸውንና ገደብና ቁጥጥር የሚደረግባቸውን 32 ዓየነት የተለያዩ ብዛት ያላቸው የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎችን በአራት ሻንጣ ሲያስገባ ተይዞ 5% ቀረጥና ታክስ ከፍሎ ወደ መጣበት ሀገር እንዲመልስ ተወስኖ ሕዳር 1 ቀን 2003 ዓ.ም ታግ ተለጥፎበት ቤልት ላይ ከገባ በኋላ ከሀገር እንዲወጣ የተባለውን ዕቃ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ደብቆ መልሶ ወደ ሀገር ውስጥ ሊያስገባ ሲል ተይዞ በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 9/1/ የተመለከተውን በመተላለፍ በፈፀመው የኮንትሮባንድ ወንጀል በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተከሶ ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙን ማስረጃ ሰምቶ ካጠናቀቀ በኋላ ለፍርድ ተቀጥሮ ባለበት ሁኔታ ከተከሳሹ ጋር በፈጠሩት ሕግ ወጥ የጥቅም ግንኙነት እንዳይቀጣ በማሰብ ለፍርድ የተቀጠረውን ክስ ያለ ሕጋዊ ምክንያት እንዲነሳ በማድረጋቸው፣
– 12ኛ ተከሣሽም በፈፀመው ወንጀል ተከሶ የነበረ ቢሆንም ከ1ኛ እና የ2ኛ ተከሳሾች ጋር በፈጠረው የጥቅም ግንኙነት የተከሳሾችን ሽፋን አግኝቶ ክሱን በማስነሳት ሕገወጥ ተጠቃሚ በመሆኑ፣
በአጠቃላይ ሁሉም ተከሣሾች በሙሉ ፈቃዳቸውና ዕውቀታቸው የወንጀሉ ሙሉ ተካፋይ በመሆን በተሰጣቸው የመንግሥት ኃላፊነት ሊጠብቁትና ሊከላከሉት የሚገባውን የመንግስትና የህዝብ ጥቅም በሚጎዳ አኳኃን በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት የመንግስት ስራን በማያመች አኳኃን መምራት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
4ኛ ክስ
በ1ኛ፣ 2ኛ፣ 8ኛ፣ 9ኛ፣ 16ኛ፣ 17ኛ እና 24ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)፣ 33፣ 411(1) (ሐ) እና 2 ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር

1ኛ፣ 2ኛ፣ 8ኛ እና 24ኛ ተከሣሾች እንደ ቅደም ተከተላቸው በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ፤ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት አፈፃፀም የሥራ ሂደት መሪ እና 24ኛ ተከሳሽ ደግሞ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አማካሪ ሲሆኑ፣ ስልጣንና ኃለፊነታቸውን በመጠቀም የማይገባ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት በማሰብ፣ 9ኛ፣ 16ኛ እና 17ኛ ተከሳሾችም በመንግስት ሰራተኞች ብቻ በሚፈፀም የሙስና ወንጀል ልዩ ተካፋይ በመሆን፣
ከ1999 ዓ.ም እስከ 2000 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት በሀገሪቱ ተከስቶ የነበረውን የሲሚንቶ እጥረትና ዋጋውን ለማረጋጋት ከውጪ አገር ያለ ውጪ ምንዛሪ ክፍያ ከቀረጥ ነፃ ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ለሀገራዊ የቤቶች ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ ላይ ለማዋል ታሰቦ የገባው ሲሚንቶ ከታለመለት ዓላማ ውጪ ለ3ኛ ወገን በመተላለፉ ቀኑና ወሩ ለጊዜው ባልታወቀበት 2002 ዓ.ም ለ2ኛ ተከሳሽ እና እሱ ለሚመራው የሕግ ማስከበር ዘርፍ ጥቆማ ተደርጎ የብር 21‚602‚608.64 /ሃያ አንድ ሚሊዮን ስድስት መቶ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ስምንት ብር ከ64/100/ ቀረጥና ታክስ ባለመከፈሉ በመንግስት ላይ ጉዳት መድረሱ በመረጋገጡ ውሉን የተዋዋለው አቅራቢው ድርጅት፣ ትራንዚተሮች፣ ሲሚንቶውን በትራንስፖርት አስገብተው ለ3ኛ ወገን አሳልፈው የሰጡ አጓጓዥ ድርጅቶች እና ስራ አስኪያጆቻቸው ወይም ባለንብረቶቻቸው እንዲሁም ቁጥጥርና ክትትል ያላደረጉት የጉምሩክ ሰራተኞች ጭምር ተጠያቂ መሆናቸው በኣዲት ተረጋግጦ ቀርቦ እያለ ይህንኑ መነሻ በማድረግ ምርመራ በማጣራት አጥፊዎችን ለሕግ እንዲቀርቡ ማድረግ ሲገባቸው ከዚህ በተቃራኒው በመስራት ሕገወጥ ተጠቃሚ ለመሆን በማሰብ፣
– 1ኛ ተከሳሽ የመ/ቤቱ የበላይ ኃላፊ እንደመሆኑ የመ/ቤቱ ሰራተኛ የሆነው 8ኛ ተከሳሽ በደንብ ቁጥር 155/2000 መሰረት በፈፀመው ድርጊት በወንጀል እና በዲሲፒሊን እንዲጠየቅ ማስደረግ ሲገባው በፈፀመው ድርጊት እንዳይጠየቅ ከማድረጉም በተጨማሪ በዐቃቤ ሕግ በኩል ክሱ ሲቀርብበትም ተከሳሹን ለሕግ ማቅረብ ሲገባው ስራውን እንዲለቅ ማመልከቻ እንዱያቀርብ ሁኔታዎችን በማመቻቸቱና ሊጠየቁ በሚገባቸውም ሲሚንቶውን ባስገቡትና ባጓጓዙት በሁሉም የትራንስፖርት ድርጅቶች ላይ ክስ እንዲቀርብ ባለማስደረጉ፤
– 2ኛው ተከሳሽ በበላይነት በሚመራው የስራ ዘርፍ ምርመራው ሲጣራና ክሱ ሲቀርብ የባለስልጣኑ መ/ቤት ሰራተኛ የሆነው 8ኛ ተከሳሽ ቃሉን እንዳይሰጥ በማስደረግ፣ ደመወዝ እየተከፈለው ስራ ላይ ያለ ሰራተኛ መሆኑን እያወቀ ያለአግባብ በጋዜጣ ሲጠራም በዝምታ በማለፍ በመጨረሻም ከ1ኛው ተከሳሽ ጋር ተመካክሮ ተከሳሹ ስራውን እንዲለቅ በማስደረጉ እንዲሁም ሊከሰሱ ከሚገባቸው የትራንስፖርት ድርጅቶችና ባለንብረቶች ጋር ባለው ስውር የጥቅም ግንኙነት ምክንያት የራሱና የሌሎችን ጥቅም በሕገወጥ መንገድ ለማራመድ በማሰብ ጉዳዩን እንዲያጣራ ምንም ኃለፊነት ካልተሰጠው የደህንነት መ/ቤት ከፍተኛ አመራር ከሆነው 24ኛ ተከሳሽ ጋር በመሆን ጉዳዩን የሚያውቁ ሰዎችን እያስቀረበ ከመረመረ በኋላ ወንጀል የተፈፀመበት ሲሚንቶ የሌላ ሰው ነው ብላችሁ መስክሩ በማለት የጉዳዩን አቅጣጫ እሱ በሚፈልገው መንገድ እንዲሄድ ከመገፋፋቱም በላይ ኤ ኤንድ ጂ ድርጅት፣ ኃይሌ አሰፋ እና ሸሚዛል በተባሉት 3 ድርጅቶች ላይ ብቻ ምርመራው ተጣርቶ ክሱ እንዲቀርብ ሲያስደርግ ከእሱ ከ24ኛ ተከሳሽ ጋር የጥቅም ግንኙነት ባላቸው 1ኛ. ነፃ ትራንስፖርት ድርጅት እና የድርጅቱ ባለቤት የሆነው 9ኛ ተከሳሽ፣ 2ኛ. ጌታስ የተባለው ድርጅት እና የድርጅቱ ባለቤት የሆነው 16ኛ ተከሳሽ እና 3ኛ. ኮሜት ትራንስፖርት ድርጅት እና የድርጅቱ ባለቤት የሆነው 17ኛ ተከሳሽ ላይ ተነጥሎ ምርመራ እንዳየጣራባቸው በማስደረጉ፤
– 24ኛ ተከሳሽም በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መ/ቤት ውስጥ ከፍተኛ መዋቅር ላይ ተመድቦ ሲሰራ ይህን ስልጣንና ኃላፊነቱን አለአግባብ መከታ በማድረግ ከቀረጥ ነፃ የገበያ ሲሚንቶ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ለገቢዎችና ጉምረክ ባለስልጣን የቀረበውን ጥቆማና ምርመራ እንዲከታተል ከመ/ቤቱ ባልተወከለበት ሁኔታ የራሱና የሌሎችን ጥቅም በሕገወጥ መንገድ ለማራመድ በማሰብ በተለያዩ ቅናት 2ኛ ተከሣሽቢሮ ድረስ በመሄድ ጉዳዩን የሚያውቁ ሰዎችን እያስቀረበ ከመረመረ በኋላ ወንጀል የተፈፀመበት ሲሚንቶ የሌላ ሰው ነው ብላችሁ መስክሩ በማለት የጉዳዩን አቅጣጫ እሱ በሚፈልገው መንገድ እንዲሄድ ሙከራ ከማድረጉም በላይ ኤ ኤንድ ጂ ድርጅት፣ ኃይሌ አሰፋ እና ሸሚዛል በተባሉት 3 ድርጅቶች ላይ ብቻ ምርመራው ተጣርቶ ክሱ እንዲቀርብ ሲያስደርግ ከእሱና ከ2ኛ ተከሳሽ ጋር የጥቅም ግንኙነት ባላቸው 1ኛ. ነፃ ትራንስፖርት ድርጅት እና የድርጅቱ ባለቤት የሆነው 9ኛ ተከሳሽ፣ 2ኛ. ጌታስ የተባለው ድርጅት እና የድርጅቱ ባለቤት የሆነው 1ኛ ተከሳሽ እና 3ኛ. ኮሜት ትራንስፖርት ድርጅት እና የድርጅቱ ባለቤት የሆነው 17ኛ ተከሳሽ ላይ ተነጥሎ ምርመራ እንዳይጣራባቸው በማስደረጉ፤
– 8ኛ ተከሳሽ በዚህ ጉዳይ ተከሶ ፍ/ቤት እንዲቀርብ የታዘዘ ቢሆንም ከ1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ጋር ባለው የጥቅም ትስስር እና የነሱን ሽፋን ተጠቅሞ ፍ/ቤት ቀርቦ እንዳይጠየቅ በማስደረጉ፣
– 9ኛ፣ 16ኛ እና 17ኛ ተከሳሾችም ከቀረጥ ነፃ የገባ ሲሚንቶ አጓጉዘው ከታለመለት ዓላማ ውጪ ለ3ኛ ወገን ለመሸጣቸው ተረጋግጦ እያለ ከ2ኛ ተከሳሽ ጋር ባላቸው የጥቅም ትስስር ምክንያት በምርመራው እንደይካተቱ የ2ኛ ተከሳሽን ሽፋን አግኝተው በሕግ እንዳይጠየቁ በማስደረጋቸው፣ ሁሉም ተከሳሾች ሊጠብቁትና ሊከላከሉት የሚገባውን የመንግስትና የህዝብ ጥቅም በሚጎዳ አኳሃን በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈፀሙት የመንግስት ስራን በማያመች አኳሃን መምራት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።

5ኛ ክስ
በ1ኛ፣ እና 2ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)፣ 33፣ 411(1) (ሐ) እና 2 ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሣሾች እንደ ቅደም ተከተላቸው በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር እና ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ ሲሆኑ፤ ስልጣንና ኃላፊነታቸውን በመጠቀም የማይገባ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት በማሰብ፣
– 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ኢኖቫ ፓኬጂንግ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር እ.ኤ.አ በ2009 ለመንግስት መከፈል የነበረበትን ገቢ ግብር ብር 2‚088‚328.72 (ሁለት ሚሊየን ሰማንያ ስምንት ሺህ ሦስት መቶ ሃያ ስምንት ብር ከሰባ ሁለት ሳንቲም) ግብርን አሳውቆ ባለመክፈሉ እና ዓመታዊ ትርፉ 11‚448‚939.30 (አሥራ አንድ ሚሊዮን አራት መቶ አርባ ስምንት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ዘጠኝ ብር ከሰላሳ ሳንቲም) ሆኖ እያለ በበጀት ዓመቱ ያሳወቀው ግብር ብር 9‚569‚671.05 (ዘጠኝ ሚሊዮን አምስት መቶ ስልሣ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ ሰባ አንድ ብር ከዜሮ አምስት ሣንቲም) ነው ብሎ አሳሳች ማስረጃ በማቅረቡ በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 96፣ 102፣ 97/1/ እና 3(ለ) የተመለከተውን ተላልፎ ሕግን በመጣስ ግብር አለመክፈልና አሳሳች መረጃ ማቅረብ ተደራራቢ ወንጀል ፈፅሟል ተብሎ በድርጅቱና በድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ላይ በፌ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ክስ ተመስርቶ እያለ ድርጅቱና የድርጅቱ ስራ አስኪያጅን ከወንጀል ተጠያቂነት ለማዳን በማሰብ 2ኛ ተከሳሽ ክሱ እንዲነሳ ለ1ኛ ተከሳሽ በ7/2/2005 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ የውሳኔ ሀሳብ አቅርቦ 1ኛ ተከሳሽ አፅድቆ ያለምንም ሕጋዊ ምክንያት ክሱን እንዲነሳ በማድረጋቸው፣ ሁለቱም ተከሣሶች በሙሉ ፈቃደቸውና ዕውቀታቸው የወንጀሉ ሙሉ ተካፋይ በመሆን በተሰጣቸው የመንግሥት ኃላፊነት ሊጠብቁትና ሊከላከሉት የሚገባውን የመንግሰትና የሕዝብ ጥቅም በሚጎዳ አኳሃን በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት የመንግስት ስራን በማያመች አኳሃን መምራት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
6ኛ ክስ
በ2ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)፣ 33፣ 411(1) (ሐ) እና 2 ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ ሲሆን፤ ስልጣንና ኃለፊነቱን በመጠቀም የማይገባ ጥቅም ለራሱ ለማግኘት ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት በማሰብ፣
– 2ኛ ተከሣሽ በ26/07/2001 ዓ.ም ጐላጐል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር የተባለ ድርጅት ያለቫት ደረሰኝ ግብይት እንደሚፈፅም ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ጥቆማ ቀርቦ እውነተኛነቱን ለማረጋገጥ የባለሥልጣኑ ሠራተኞች ተልከው እንደጥቆማው አቀራረብ እንደሚፈፅም በወቅቱ በተላኩት ሠራተኞች ከተረጋገጠና ተጠርጣሪዎችም ከተለዩና ምርመራ መዝገቡ ተደራጅቶ እንደሚያስከስስ ከተረጋገጠ በኋላ ተከሣሹ የባለሥልጣኑ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የድርጅቱ ባለቤት አቤቱታ ስላቀረበ ጉዳዩ በድጋሚ መታየት አለበት በሚል ሽፋን ምርመራው እንደገና እንዲጣራ በማድረግ ቀደም ሲል በጉዳዩ ዙርያ ከተሰጠው የምስክርነት ቃል በተለየ ጉዳዩን ሊያዳክም የሚችል አዲስ ተጨማሪ ቃል እንዲቀርብ በማድረግ መዝገቡ ውጤት እንዳይኖረው ካመቻቸ በኋላ ምርመራ መዝገቡ እንዲዘጋ በማስደረጉ፣ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈፀመው የመንግስት ሥራን በማያመች አኳሃን መምራት የሙስና ወንጀል ተከሷል።

7ኛ ክስ
በ2ኛ፣ እና 7ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)፣ 33፣ 411(1) (ሐ) እና 2 ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሣሾች እንደ ቅደም ተከተላቸው በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ እና የአዳማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ ሲሆኑ፤ ስልጣንና ኃለፊነታቸውን በመጠቀም የማይገባ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት በማሰብ፤
– ገላን ታነሪ ኃ/የተ/የግ ማኅበር የተባለው ድርጅት በዲክላራሲዮን ቁጥር E-3248/1 ወደ ውጭ ለመላክ ዲክሌር ያደረገው የቆዳ ብዛት 33‚600.00 (ሰላሳ ሦስት ሺህ ስድስት መቶ) ሆኖ በአዳማ ገቢዎችና ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ11/03/04 ፍተሻ በሚደረግበት ጊዜ ብዛቱ 42‚360 (አርባ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ስልሳ) ሆኖ በመገኘቱ ምክንያት በልዩነት ለተገኘውና ግምቱ ብር 423‚189.94 (አራት መቶ ሃያ ሦስት ሺህ አንድ መቶ ሰማንያ ዘጠኝ ከ94/100) ለሆነው 8‚760 (ስምንት ሺህ ሰባት መቶ ስልሳ) ቀዳ በድርጅቱ እና በድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ አህመድ ኑር ሐሰን ላይ የወንጀል ምርመራ ተጣርቶ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዐቃቤ ሕግ በቁጥር 8-54593/04 በ26/08/2004 የተዘጋጀ ክስ አቅርቦባቸው እያለ፤
7ኛ ተከሳሽ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በነበረው ኃላፊነት ባለሀብቱ ወደ ውጪ ለመላክ ባቀረበው ቆዳ ላይ ፍተሻ በሚደረግበት ወቅት ቆዳ በትርፍነት የተገኘበትና ምርመራም የተጣራበት መሆኑን እያወቀ ባለሀብቱንና ድርጅቱን ከተጠያቂነት ለማዳን አስቀድሞ በቁ.8.0/0/1048 በ12/06/04 ለድርጅቱ በፃፈው ደብዳቤ ጉዳዩን ለዐቃቤ ሕግ እንደማይልክ ከመግለፁም በተጨማሪ በባለሀብቱ ላይ የቀረበው ክስ እንዲነሳ የሚጠይቅ የውሳኔ ሀሳብ በ15/09/04 በተፃፈ ቃለ ጉባኤ ለ2ኛ ተከሳሽ በማቅረቡ፣ 2ኛ ተከሳሽ በበኩሉ ባለሀብቱ የማታለል ድርጊት በመፈፀም ቆዳ በትርፍነት ለመላክ ሲሞክር መያዙን እያወቀ በባለሀብቱ ላይ የተመሰረተው ክስ የሚነሳበት ሕጋዊ ምክንያት በሌለበት ሁኔታ ከባለሀብቱ ጋር በጥቅም በመመሳጠር በባለሀብቱ ላይ የቀረበው ክስ እንዲቋረጥ በ24/09/04 ትዕዛዝ በመስጠት ክሱ እንዲነሳ በማድረጉ፣ ሁለቱም ተከሳሾች ባለሀብቱ በሕግ እንዳይጠየቅና በትርፍነት የተገኘው ቆዳ ላይም እርምጃ እንዳይወሰድ በማድረጋቸው፣ በተሰጣቸው የመንግሠት ኃላፊነት ሊጠብቁትና ሊከላከሉት የሚገባውን የመንግስትና የሕዝብ ጥቅም በሚጎዳ አኳሃን በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት የመንግስት ስራን በማያመች አኳሃን መምራት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
8ኛ ክስ
በ2ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)፣ 33፣ 411(1) (ሐ) እና 2 ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ ሲሆን፤ ስልጣንና ኃላፊነቱን በመጠቀም የማይገባ ጥቅም ለራሱ ለማግኘት ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት በማሰብ፣
– 2ኛ ተከሣሽ አቢ ብርሃኑ የተባለ ግለሰብ ተገቢው ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸውን የሰሌዳ ቁ.ኮድ 3-48863 አ.አ. እና ተላላፊ ሰሌዳ ቁ.545 አ.አ. የሆኑ ሁለት ተሽከርካሪዎች ይዞ በ30/01/2001 ዓ.ም በመገኘቱ ምክንያት ከሌላ ግብረአበሩ ጋር ምርመራ ተጣርቶበት መዝገቡ ለሚመለከተው ዐቃቤ ሕግ ከተላለፈ በኋላ ተከሳሹ ሥልጣኑን በመጠቀም በመዝገቡ ውስጥ 1ኛ ተጠርጣሪ ከሆነው አቢ ብርሃኑ ከተባለው ተጠርጣሪ አባት አቶ ብርሃኑ ብሩ ጋር ባለው የጥቅም ትስስር ጉዳዩ ወደ ፍ/ቤት እንዳይሄድና መኪናውም እንዲለቀቅ ለማድረግ ከተያዙት ሁለት መኪኖች ውስጥ ኮድ 3-48863 አ.አ የሆነው መኪና በአዋጅ ቁ. 60/89 አንቀፅ 74 መሠረት መወረስ እየተገባው ቀረጥና ታክሱ ተከፍሎ እንዲለቀቅ በማድረግ በዚህም መነሻነት የወንጀል መዝገቡ እንዲዘጋ በማድረጉና ለዚህም ውለታው በአሁኑ አጠራር ለገጣፎ ለገዳዲ በቀድሞ ስሙ ወልገወ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ሊቀመንበር በነበረው አቶ ብርሃኑ ብሩ አማካኝነት በአሁኑ ሰዓት ሊገኝ ያልቻለ ሕገ ወጥ የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያ በመስጠትና በዚህም መታወቂያ መነሻነት በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ 500 ካ.ሜ ቦታ በሕገወጥ መንገድ በመውሰዱ፣ በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀመው የመንግስት ሥራን በማያመች አኳሃን መምራት የሙስና ወንጀል ተከሷል።
9ኛ ክስ
በ2ኛ፣ 4ኛ፣ 5ኛ እና 6ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)፣ 33፣ 411(1) (ሐ) እና 2 ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሣሶች እንደ ቅደም ተከተላቸው በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ፣ ምክትል ዋና ዐቃቤ ሕግ፣ በዐቃቤ ቃሊቲ ቅ/ፅ/ቤት የሕግ ማስከበር ኃላፊ እና የድሬ ዳዋ ቅ/ፅ/ቤት የጣቢያ አስተባባሪ ሲሆኑ፤ ስልጣንና ኃለፊነታቸውን በመጠቀም የማይገባ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት በማሰብ፣
6ኛ ተከሳሽ በ8/8/2002 ዓ.ም በባለሥልጣኑ አዋሽ መቅረጫ ጣቢያ ማንነቷ ለጊዜው ካልታወቀች ግለሰብ ላይ በፍተሻ ከተያዙ ኮንትሮባንድ ካሜራዎች ውስጥ ሦሰት ሶኒ ጂጅታል ካሜራዎችን ወስዶ ለግል ጥቅሙ ማዋሉ ታውቆ ምርመራ መጣራት ሲጀመርበት፡-
– 5ኛ ተከሣሽ የባለስልጣኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዐቃቤ ሕግ የሆኑትን አቶ ምንይችል ተኮላ ጋር ስልክ ደውሎ “6ኛ ተከሳሽ ለምን ታሰረ? እንዲፈታ!” ብሎ በቃል ትዕዛዝ ከማስተላለፉም በላይ በአካል ከሥፍራው ድረስ በመሄድ ምርመራው እንዳይጣራ ለፍ/ቤት በቃል አመልክቶ እንዲፈታ በማስደረጉ፣
– 4ኛ ተከሣሽ ምርመራ እንዲጣራ ትዕዛዝ ሰጥተው ለነበሩት ዐቃቤ ሕግ አቶ አምደሚካኤል ጌታቸው የስልክ ትዕዛዝ በመስጠት በ6ኛ ተከሣሽ ላይ ምርመራ እንዳይጀመር በማድረጉ፣
– 2ኛ ተከሳሽ 6ኛ ተከሣሽ በተጠረጠረበት ብልሹ አሰራርና የሙስና ወንጀል በባለሥልጣኑ ደንብ ቁጥር 155/2000 አንቀጽ 37/1/ መሠረት የዲሲፒሊን እርምጃ እንድወሰድና ለሕግም እንዲቀርብ ማስደረግ ሲገባው በስራው ላይ እንዲቆይና በሕግም እንዳይጠየቅ በማድረጉ፤
– 6ኛ ተከሳሽ በዚህ ጉዳይ ታስሮ ምርመራው የተጀመረበት ቢሆንም ከ2ኛ፣ 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች ጋር ባለው የጥቅም ትስስር ምክንያት የነሱን ሽፋን ተጠቅሞ ምርመራው እንዲቋረጥለት በማስደረግ ሕገወጥ ተጠቃሚ በመሆኑ፣
በአጠቃላይ ሁሉም ተከሣሾች በሙሉ ፈቃዳቸውና ዕውቀታቸው የወንጀሉ ሙሉ ተካፋይ በመሆን በተሰጣቸው የመንግሥት ኃላፊነት ሊጠብቁትና ሊከላከሉት የሚገባውን የመንግስትና የህዝብ ጥቅም በሚጎዳ አኳሃን በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈፀሙት የመንግስት ስራን በማያመች አኳሃን መምራት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
10ኛ ክስ
በ6ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 413/1/ሀ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሣሹ በኢት/ገ/ጉ/ባለሥልጣን የአዋሽ መቅረጫ ጣቢያ አስተባባሪ ሆኖ ሲሰራ የማይገባ ቁሳዊ ጥቅም ለራሱ ለማግኘትና ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት አስቦ በ8/8/2002 ዓ.ም ስሟ ለጊዜው ያልታወቀች ኮንትሮባንዲስት ከጅጅጋ ወደ አዲስ አበባ በሚጓዝ ተሽከርካሪ ተሳፍራ ስትመጣ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን አዋሽ መቅረጫ ጣቢያ ላይ በተደረገባት ፍተሻ ሦስት ሶኒ ዲጅታል ካሜራ ተይዞባት በደረሰኝ ቁጥር 849781 ተመዝግቦ የነበረውን ደረሰኝ እንዲሰረዝ (void እንዲሆን) በማድረግና በማስደረግ ወስዶ ለግል ጥቅሙ በማዋሉ በፈፀመው በሥራ ተግባር ላይ የሚፈፀም የመውሰድና የመሰወር የሙስና ወንጀል ተከሷል።

11ኛ ክስ
በ6ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 408(1) ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት የላጋር መቅረጫ ጣቢያ አስተባባሪ ሆኖ ሲሰራ በኃላፊነቱ እና በሥራ ግዴታው ማድረግ የማይገባውን በማድረግ ሕገወጥ ጥቅም ለማግኘት አስቦ፤
– ቀኑ በውለ ተለይቶ ባልታወቀበት ጥር ወር 2005 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ ድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 03 ፖሊስ መምሪያ አካባቢ ወደ ኮንደሚኒየም በሚወስደው መንገድ ላይ ኤምዲ (MD Transit) የተባለ ድርጅት አስተላላፊ ሥራ አስኪያጅ ከሆኑት አቶ ታደሰ ገ/ዮሐንስ ላይ ከጅቡቲ ተጓጉዞ ድሬዳዋ ጉምሩክ የገባ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች በሠነድ ከተዘረዘሩት በላይ (ትርፍ) በመገኘቱ ዕቃው በመያዙ ዕቃውን ለመልቀቅ ብር 10‚000 (አሥር ሺ ብር) ተቀብሎ በመውሰዱ፤
– ቀኖቹ በውል ተለይተው ባለታወቁበት በሚያዝያ ወር 2005 ዓ.ም በተለያዩ ሁለት ቀናት ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ሲሆን፤ በድሬዳዋ ከተማ 03 ቀበሌ ማርያም ሰፈር ዲፖ አካባቢ የንግድ ረዳት ሆነው ይሰሩ ከነበሩት አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው ከጅቡቲ ተጓጉዘው ድሬዳዋ ጉምሩክ የገቡ አምፖሎች ተፈትሸው ከተጠናቀቁ በኋላ ተከሳሹ ገንዘብ ካልሰጠኸኝ እቃዎቹ አይወጡም ብሎ በመደራደር ለመጀመሪያዎቹ ብር 15‚000 (አስራ አምስት ሺህ)፣ ለሁለተኛዎቹ ብር 20‚000 (ሃያ ሺህ) በድምሩ ብር 35‚000 (ሰላሳ አምስት ሺህ ብር) ተቀብሎ በመውሰዱ፤ በፈፀመው ጉቦ መቀበል የሙስና ወንጀል ተከሷል።

12ኛ ክስ
በ2ኛ፣ 4ኛ እና 9ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)(ለ)፣ 33፣ እና 408(1) እና (2) ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር
2ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች እንደቅደም ተከተላቸው በኢትዮጰያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ እና ምክትል ዋና ዐቃቤ ሕግ ሆነው ሲሰሩ፣ በስራ ኃላፊነታቸው ማድረግ የማይገባቸውን በማድረግ ሕገወጥ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ፣ 9ኛ ተከሳሽ በበኩሉ የመንግስት ሰራተኞች ብቻ በሚፈፀም የሙስና ወንጀል ልዩ አካፋይ በመሆን፤
– 2ኛ ተከሣሽ ብሥራት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር የተባለ ድርጅት ያለ ቫት ደረሰኝ ግብይት ሲፈፅም ተከሣሹ ለሚሰራበት መ/ቤት ጥቆማ ቀርቦ እንደ ጥቆማው አቀራረብ ለማረጋገጥ የድርጅቱ ሠራተኞች መጋቢት 29 ቀን 2001 ዓ.ም ወደ ድርጅቱ በመሄድ ኦፕሬሽን ሲካሄድ ያለደረሰኝ ግብይት እያከናወነ መሆኑ በመረጋገጡ በድርጅቱ፤ በድርጅቱ ባለቤትና ሌሎች ሁለት የድርጅቱ ሠራተኞች ላይ ምርመራ ተጣርቶ ክስ ቀርቦባቸው በክርክር ላይ እያለ ተከሣሹ ለብሥራት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ባለቤት አቶ ባህሩ አብርሃ በቀጥታ መስመር ስልካቸው ላይ በመደወል “አንተ ከማን ትበልጣለህ ወደ መደበኛ ፍ/ቤት ክስህን አቅርበን ከፍተኛውን ቅጣት አንደምናስቀጣህ እወቅ” በማለት ግለሰቡን በማስፈራራትና በማስጨነቅ በተከሳሹ የቅርብ አገናኝ በነበረው 9ኛ ተከሳሽ አማካኝነት ቀጠሮ በማስያዝ ከላይ የተጠቀሰውን ባለሀብት ቢሮው በተደጋጋሚ እንዲገኝ በማድረግ ከላይ በተጠቀሰው የማስፈራሪያ ቃል በማስፈራራት “ሌሎች ልጆች ከእኔ ጋር ስላሉ በደንብ ተዘጋጅተህ ና” በማለት የራሱን ስልክ ቁጥር በመስጠት የስልክ ግንኙነት በማድረግ ቀኑና ወሩን በትክክል በማይታወቅበት 2004 ዓ.ም መጀመሪያ አካባቢ ዮርዳኖስ ሆቴል አካባቢ ከምሽቱ 1፡45 ሰዓት በመቅጠር ብር 250‚000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ከባለሀብቱ ከተቀበለ በኋላ ባሀብቱ አድርጐት የነበረውን ብራስሌት እጁ ላይ ከተመለከተ በኋላ “የእሱ ዓይነት ግዛልኝ” በማለት ግለሰቡ በብር 30‚000 (ሠላሳ ሺህ ብር) የተገዛ ብራስሌት በማግስቱ ኢንተርኮንቴኔታል ሆቴል አካባቢ ድረስ ይዞ በመሄድ ከምሽቱ 1፡30 ሰዓት አካባቢ ተከሳሹ በእራሱ መኪና ውስጥ ሆኖ ተቀብሎ ጉዳዩ እንዲጨርስለት ለ4ኛ ተከሣሽ ነግሮ ጉዳዩ እንዲያልቅ በማድረጉ፤
– 4ኛ ተከሣሽ በበኩሉ ቀኑና ወሩን በውል በማይታወቅበት በ2004 ዓ.ም መጀመሪያ አካባቢ ፒያሣ ግራር ሆቴል እየተባለ ከሚጠራ ሆቴል ውስጥ በግምት ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት አካባቢ ከላይ ከተጠቀሰው ድርጅት ባለቤት (አቶ ባህሩ አብርሃ) ብር 50‚000 (ሃምሳ ሺህ ብር)፤ ከላይ በተጠቀሰው ቀኑና ወሩ በውል በማይታወቅበት ጊዜ ባለሀብቱን እቤቱ ድረስ በመጥራት ብር 30‚000 (ሠላሳ ሺህ ብር) እና ብር 20‚000 (ሃያ ሺህ ብር) በአጠቃላይ ብር 100‚000 (መቶ ሺህ ብር) በመቀበሉ እና ከባለሀብቱ ከላይ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ተቀብሎ በባለሀብቱ ላይ የተመሠረተውን ክስ በፍ/ቤት በነፃ ከተሰናበተ በኋላ ይግባኝ እንይጠየቅ በማድረጉ፤
– 9ኛ ተከሣሽ በበኩሉ ቀኑና ወሩ በማይታወቅ በ2004 ዓ.ም ባህሩ አብርሃ የተባሉ የብሥራት ኃ/የተ/ማኅበር ባለቤት በገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የተመሰረተባቸውን ክስ እንዲዘጋ ከ2ኛ ተከሣሽ ጋር በማገናኘት ብር 250‚000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) እና ብር 30‚000 (ሠላሳ ሺህ ብር) የሚያወጣ ብራስሌት 2ኛ ተከሣሽ በሕገ ወጥ መንገድ እንዲያገኝ በማድረጉ፤
በአጠቃላይ ተከሣሾች በመላ ሀሳባቸውና አድራጐታቸው በወንጀሉ ድርጊትና በሚሰጠው ውጤት ሙሉ ተከፋይ በመሆን በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት ጉቦ መቀበል የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
13ኛ ክስ
በ2ኛ፣ እና 13ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 419(1) (ሀ) እና ለ ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣

የወንጀሉ ዝርዝር
2ኛ ተከሳሽ በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከ1978 ዓ.ም ጀምሮ እጁ እስከተያዘበት 2005 ዓ.ም ተቀጥሮና ተሹሞ ሲሰራ ከብር 247 (ሁለት መቶ አርባ ሰባት) እስከ ብር 5‚700 (አምስት ሺህ ሰባት መቶ) ያልተጣራ ወርሃዊ ደመወዝ ይከፈለው እንደነበረ እና 13ኛ ተከሣሽ ደግሞ በአገር መከላከያ ሚኒስቴር ከ01/11/1989 ዓ.ም እስከ 30/01/2000 ዓ.ም ተቀጥራ ስትሰራ ከብር 790 (ሰባት መቶ ዘጠና ብር) እስከ ብር 2‚145 (ሁለት ሺህ አንድ መቶ አርባ አምስት) ያልተጣራ ወርሃዊ ደመወዝ ይከፈላት የነበረ ሲሆን ተከሳሾቹ ያገኙት ከነበረው ደመወዝና ገቢ ጋር የማይመጣጠን፤
1ኛ. በወጋገን ባንክ ካዛንቺስ አካባቢ በሂሣብ ቁጥር 302993 ብር 96‚477.79 (ዘጠና ስድስት ሺ አራት መቶ ሰባ ሰባት ከሰባ ዘጠኝ ሣንቲም) በ13ኛ ተከሳሽ ስም
2ኛ. በእናት ባንክ እቴጌ ጣይቱ አብይ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር R/S746 ብር 4‚000 (አራት ሺህ) በ13ኛ ተከሳሽ ስም፤
3ኛ. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፊንፊኔ ቅርንጫፍ በሂሣብ ቁጥር 1000001730766 ብር 1‚427.59 (አንድ ሺ አራት መቶ ሃያ ሰባት ከሃምሳ ዘጠኝ ሳንቲም) በ13ኛ ተከሳሽ ስም፤
4ኛ. በኢትዮጰያ ልማት ባንክ በሂሣብ ቁጥር 1258hA, 40612HC, 35933HD, 41304HE, 2636HG, ብር 3‚925 (ሦስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ አምስት) በ13ኛ ተከሳሽ ስም፤
5ኛ. የካ ክ/ከተማ ቀበሌ 11/12 የቤ.ቁ. 634 የካርታ ቁጥር 29870 የቦታው ስፋት 4‚000 ካ.ሜ የሆነ ቦታ ተከሣሽን ጨምሮ 7 ሰዎች በብር 4‚200‚000 (አራት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ ብር) የተገዛ ቦታ (የተከሳሽ ድርሻ ብር 600‚000 (ስድስት መቶ ሺህ ብር)፤
6ኛ. የሠሌዳ ቁጥር 3-02725 ትግ የሆነ አውቶቡስ ተሽከርካሪ (ለጊዜው ግምቱ ያልታወቀ) በ13ኛ ተከሳሽ ስም፤
7ኛ. የሠሌዳ ቁጥር 3-49614 አ.አ የሆነ የንግድ መኪና (ለጊዜው ግምቱ ያልታወቀ) በ13ኛ ተከሳሽ ስም፤
8ኛ. የካረታ ቁጥር 2713/22/93 መቀሌ ከተማ ቀበሌ 11 የሚገኝ መኖሪያ ቤት በ13ኛ ተከሳሽ ስም፤
9ኛ. በ2ኛ ተከሳሽ ስም ዳሸን ባንክ መቀሌ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር 5013022467001 ብር 42244.62፣
10ኛ. በ2ኛ ተከሳሽ ስም አንበሳ ባንክ የካ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር 00300000799-97 ብር 387.65
11ኛ. በ2ኛ ተከሳሽ ስም ወጋገን ባንክ መስቀል ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር 23444/501/03024 ብር 102‚553.50 (አንድ መቶ ሁለት ሺ አምስት መቶ ሃምሳ ሦስት ከ50/100)
12ኛ. በፀረ ብርሃን ገ/ዋህድ ስም (ልጅ) ካሳንቺስ ቅርንጫፈ በሂሳብ ቁጥር 262179 ብር 18‚142.04፣
13ኛ. በፀረ ብርሃን ገ/ዋህድ ስም (ልጅ) ካሳንቺስ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር 262180 ብር 1‚015.07፣
14ኛ. በፀረ ብርሃን ገ/ዋህድ ስም (ልጅ) በኢትዮጰያ ንግድ ባንክ ሀዋሳ ቅርንጫፈ በሂሳብ ቁጥር 1000013401587 ብር 1‚753.77፣
15ኛ. በፀረ ብርሃን ገ/ዋህድ ስም (ልጅ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፊንፊኔ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር 0173007267000 ብር 203424.99 (ሁለት መቶ ሦስት ሺ አራት መቶ ሃያ አራት ከ99/100)፤
16ኛ. በ2ኛ ተከሳሽ ስም በአንበሳ ባንክ የብር 34‚275.25 (ሰላሳ አራት ሺ ሁለት መቶ ሰባ አምስት ከ25/100) አክስዮን፤
17ኛ. በሳሙኤል ገ/ዋህድስም (ልጅ) የብር 10‚000 (አሰር ሺ) አክስዮን፤
18ኛ. ከተከሳሾች መኖሪያ ቤት የተገኘ፡-
18.1. የኢትዮጵያ ብር 200‚000 (ሁለት መቶ ሺ)
18.2. EURO 19435 (አስራ ዘጠኝ ሺ አራት መቶ ሰላሳ አምስት)
18.3. USD 26300(ሃያ ስድስት ሺ ሶስት መቶ)
18.4. POUND 560 (አምስት መቶ ስድሳ)
18.5. TAILAND 210 (ሁለት መቶ አስር)
19ኛ/ በካርታ ቁጥር L/X/L/D/3139100 ግምቱ ብር 596868፣24 የሆነ 500 ካ.ሜ
20ኛ/ 6 የተለያዩ ላፕቶፖች፤
በአጠቃላይ ተከሳሾች የኑሮ ደረጃቸው አሁን ባለበትም ሆነ አስቀድሞ በነበሩት የመንግሥት ሥራ ከሚያገኙት ህጋዊ ገቢ ጋር የማይመጣጠን ብር 1,451,941.609 (አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ሃምሳ አንድ ሺ ዘጠኝ መቶ አርባ አንድ ከ60/00)፣ ከላይ ከተራ ቁጥር 18.2 – 18.5 ድረስ የተጠቀሱትን የውጭ አገር ገንዘቦችና እና እንዲሁም የተለያዩ ንብረቶች ይዘው በመገኘታቸው በፈፀሙት ምንጩ ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ ይዞ መገኘት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
14ኛ ክስ
በ2ኛ እና 13ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)፣ 684(1) እና (2) ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሾች ከላይ በ13ኛው ክስ በተገለፀው ጊዜና አኳኋን በፈፀሙት የሙስና ወንጀል ያገኙትን ገንዘብና ንብረት ህገወጥ አመጣጡን በመሰወር ህጋዊ ለማድረግ በማሰብ መሬት እና መኪና በመግዛት፣ በተለያዩ ባንኮች በእራሳቸውና በልጆቻቸው ስም እንዲሁም መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ገንዘቦችን በማስቀመጥ በፈፀሙት በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብና ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብና በወንጀሉ መርዳት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
15ኛ ክስ
በ13ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 40፣419 እና 684 ላይ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች በመተላለፏ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሿ ባለቤቷ የሆነው 2ኛ ተከሳሽ ግንቦት 2 ቀን 2005 ዓ.ም በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ ተጠርጣሪው የተጠረጠረበትን የወንጀል ፍሬ መሆናቸውን እያወቀች ባለቤቷ በፈፀመው የወንጀል ድርጊት ከመከሰስና ከመቀጣት እንዲያመልጥ ለመርዳት፡-
1. በአቶ ገ/ዋህድ ወ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል ስም ተመዘገበ የባንክ ደብተር ቁጥር 0123586 የሆነ ብር 10000 (አስር ሺ) ተቀማጭ ያለው፤
2. ካርታ ቁጥር L/X/L/D/3139/00/06/01 ከለገጣፎ ለገዳዲ አስተዳደር ለገ/ዋህድ ወ/ጊዮርጊስ የተሰጠ፤
3. በአቶ ገ/ዋህድ ወ/ጊዮርጊስ እና በወ/ሮ ሀይማኖት ተስፋዬ ስም ለኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ብር 820,000 (ስምንት መቶ ሃያ ሺ ብር) ብድር ለመጠየቅ የተሞላ ቅፅ፤
4. በአቶ ገ/ዋህድ ወ/ጊዮርጊስ እና በኮ/ል ሃይማኖት ተስፋዬ ስም ለኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ብር 1,000,000 (አንድ ሚሊዮን ብር) የባንክ ሼር ለመግዛት የጠየቁበት ሰነድና የተለያዩ የቤት ፕላኖችን ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ እህቷ ለሆነችው ወ/ሮ ንግስቲ ተስፋ ገ/ስላስ እና አቶ ሀብቶም ገ/መድህን ገ/የስ ለተባሉ ግለሰቦች አሳልፋ በመስጠትዋ በፈፀመችው ወንጀል ከተፈፀመ በኋላ ወንጀል አድራጊውን መርዳት ወንጀል ተከሳለች።
16ኛ ክስ
በ2ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን ኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀፅ 808(ሀ) ላይ የተደነገገውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ የጦር መሳሪያ አያያዝና አጠቃቀም ደንብ ተከትሎ ፈቃድ ከሚሰጥ አካል አስፈቅዶ መያዝና መጠቀም ሲገባው ከሚመለከተው ፈቃድ ሰጪ አካል ሳያስፈቅድ የመኖሪያ ቤቱ በ02/09/05 ዓ.ም በፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ብርበራ በተካሄደበት ወቅት፡-
1. የውግ ቁጥር 1529 የሆነ ባለ አንድ እግር ታጣፊ ክላሽ፣
2. የውግ ቁጥር 0624 የሆነ ባለ አንድ እግር ታጣፊ ክላሽ፣
3. የውግ ቁጥር ሠበ0402 የሆነ ማክሮቭ ሽጉጥ
4. የውግ ቁጥር የሌለው ማካሮቭ ሽጉጥ፣
5. የውግ ቁጥር የሌለው ኮልት ሽጉጥ፣
6. የውግ ቁጥር 47391 ኮልት ሽጉጥ፣
7. የውግ ቁጥር NK252926 ማካሮቭ ሽጉጥ፣
8. የውግ ቁጥር የሌለው ማካሮቭ ሽጉጥ
9. የውግ ቁጥር 2235 ስታር ሽጉጥ እና
10. የተለያዩ ጥይቶችን ይዞ በመገኘቱ
በፈፀመው እንዲይዝ ያልተፈቀደለትና ፈቃድ የሌለው የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት ወንጀል ተከሷል።
17ኛ ክስ
በ8ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀፅ 419(1)(ለ) ላይ የተደነገገውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የመንግስት ሰራተኛ ሆኖ በሰራበት ከ22/11/87 ዓ.ም እስከ 30/7/2004 ዓ.ም ድረስ ባሉት ጊዜያት ተቀጥሮ ሲሰራ በወር ይከፈለው የነበረው ያልተጣራ ደሞዝ ከብር 445 (አራትመቶ አርባ አምስት) እስከ ብር 8,651 (ስምንት ሺ ስድስትመቶ ሃምሳ አንድ ሺህ) ሲሆን በመንግስት ስራ ላይ እያለ ያገኝ ከነበረው ከህጋዊ ገቢው ጋር የማይመጣጠን፡-
1ኛ/ ግንቦት 2 ቀን 2005 ዓ.ም በመኖሪያ ቤቱ ብርበራ ተደርጎ የተገኘ ብር 1,947,676.10 /አንድ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አርባ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ሰባ ስድስት ብር ከአስር ሳንቲም/፣
2ኛ/ በተለያዩ ባንኮች እና የአክሲዮን ማህበራት በተከሳሽ ስም የተቀመጠ በድምሩ ብር 2,090,880.03 /ሁለት ሚሊዮን ዘጠኛ ሺ ስምንተ መቶ ሰማንያ ብር ከአስር ሳንቲም/
3ኛ/ በተከሳሽ ስም ቦንድ የተገዛበት ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/
4ኛ/ በአዲስ አበባ ልደታ ክ/ከተማ ፣ ወረዳ 24፣ ቀበሌ 02/03 በተከሳሽ ደሞዝ በምትተዳደረው ባለቤቱ ወ/ሮ ሀዲስ ሙሉ ስም ተመዘግቦ የሚገኝ 74.56 ካ/ሜ ስፋት ላይ የተሰራና ግምቱ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ የሆነ ባለ ሁለት መኝታ ኮንደምኒየም ቤት፣
5ኛ/ በተከሳሽ ደሞዝ በምትተዳደረው ባለቤቱ ወ/ሮ ሀዲስ ሙሉ ስም በተለያዩ ባንኮች የተቀመጠ በድምሩ ብር 185,641.19 (አንድ መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ስድስት መቶ አርባ አንድ ብር ከአስራ ዘጠኝ ሳንቲም/
6ኛ/ በተከሳሽ ደሞዝ በምትተዳደረው ባለቤቱ ወ/ሮ ሀዲስ ሙሉ ስም አክሲዮን የተገዛበት ብር 5,000፣ አምስት ሺህብር/፣
7ኛ/ በተከሳሽ ደሞዝ በምትተዳደረው ባለቤቱ ወ/ሮ ሀዲስ ሙሉ ስም ቦንድ የተገዛበት ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/፣
በአጠቃላይ ተከሳሹ በስሙና በባለቤቱ ስም ብር 4,459,197.5 /አራት ሚሊዮን አራት መቶ ሀምሳ ዘጠኝ ሺህ አንድ መቶ ዘጠና ሰባት ብር ከሃምሳ ሳንቲም/ የሆነ ከፍተኛ ንብረትና ገንዘብ በመያዝ የኑሮ ደረጃው የማይፈቅድለትን ሀብት አከማችቶ በመገኘቱ በፈፀመው ምንጩ ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ ይዞ መገኘት የሙስና ወንጀል ተከሷል።
18ኛ ክስ
በ8ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 684(1) ላይ የተደነገገውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ17ኛው ክስ በተጠቀሰው ጊዜና አኳኋን በፈፀመው በሙስና ወንጀል ያገኘውን ገንዘብና ንብረት ህገወጥ አመጣጡን በመሰወር ህጋዊ ለማድረግ በማሰብ፣
1ኛ/ በመኖሪያ ቤቱ ብርበራ ተደርጎ የተገኘ ብር ብር 1,947,676.10/ አንድ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አርባ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ሰባ ስድስት ብር ከአስር ሳንቲም/
2ኛ/ በተለያዩ ባንኮች እና የአክሲዮን ማህበራት በተከሳሽ ስም የተቀመጠ በድምሩ ብር 2,090,880.03 /ሁለት ሚሊዮን ዘጠና ሺህ ስምንተ መቶ ሰማንያ ብር ከአስር ሳንቲም/
3ኛ/ በተከሳሽ ስም ቦንድ የተገዛበት ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/፣
4ኛ/ በአዲስ አበባ ልደታ ክ/ከተማ ፣ ወረዳ 24፣ ቀበሌ 02/03 በተከሳሽ ደሞዝ በምትተዳደረው ባለቤቱ ወ/ሮ ሀዲስ ሙሉ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ 74.56 ካ/ሜትር ስፋት ላይ የተሰራና ግምቱ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ የሆነ ባለ ሁለት መኝታ ኮንዶሚኒየም ቤት፣
5ኛ/ በተከሳሽ ደሞዝ በምትተዳደረው ባለቤቱ ወ/ሮ ሀዲስ ሙሉ ስም በተለያዩ ባንኮች የተቀመጠ በድምሩ ብር 185,641.19 /አንድ መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ስድስት መቶ አርበ አንድ ብር ከአስራ ዘጠኝ ሳንቲም/
6ኛ/ በተከሳሽ ደሞዝ በምትተዳደረው ባለቤቱ ወ/ሮ ሀዲስ ሙሉ ስም አክሲዮን የተገዛበት ብር 5,000 /አምስት ሺህ ብር/
7ኛ/ በተከሳሽ ደሞዝ በምትተዳደረው ባለቤቱ ወ/ሮ ሀዲስ ሙሉ ስም ቦንድ የተገዛበት ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ህጋዊ አስመስሎ ይዞ በመገኘቱ በፈፀመው በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ በማቅረብ የሙስና ወንጀል ተከሷል።
19ኛ ክስ
በ8ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ2002 ዓ.ም በስራ ላይ የዋለውን ሀብትን ለማሳወቅና ለማስመዝገብ የወጣ አዋጅ ቁጥር 668/2002 አንቀጽ 22/1/ሀ/ ላይ የተደነገገውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ17ኛ ክስ በተጠቀሰው ስራ ኃላፊነት ተመድቦ ሲሰራ በራሱና በባለቤቱ ስም የሚገኘውን ሀብት የማስመዝገብ ግዴታ እያለበት በ17/08/03 ዓ.ም ለፌዴራል የስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ሀብትማሳወቂያና ማስመዝገቢያ ዳይሬክቶሬት ሲያስመዘግብ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ በ02/09/05 ዓ.ም በተደረገ ብርበር የተገኘውን ብር 1,947,676.10 /አንድ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አርባ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ሰባ ስድስት ብር ከአስር ሳንቲም/ ሳያስመዘግብ፣ በስሙና በባለቤቱ ስም በተለያዩ ባንኮች እና የአክስዮን ማህበራት ያስቀመጠውን የገንዘብ መጠን ቀንሶ በማስመዝገብ እና ደብቆ ይዞ የተገኘበት በመሆኑ ማሳወቅ የሚገባውን ሀብት ባለማሳወቅና ባለማስመዝገብ ወንጀል ተከሷል።
20ኛ ክስ
በ4ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኤ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 419/1/ሀ/እና /ለ/ ላይ የተደነገገውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከ1/5/87 ዓ.ም ጀምሮ እጁ እስከተያዘበት እስከ ግንቦት 3 ቀን 2005 ዓ.ም ተቀጥሮ ሲሰራ ከብር 2535 (ሁለት ሺ አምስት መቶ ሰላሳ አምስት ብር) እስከ ብር 10234 (አስር ሺህ ሁለትመቶ ሰላሳ አራት ብር) ያልተጣራ ወርሃዊ ደመወዝ ይከፈለው የነበረ ሲሆን ተከሳሹ ያገኘው ህጋዊ ገቢው ጋር የማይመጣጠን ፣
1ኛ/ በ30/09/2005 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት በተደረገ ብርበር በኤግዚቢትነት ተመዝግቦ የሚገኝ ጥሬ ብር 1,388,899 (አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰማኒያ ስምንት ሺህ ስምንት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ብር)
2ኛ/ እ.ኤ.አ ከ4/8/2012 እስከ 19/06/2013 ባለው ጊዜ የቤት እመቤት በሆነችው ባለቤቱ ወ/ሮ ካሰች አምደመስቀል መገርሳ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጦር ኃይሎች ቅርንጫፍ የሚገኝ ብር 907,633.62 (ዘጠኝ መቶ ሰባት ሺ ስድስት መቶ ሰላሳ ሶስት ብር ከ62 /100 ሳንቲም)
3ኛ/ ከ2002 ዓ.ም እስከ 2005 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ በተለያየ ጊዜ የተለያየ ገንዘብ መጠን ይዞ እየተመላለሰ “ውጭ ሀገር የሚገኙ ጓደኞቼ የላኩልኝ ገንዘብ ነው አንቺ ጋር ይቀመጥልኝ” በማለት በሀሳዋ ከተማ አላሙራ ክ/ከተማ ጉዮ ቀበሌ ነዋሪ ከሆነችው እህቱ ወ/ት ትእግስት አለማየሁ ድረስ በመሄድ በድምሩ ብር 1,900,000.00 (አንድ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሺህ ብር) እሷ በከፈተችው አካውንት እንዲቀመጥ በማድረጉ፤
4ኛ/ በተለያዬ ወቅት ለእህቱ ትእግስት አለማየሁ ገንዘብ በመስጠት በአዋሳ ከተማ አላሙራ ክ/ከተማ በተለምዶ ዲያስፖራ መንደር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ግምቱ ብር 1,425,000 (አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ሃያ አምስት ሺ) የሚያወጣ መኖሪያ ቤት በስሟ በማሰራቱ፣
5ኛ/ በሃሳዋ ከተማ መናኸሪያ ክ/ከተማ የቦታ መለያ ቁጥር APR-95 59 የፋይል ቁጥር 1595/1737 የቦታው ስፋት 275 ካ.ሜ በሆነው ቦታ የገቢ ምንጩ ሊያሰራው የማይችለውን ቤት ሰርቶ ሚያዝያ 15 ቀን 2005 ዓ.ም በተፃፈ የቤት ሽያጭ ብር 930,000.00 (ዘጠኝ መቶ ሰላሳ ሺ ብር) በማስተላለፉ፣
በአጠቃላይ ተከሳሹ ከሚያገኘው የደመወዝ ገቢ ጋር የማይመጣጠን በድምሩ ብር 6,551,532.62 (ስድስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሃምሳ አንድ ሺህ አምስትመቶ ሰላሳ ሁለት ብር ከስድሳ ሁለት ሳንቲም) ገንዘብ አካብቶ በመገኘቱ በፈፀመው ምንጩ ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ አካብቶ መገኘት የሙስና ወንጀል ተከሷል።
21ኛ ክስ
በ4ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 684(1) ላይ የተደነገገውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ20ኛው ክስ የተገለፀውን በሙስና ያገኘውን ንብረትና ገንዘብ የወንጀል ፍሬ መሆኑን እያወቀ ምንጩን ለመደበቅ ወይም ለመሸፈን እና የንብረቱን ሕገወጥ አመጣጥ በመሰወር ህጋዊ ለማድረግ አስቦ፣ በራሱ ስም ቤት ሰርቶ በውክልና ስም በእጅ አዙር በማሸጥ፣ በእህቱ ትእግስት አለማየሁ ስም ቤት በማሰራት እና ገንዘብ በማስቀመጥ ፣ በባለቤቱ ስም በተከፈተ አካውንት ገንዘቡ እንዲቀመጥ በማድረግ እንዲሁም፣ በሚስጥር ገንዘቡን ወደ ወላይታ ሶዶ ዞን ሶዶ ወረዳ ላሾ ቀበሌ ከሚገኘው ወንድሙ አቶ ብርሃኑ አለማየሁ ዘንድ መኖሪያ ቤታቸው በመላክ መሬት ውስጥ እንዲቀበር በማድረጉ በፈፀመው በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብና ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ የሙስና ወንጀል ተከሷል።
22ኛ ክስ
በ4ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 407/1/ሀ/እና /ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዐቃቤ ህግ ሲሆን የማይገባ ጥቅም ለራሱ ለማግኘትና ለሌሎች ሰዎችም ለማስገኘት በማሰብ ሂልቦቶም የመዝናኛ ማዕከል ኃ/የተ/የግ/ማህበር በሐምሌ እና ነሀሴ 2001 ዓ.ም የሚፈለግበትን የተርን ኦቨር ታክስ እንደከፈለ በማስመሰል ቁጥራቸው 1398705002 የሆኑ ሁለት ተመሳሳይ ቁጥር ያላቸው ሀሰተኛ የተርን ኦቨር ታክስ መሰብሰቢያ ደረሰኞች በጥቅምት ወር 2003 ዓ.ም ለኢት/ገ/ጉ/ባለሥልጣን ምሥራቅ ቅ/ጽ/ቤት በማቅረቡ በፈፀመው ሀሰተኛ ወይም አሳሳች መረጃ ማቅረብ ወንጀል በድርጅቱ፣ በድርጅቱ ስራ አስኪያጅ እና በፋይናንስ አስተዳደር ሠራተኞች ላይ በፌ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ክስ ተመስርቶ እለ ያለምንም ህጋዊ ምክንያት ተከሳሾቹ ከህግ ተጠያቂነት እንዲያመልጡ እርምጃም እንዳይወሰድባቸው ለማድረግ በቁጥር 5.2.2/2412/80 በ24/8/2004 ዓ.ም በፍ/ቤቱ በፃፈው ማመልከቻ ክሱ አለአግባብ እንዲነሳ በማድረጉ በፈፀመው በሥልጣን አላግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል ተከሷል።
23ኛ ክስ
በ10ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የገንዘብና የባንክ አዋጅ ቁጥር 83/1986 አንቀጽ 59(1) (ሸ) ስር የተደነገገውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ አሜሪካ አገር ከምትኖረው ትእግስት ከተማ ከበደ ከተባለች ልጁ ውክልና በመውሰድ ጌታነህ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሥራ አስኪያጅ ለሆኑት አቶ ዮሐንስ ጌታነህ ካሳ ጥቅምት 1 ቀን 1998 ዓ.ም በተፃፈ የብድር ውል ስምምነት ብር 40,000,000 (አርባ ሚሊዮን ብር) ብድር በመስጠት ለባንኮችና መሰል የፋይናንስ ተቋማት ብቻ የተፈቀደውን የባንክ ስራ በህገወጥ መንገድ እንደ ንግድ ስራ ሲሰራ በመገኘቱ በፈፀመው ወንጀል ተከሷል።
24ኛ ክስ
በ10ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 715(ሀ) እና (ሐ) ላይ የተደነገገውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ አቶ ዮሀንስ ጌታነህ ካሳ የተባሉ የግል ተበዳይን የገንዘብ ችግር መሰረት በማድረግ ከንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አክስዮን ማህበር ጣና ቅርንጫፍ እና ከአቢሲኒያ ባንክ ነጋድራስ ቅርንጫፍ ከ1998 እስከ 2001 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ከግል ተበዳይ ድርጅት በተለያዩ ቀናት በተፃፉ የተለያ ቼኮች በልጁ ትእግስት ከተማ ከበደ፣ በእራሱ በተከሳሹ እና ኬኬ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በተባለ በእራሱ ድርጅት በህግ ከተፈቀደው ወለድ በላይ ብር 111,705,397.83 (አንድ መቶ አስራ አንድሚሊዮን ሰባት መቶ አምስት ሺህ ሶስት መቶ ዘጠና ሰባት ብር 83/100 ሳንቲም) አራጣ በማስከፈል በግል ተበዳይ ላይ የሀብት መራቆት እንዲደርስበትና እራሱን እንዲያጠፉ በማድረጉ በከባድ ሁኔታ አራጣ ማበደር ወንጀል ተከሷል።
25ኛ ክስ
በ4ኛ ተከሳሽ ላይ
ወንጀል
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 407/1/ሀ ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዐቃቤ ህግ ሲሆን የማይገባ ጥቅም ለማግኘትና ለማስገኘት እንዲሁም በሌላ ሰው መብት ወይም ጥቅም ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ ኢኖቫ ፖሊባግ ኃ/የተ/የግ/ማ እ.ኤ.አ ከ2005 እስከ 2009 የገቢ ግብር ብር 16,099.26 (አስራ ስድስት ሺህ ዘጠና ዘጠኝ ብር ከሃያ ስድስት ሳንቲም፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ብር 52,679.93 /ሃምሳ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ሰባ ዘጠኝ ብር ከዘጠና ሶስት ሳንቲም) አለመክፈሉ በወንጀል ምርመራ መዝገብ ተጣርቶ ዐቃቤ ክስ ለመመስረት በዝግጅት ላይ እያለ የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ እና ድርጅቱ በፍ/ቤት እንዳይቀጡ ለማድረግ እንዲሁም በቀረበው የምርምራ መዝገብ ያልተሸፈነ ተጨማሪ ዕዳ ያለበት መሆኑ እየተገለፀለት ባለበት ሁኔታ ምርመራው እንዲቋረጥ ትዕዛዝ ለምርመራ ክፍሉ ሲያስተላልፍ የባለሥልጣኑ የምርመራ ክፍሉም ክስ መቅረብ ሲገባው መቋረጡ ተገቢ አይደለም፣ ጉዳዩ በድጋሚ ታይቶ እንዲወሰን፣ ቢጠይቅም በድጋሚ በቁጥር 5.2.2/5978/1993 መጋቢት 2 ቀን 2005 ዓ.ም ለባለሥልጣኑ ወንጀል ምርመራ ቡድን በፃፈው ደብዳቤ ምርመራው እንዲቋረጥ በማድረጉ በፈፀመው በሥልጣን አላግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል ተከሷል።
26ኛ ክስ
በ2ኛ ፣ 4ኛ፣ 14ኛ እና 15ኛ ተከሳሾች ላይ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴሪ. የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 (1) (ሀ) እና 408 (1) ላይ የተመለከተውን በመተላፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሾች በክሱ በተከሳሾች ዝርዝር ውስጥ በተጠቀሰው ኃላፊነት ሲሰሩ በሥራ ኃላፊነታቸው ማድረግ የማይገባቸውን በማድረግ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት በማሰብ የባለሥልጣኑ ግብር ከፋይ የሆነውን ኦፊስ ቴክ ኃ/ተ/የግል ማህበር ባለቤት አቶ መሀመድ ዩሱፍን ድርጅቱ ኦዲት በሚደረግበት፣ በታክስ ማጭበርበር በወንጀል ከመከሰሱ በፊትና ከተከሰሰም በኋላ በ2002 እና በ2003 ዓ.ም በተለያየ ጊዜ በማግኘት፣
14ኛ ተከሳሽ በ2002 ዓ.ም ጥቅምት ወር ጀምሮ በተለያዩ ቀናት ውስጥ የግል ተበዳዩን ተከታትሎ ካገኘው በኋላ “የላከን ገብረዋህድ ነው የደቡብ ፖሊስ ኮሚሽን አንተን እንድንቀጣላቸው ይፈልጋሉ። ስለዚህ ሁለት ሚሊዮን ብር አምጣ ካልሆነ ግብርም ይጨመርብሃል፤ አንተም ትታሰራለህ” በማለት የግል ተበዳይ ጉቦ እንዲሰጠው በአካልና በስክል በመጠየቁ፣ በመቀጠልም የግል ተበዳይ ወደ ዱባይ ሀገር በሄደበት ወቅት አብሮ እንዲሰራ የተመደበውን ኦዲተር ትቶ ብቻውን ወደ ግል ተበዳይ ድርጅት በመግባት በአንድ ቀን ውስጥ የድርጅቱን ሂሳብ ኦዲት አድርጎ አርባ ሁለት ሚሊዮን ብር በማምጣት በድርጅቱ ውስጥ በተለማማጅነት የምትሰራውንና የመፈረም ሥልጣን የሌላትን 2ኛ የዐቃቤ ህግ ምስክርን አስፈራርቶ በማስፈረሙ፣
2ኛ ተከሳሽ በበኩሉ በ2003 ዓ.ም መጨረሻ ላይ የግል ተበዳይ ግብር ዜሮ እንዲሆንለት የወንጀል ክሱም እንዲቋረጥለት ሁለት ሚሊዮን ብር እንዲከፍል፣ ይህንንም ገንዘብ ዱባይ ሀገር በሚገኝ ሰው አማካኝነት እንዲያስገባ በተደጋጋሚ ጊዜ 14ኛ ተከሳሽንና ሌሎችንም የግል ተበዳይ አዲስ አበበ ውስጥ ኦሎምፒያ በሚባለው አካባቢ ያገኛቸው ሶስት ደላሎችን በመላክ ጉቦ በመጠየቁ፣ በማግስቱም የግል ተበዳይ ሁኔታውን ለማጣራት ፈልጎ ተከሳሹ ቢሮ ሲሄድ ተከሳሹ እንዲገባ ከፈቀደለት በኋላ የግል ተበዳይን “አንተ አመፀኛ ይህ የከተማ ጮሌነት ከአንተ በላይ አውቀዋለሁ። ኦሎምፒያ አካባቢ ከቀጠሩህ ሰዎች ጋር ጨርስ” በማለት የግል ተበዳይን በማስፈራራት በቀጥታ ገንዘቡን እንዲከፍል በመጠየቁ፣
4ኛ እና 14ኛ ተከሳሾች በበኩላቸው የግል ተበዳይ ላይ ክስ ቀርቦበት በሂደት ላይ እያለ የፍ/ቤት ቀጠሮ ለማራዘምና ለተከሳሹ ጊዜ ለመስጠት በሚል በ4ኛ የዐቃቤ ህግ ምስክር አማካኝነት ጉቦ እንዲሰጣቸው በመጠየቅና በመደራደር ሁለት ቶሺባ ላፕቶፕ፣ ሁለት ሲዲኤምኤ እና ብር 20,000 (ሃያ ሺ) ቀኑ ባልታወቀ መስከረም ወር 2004 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ኒዎርክ ካፌ ተቀብለው በመውሰድ ለግል ጥቅማቸው በማዋላቸው፣
በአጠቃላይ ተከሳሾቹ በግል ተበዳይ የሚተዳደረው ኦፊስቴክ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተባለው ድርጅት ኦዲት ከመደረጉ በፊትና ከተደረገም በኋላ እንዲሁም የግል ተበዳይ ላይ የወንጀል ክስ ከመቅረቡ በፊትም ሆነ ከቀረበበት በኋላ የግል ተበዳዩ ግብር እንዲቀነስለት የወንጀል ተጠያቂነትም እንዳይመጣበት ለማድረግ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ 2ኛ እና 14ኛ ተከሳሾች የግል ተበዳይ ጉቦ እንዲሰጣቸው በመጠየቃቸው፣ 4ኛ እና 15ኛ ተከሳሾች ደግሞ ጉቦ በመቀበላቸው ሁሉም ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈጸሙት ጉቦ መጠየቅና መቀበል የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
27ኛ ክስ
በ18ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀፅ 49 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ሆኖ ሲሰራ ከ1998 ዓ.ም እስከ 2004 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ካደረጋቸው የንግድ እንቅስቃሴዎች ከሰበሰበው ገቢ ላይ ለመንግስት ገቢ ማድረግ የነበረበትን የተጨማሪ እሴት ታክስ ብር 32,217,578.36 (ሰላሳ ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ አስራ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ሰባ ስምንት ብር ከ36/100 ሳንቲም) ለመንግስት አሳውቆ መክፈል ሲገባው አስታውቆ ባለመክፈሉ በፈፀመው ህግን በመጣስ ታክስ ያለመክፈል ወንጀል ተከሷል።
28ኛ ክስ
በ10ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሰቴ ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 56(1) እና 49 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በ18ኛ ተከሳሽ ላይ በቀረበው 27ኛ ክስ የተመለከተውን ህግን በመጣስ ታክስን አስታውቆ ያለመክፈል ወንጀል ድርጊት ሲፈፀም የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ በመሆኑ በፈፀመው ህግን በመጣስ ታክስ ያለመክፈል ወንጀል ተከሷል።
29ኛ ክስ
በ18ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀፅ 50(1) እና 3(ለ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በ27ኛ ክስ በተጠቀሰው ጊዜ ለግብር አስገቢው ባለሥልጣን በህግ በተደነገገው የሂሳብ ጊዜ ገቢ መደረግ የሚገባውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ብር 32,217,578.36 (ሰላሳ ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ አስራ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ሰባ ስምንት ብር ከ36/100 ሳንቲም) አስታውቆ መክፈል ሲገባው ሊከፍል የሚገባውን ሳይገልፅ በመቅረቱ በፈፀመው አሳሳች መረጃ ማቅረብ ወንጀል ተከሷል።
30ኛ ክስ
በ10ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀፅ 56(1)፣50(1) እና 3(ለ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፡-
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በ18ኛ ተከሳሽ ላይ በቀረበው 29ኛ ክስ የተመለከተው አሳሳች መረጃ ማቅረብ የወንጀል ድርጊት ሲፈፅም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በወንጀል ተከሷል።
31ኛ ክስ
በ18ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀፅ 96 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፡-
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከ2001 እስከ 2004 ዓ.ም ባሉት የግብር ዓመታት ካከናወናቸው የንግድ እንቅስቃሴዎች ብር 17,869,941.49 (አስራ ሰባት ሚሊዮን ስምነት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ አንድ ብር ከ49/100 ሳንቲም) ለመንግሥት አስታውቆ መክፈል ሲገባው አሳውቆ ባለመክፈሉ በፈፀመው ህግን በመጣስ ግብርን ባለመክፈል ወንጀል ተከሷል።
32ኛ ክስ
በ10ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 102(1) እና 96 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፡-
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከላይ በ18ና ተከሳሽ ላይ በቀረበው 31ኛ ክስ የተመለከተው ህግን በመጣስ ግብርን ያለመክፈል የወንጀል ድርጊት ሲፈፀም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በወንጀል ተከሷል።
33ኛ ክስ
በ18ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1004 አንቀጽ 97(1) እና 3(ለ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በግብር ከፋይነት የሚታወቅ ድርጅት ሆኖ የንግድ ሥራ እያከናወነ በህግ ከተፈቀደው አሰራር ውጭ የሂሳብ አያያዝ መርሆዎች ከሚፈቅዱት በተለየ መልኩ በመስራት ከ1998 እስከ 2004 ዓ.ም ባሉት የግብር ዓመታት በአጠቃላይ ብር 17,869,941.49 (አስራ ሰባት ሚሊዮን ስምንት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ አንድ ብር ከ49/100 ሳንቲም) አስታውቆ መክፈል ሲገባው ሊከፍል የሚገባውን ሳይገልፅ በመቅረቱ በፈፀመው አሳሳች መረጃ ማቅረብ ወንጀል ተከሷል።
34ኛ ክስ
በ10ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ 286/1994 አንቀጽ 102(1)፣97(1) እና 3(ለ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፡-
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከላይ በ18ና ተከሳሽ ላይ በቀረበው 33ኛ ክስ የተመለከተውን አሳሳች መረጃ የማቅረብ ወንጀል ድርጊት ሲፈፅም ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በወንጀል ተከሷል።
35ኛ ክስ
በ10ኛ እና 18ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1997 ዓ.ም ሥራ ላይ የዋለውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 32(1) (ሀ) (3) እናየጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀፅ 93(1)(ሀ)2 ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፡-
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሾች ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት በማሰብ ከ1998 እስከ 2004 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ከውጭ አገር ወደ አገር ውስጥ ያስገቧቸው የተለያዩ ዕቃዎች በህጉ በተቀመጠው የእቃዎች የታሪፍ አመዳደብና የዋጋ ተመን መሰረት ክፍያ መክፈል ሲገባቸው ከህግና ከመመሪያ ውጭ በመስተናገድ ብር 9,543,391.45 በማጭበርበር ያለአግባብ ተጠቃሚ በመሆናቸው በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት የማጭበርበር ወንጀል ተከሰዋል።
36ኛ ክስ
በ10ኛ እና በ18ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1997 ዓ.ም ሥራ ላይ የዋለውን የኢፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)(3)፣ 684(1)(2)(6) እና (7) ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሾች ከላይ በተመለከቱት ከባድ የወንጀል ድርጊቶች ከ1998 እስከ 2004 ዓ.ም ድረስ ለመንግሥት መከፈል የሚገባውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ብር 32,217,578.36 (ሰላሳ ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ አስራ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ሰባ ስምንት ብር ከ36/100 ሳንቲም)፣ የገቢ ግብር 17,869,941.49 (አስራ ሰባትሚሊዮን ስምንት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሺ ዘጠኝ መቶ አርባ አንድ ብር ከ49/100 ሳንቲም)፣ ከገቢ ዕቃዎች ብር 9,543,391.45 (ዘጠኝ ሚሊዮን አምስት መቶ አርባ ሶስት ሺህ ሶስት መቶ ዘጠና ሺ ዘጠኝ መቶ አስራ አንድ ከ30/100 ሳንቲም) ከግብርና ታክስ ስወራ የተገኘ ገንዘብን ህጋዊ አስመስለው በማቅረባቸው በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት ከወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብና በወንጀሉ መርዳት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
37ኛ ክስ በ19ና ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 49 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፡-
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ሆኖ ሲሰራ ከ1998 ዓ.ም እስከ 2004 ዓ.ም ድረስ ካደረጋቸው የንግድ እንቅስቃሴዎች ከሰበሰበው ገቢ ላይ ለመንግሥት ገቢ ማድረግ የነበረበትን የተጨማሪ እሴት ታክስ ብር 20,111,328.94 (ሃያ ሚሊዮን አንድ መቶ አስራ አንድ ሺህ ሶስት መቶ ሃያ ስምንት ብር ከ94/100 ሳንቲም) ለመንግስት አሳውቆ መክፈል ሲገባው አሳውቆ ባለመክፈሉ በፈፀመው ህግን በመጣስ ታክስ ያለመክፈል ወንጀል ተከሷል።
38ኛ ክስ በ11ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 56(1) እና 49 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፡-
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በ19ኛ ተከሳሽ ላይ በቀረበው 37ኛ ክስ የተመለከተውን ህግን በመጣስ ታክስን አስታውቆ ያለመክፈል ወንጀል ድርጊት ሲፈፀም የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ በመሆኑ በፈፀመው ህግን በመጣስ ታክስ ያለመክፈል ወንጀል ተከሷል።
39ኛ ክስ
በ19ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 50(1) እና 3(ለ) ላይ ተመለከተውን በመተላለፉ፡-
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በ37ኛ ክስ በተጠቀሰው ጊዜ ለግብር አስገቢው ባለሥልጣን በህግ በተደነገገው የሂሳብ ጊዜ ገቢ መደረግ የሚገባው የተጨማሪ እሴት ታክስ ብር 20,111,328.94 (ሃያ ሚሊዮን አንድ መቶ አስራ አንድ ሺህ ሶስት መቶ ሃያ ስምንት ብር ከ49/100 ሳንቲም) አስታውቆ መክፈል ሲገባው ሊከፍል የሚገባውን ሳይገልጽ በመቅረቱ በፈፀመው አሳሳች መረጃ ማቅረብ ወንጀል ተከሷል።
40ኛ ክስ
በ11ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 56(1)፣ 50(1) እና 3(ለ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፡-
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በ19ኛ ተከሳሽ ላይ በቀረበው 39ኛ ክስ የተመለከተው አሳሳች መረጃ ማቅረብ የወንጀል ድርጊት ሲፈፅም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በወንጀል ተሰኳል።
41ኛ ክስ
በ19ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀፅ 96 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፡-
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከ2001 እስከ 2004 ዓ.ም ባሉት የግብር ዓመታት ካከናወናቸው የንግድ እንቅስቃሴዎች ብር 29,433,214.24 (ሃያ ዘጠኝ ሚሊዮን አራት መቶ ሰላሳ ሶስት ሺህ ሁለት መቶ አስራ አራት ብር ከ24/100 ሳንቲም) የገቢ ግብር እና በግዥና እቃ አቅርቦት ውል ከሚፈፀም ክፍያ ብር 632,860.27 (ስድስት መቶ ሰላሳ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ዘጠና ስልሳ ብር ከ27/100 ሳንቲም) ለግብር አስገቢው ባለስልጣን ገቢ ባለማድረጉና አስታውቆ መክፈል የሚገባውን ግብር አሳውቆ ባለመክፈሉ በፈፀመው ህግን በመጣስ ግብርን ባለመክፈል ወንጀል ተከሷል።
42ኛ ክስ
በ11ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀፅ 102(1) እና 96 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፡-
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከላይ በ19ኛ ተከሳሽ ላይ በቀረበው 41ኛ ክስ የተመለከተው ህግን በመጣስ ግብርን ያለመክፈል የወንጀል ድርጊት ሲፈፀም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በወንጀል ተከሷል።
43ኛ ክስ
በ19ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1991 አንቀጽ 97(1) እና 3(ለ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በግብር ከፋይነት የሚታወቅ ድርጅት ሆኖ የንግድ ሥራ እያከናወነ በህግ ከተፈቀደው አሰራር ውጭ የሂሳብ አያያዝ መርሆዎች ከሚፈቅዱት በተለየ መልኩ በመሥራት ከ2001 እስከ 2004 ዓ.ም ባሉት የግብር ዓመታት የንግድ ትርፍ ግብር ብር 29,433,214.24 (ሃያ ዘጠኝ ሚሊዮን አራት መቶ ሰላሳ ሶስት ሺህ ሁለት መቶ አስራ አራት ብር ከ24/100 ሳንቲም) እና በግዥና እቃ አቅርቦት ውል 632,860.27 (ስድስት መቶ ሰላሳ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ዘጠና ስልሳ ብር ከ27/100 ሳንቲም) በድምሩ 30,263,641.12 (ሰላሳ ሚሊዮን ሁለት መቶ ስልሳ ሶስት ሺህ ስድስት መቶ አርባ አንድ ብር ከ12/100 ሳንቲም) አስታውቆ መክፈል ሲገባው ሊከፍል የሚገባውን ሳይገልፅ በመቅረቱ በፈፀመው አሳሳች መረጃ ማቅረብ ወንጀል ተከሷል።
44ኛ ክስ
በ11ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ 286/1994 አንቀጽ 102(1)፣97(1) እና 3(ለ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከላይ በ19ኛ ተከሳሽ ላይ በቀረበው 43ኛ ክስ የተመለከተውን አሳሳች መረጃ የማቅረብ ወንጀል ድርጊት ሲፈፅም ሰራ አስኪያጅ በመሆኑ በወንጀል ተከሷል።
45ኛ ክስ
በ11ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ2001 ዓ.ም ሥራ ላይ የዋለውን የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 98(1) ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፡-
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ ከ2001 እስከ 2004 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ በ19ኛ ተከሳሽ ስም የቀረጥ ነፃ መብት በመጠቀም ወደ ሀገር የገቡ የቀረጥና ታክስ መጠናቸው ብር 197,556.61 (አንድ መቶ ዘጠና ሰባት ሺህ አምስት መቶ ሃምሳ ስድስት ብር ከ61/100 ሳንቲም የሆኑ ለኮንስትራክሽን መሳሪያዎች ኪራይ ፕሮጀክት አገልግሎት እንዲያውል ከቀረጥ ታክስ ነፃ ተፈቅዶለት እያለ ከተፈቀደለት ዓላማ ውጭ ለሆቴል ማስፋፊያ ስራ በማዋሉ በፈጸመው ከቀረጥ ነፃ የገባን ዕቃ አላግባብ መገልገል ወንጀል ተከሷል።
46ኛ ክስ በ11ኛ እና በ19ና ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1997 ዓ.ም ሥራ ላይ የዋለውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)(3)፣ 684(1)(2)(6) እና (7) ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣
የወንጀሉ ዝርዝር

ተከሳሾች ከላይ በተመለከቱት ከባድ የወንጀል ድርጊቶች ከ1998 እስከ 2004 ዓ.ም ድረስ ለመንግሥት መከፈል የሚገባውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ብር 20,111,328.94 (ሃያ ሚሊዮን አንድ መቶ አስራ አንድ ሺህ ሶስት መቶ ሃያ ስምንት ብር ከ94/100 ሳንቲም)፤ የንግድ ትርፍ ግብር ብር 29,433,214.24 ሃያ ዘጠኝ ሚሊዮን አራት መቶ ሰላሳ ሶስት ሺህ ሁለት መቶ አስራ አራት ብር ከ24/100 ሳንቲም፤ በግዥና እቃ አቅርቦት ውል ከሚፈፀም ክፍያ ላይ ሁለት በመቶ የንግድ ትርፍ ግብር ቀንሶ ማስቀረት ሲገባው ብር 632,860.27 (ስድስት መቶ ሰላሳ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ዘጠና ስልሳ ብር ከ27/100 ሳንቲም) እና በ19ኛ ተከሳሽ ስም የቀረጥ ነፃ መብት በመጠቀም ወደ ሀገር የገቡ የቀረጥና ታክስ መጠናቸው ብር 197,556.61 (አንድ መቶ ዘጠና ሰባት ሺህ አምስት መቶ ሃምሳ ስድስት ብር ከ61/100 ሳንቲም) የሆኑ ለኮንስትራክሽን መሳሪያዎች ኪራይ ፕሮጀክት አገልግሎት እንዲያውል ከቀረጥ ታክስ ነፃ ተፈቅዶለት እያለ ከተፈቀደለት ዓላማ ውጭ ለሆቴል ማስፋፊያ ስራ በማዋሉ በድምሩ ብር 50,374,960.06 (ሃምሳ ሶስት መቶ ሰባ አራት ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳ ብር ከ06/100 ሳንቲም) ከግብርና ታክስ ስወራ የተገኘ ገንዘብን ህጋዊ አስመስለው በማቅረባቸው በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት ከወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብና በወንጀሉ መርዳት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።

47ኛ ክስ
በ9ኛ፣ 16ኛ፣ 17ኛ፣ ከ20ኛ–22ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ

ወንጀሉ
የጉምሩክ ባለስልጣንን እንደገና ለማቋቋምና አሰራሩን ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁጥር 60/89 አንቀፅ 64/3(ሀ) እና (ለ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው፣

የወንጀሉ ዝርዝር
9ኛ፣ 16ኛ እና 17ኛ ተከሳሾች እንደቅደምተከተላቸው በህግ የሰውነት መብት የተሰጣቸው የ20ኛ፣ 21ኛ እና 22ኛው ተከሳሾች ባለቤትና ስራ አስኪያጆች ሲሆኑ ከ1999 ዓ.ም እስከ 2000 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት በፍራንኮቫሉታ /ከቀረጥና ታክስ ነፃ መብት/ ከውጪ አገር በጂቡቲ በኩል 9ኛ እና 20 ተከሳሾች 13150 ኩንታል ሲሚንቶ፣ 16ኛ እና 21 ተከሳሾች 9000 ኩንታል ሲሚንቶ 17ኛ እና 22 ተከሳሾች 28980 ኩንታል ሲሚንቶ በየራሳቸው የትራንስፖርት ድርጅቶች በማጓጓዝ ካስገቡ በኋላ በገቡት ኃላፊነት መሰረት ያስገቡትን ሲሚንቶ በሙሉ ለተጠቃሚው አካል ማስረከብ ሲገባቸው በገበያ ላይ ለሽያጭ ለማዋል እንዳልሆነ እያወቁ የጉምሩክ ስነ ሥርዓት ባልተፈጸመበት መንገድ በመጠቀም ከታለመለት አላማ ውጪ 9ኛ እና 20ኛ ተከሳሾች 18950 ኩንታል ሲሚንቶ፣ 16ኛው እና 21ኛው ተከሳሾች 8540 ኩንታል ሲሚንቶ፣ 17ኛው እና 22ኛው ተከሳሾች 17020 ኩንታል ሲሚንቶ ለ3ኛ ወገን በማስተላለፋቸው ሁሉም ተከሳች በፈፀሙት የማጓጓዝ ኃላፊነት ግዴታን በመጣስ ወንጀል ተከሰዋል።

48ኛ ክስ
በ20ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 96 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፤

የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ47ኛው ክስ ላይ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ እንዲሁም ሁኔታ ከቀረጥና ታክስ ነፃ መብት ገብቶ ለግል ተጠቃሚ በተላለፈው ሲሚንቶ መክፈል የነበረበትን ብር 1,490,103.97 /አንድ ሚሊዮን አራ መቶ ዘጠና ሺህ አንድ መቶ ሰላሳ ሶስት ብር ዘጠና ሰባት ሳንቲም/ የገቢ ግብር ባለመክፈሉ በፈፀመው ህግን በመጣስ ግብርን አለመክፈል ወንጀል ተከሷል።

49ኛ ክስ
በ9ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 102/1/ እና 96 ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ

የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ48ኛ ክስ ላይ የተመለከተው ህግን በመጣስ ግብርን ያለመክፈል የወንጀል ድርጊት ሲፈፀም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በወንጀል ተከሰዋል።

50ኛ ክስ
በ20ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥረ 286/94 አንቀጽ 97/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ47ኛው ክስ ላይ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ እንዲሁም ሁኔታ ከቀረጥና ታክስ ነፃ መብት ገብቶ ለግል ተጠቃሚ በተላለፈው ሲሚንቶ መክፈል የነበረበትን ብር 1,490,103.97 /አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ዘጠና ሺህ አንድ መቶ ሰላሳ ሶስት ብር ዘጠና ሰባት ሳንቲም/ የገቢ ግብር ባለመክፈሉ በፈፀመው አሳሳች መረጃ ማቅረብ ወንጀል ተከሷል።
51ኛ ክስ
በ9ኛ ተከሳሽ ላይ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀፅ 102/1/፣ 97/1 እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከላይ በ50ኛ ክስ የተመለከተው አሳሳች መረጃ የማቅረብ ወንጀል ድርጊት ሲፈፀም ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በወንጀል ተከሷል።
52ኛ ክስ
በ20ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 49 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ47ኛው ክስ ላይ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ እንዲሁም ሁኔታ ከቀረጥ ነፃ መብት ገብቶ ለግል ተጠቃሚ በተላለፈው ሲሚንቶ ካገኘው ገቢ ላይ መክፈል የነበረበትን ብር 5,093,734.61 /አምስት ሚሊዮን ዘጠና ሶስት ሺህ ሰባት መቶ ሰላሳ አራት ብር ከስልሳ አንድ ሳንቲም/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ባለመክፈሉ በፈፀመው ህግን በመጣስ ግብርን አለመክፈል ወንጀል ተከሷል።
53ኛ ክስ
በ9ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 56/1/ እና 49 ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ።

የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በ52ኛ ክስ ላይ የተመለከተው ህግን በመጣስ ታክስን አስታውቆ ያለመክፈል ወንጀል ድርጊት ሲፈፀም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በፈፀመው ህግን በመጣስ ታክስ ያለመክፈል ወንጀል ተከሰዋል።

54ኛ ክስ
በ20ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 50/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፤
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ47ኛው ክስ ላይ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ እንዲሁም ሁኔታ ከቀረጥ ነፃ መብት ገብቶ ለግል ተጠቃሚ በተላለፈው ሲሚንቶ ካገኘው ገቢ ላይ መክፈል የነበረበትን ብር 5,093,734.61 /አምስት ሚሊዮን ዘጠና ሶስት ሺህ ሰባት መቶ ሰላሳ አራት ብር ከስልሳ አንድ ሳንቲም/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ባለመክፈሉ በፈፀመው አሳሳች መረጃ ማቅረብ ወንጀል ተከሷል።

55ኛ ክስ
በ9ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 56/1/፣ 50/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከላይ በ54ኛ ክስ የተመለከተው አሳሳች መረጃ ማቅረብ የወንጀል ድርጊት ሲፈፀም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በወንጀል ተከሷል።

56ኛ ክስ
በ21ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 96 ላይ የተመለከተውን በተመላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ47ኛ በቀረበው ክስ ላይ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ እንዲሁም ሁኔታ ከቀረጥና ነፃ መብት ገብቶ ለግል ተጠቃሚ በተላለፈው ሲሚንቶ መክፈል የነበረበትን ብር 5,489,670.63 /አምስት ሚሊዮን አራት መቶ ሰማንለያ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ ሰባ ብር ከስልሳ ሶስት ሳንቲም/ የገቢ ግብር ባለመክፈሉ በፈፀመው ህግን በመጣስ ግብርን አለመክፈል ወንጀል ተከሷል።

57ኛ ክስ
በ16ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 102/1/ እና 96 ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ56ኛ ክስ ላይ የተመለከተው ህግን በመጣስ ግብርን ያለመክፈል የወንጀል ድርጊት ሲፈፀም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በወንጀል ተከሰዋል።

58ኛ ክስ
በ21ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 97/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ47ኛው ክስ ላይ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ እንዲሁም ሁኔታ ከቀረጥና ታክስ ነፃ መብት ገብቶ ለግል ተጠቃሚ በተላለፈው ሲሚንቶ መክፈል የነበረበትን ብር 5,489,670.63 /አምስት ሚሊዮን አራት መቶ ሰማንያ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ ሰባ ብር ከስልሳ ሶስት ሳንቲም/ የገቢ ግብር ባለመክፈሉ በፈፀመው ባለመክፈሉ በፈፀመው አሳሳች መረጃ ማቅረብ ወንጀል ተከሷል።

59ኛ ክስ
በ16ኛ ተከሳሽ ላይ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 102/1/፣ 97/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከላይ በ58ኛ ክስ የተመለከተው አሳሳች መረጃ የማቅረብ ወንጀል ድርጊት ሲፈፀም ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በወንጀል ተከሷል።

60ኛ ክስ
በ21ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁር 285/94 አንቀጽ 49 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ47ኛው ክስ ላይ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ እንዲሁም ሁኔታ ከቀረጥ ነፃ መብት ገብቶ ለግል ተጠቃሚ በተላለፈው ሲሚንቶ ካገኘው ገቢ ላይ መክፈል የነበረበትን ብር 17,328,345.99 /አስራ ሰባት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሃያ ስምንት ሺህ ሶስት መቶ አርባ አምስት ብር ከዘጠና ዘጠኝ ሳንቲም/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ባለመክፈሉ በፈፀመው ህግን በመጣስ ግብርን አለመክፈል ወንጀል ተከሷል።

61ኛ ክስ
በ16ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀፅ 56/1/ እና 49 ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ።
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በ60ኛ ክስ ላይ የተመለከተው ህግን በመጣስ ታክስን አስታውቆ ያለመክፈል ወንጀል ድርጊት ሲፈፀም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በፈፀመው ህግን በመጣስ ታክስ ያለመክፈል ወንጀል ተከሰዋል።

62ኛ ክስ
በ21ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 50/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ47ኛው ክስ ላይ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ እንዲሁም ሁኔታ ከቀረጥ ነፃ መብት ገብቶ ለግል ተጠቃሚ በተላለፈው ሲሚንቶ ካገኘው ገቢ ላይ መክፈል የነበረበትን ብር 17,328,345.99 /አስራ ሰባት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሃያ ስምንት ሺህ ሶስት መቶ አርባ አምስት ብር ከዘጠና ዘጠኝ ሳንቲም/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ባለመክፈሉ በፈፀመው አሳሳች መረጃ ማቅረብ ወንጀል ተከሷል።

63ኛ ክስ
በ16 ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁር 285/1994 አንቀጽ 56/1/፣ 50/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከላይ በ62ኛ ክስ የተመለከተው አሳሳች መረጃ ማቅረብ የወንጀሉ ድርጊት ሲፈፀም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በወንጀል ተከሷል።

64ኛ ክስ
በ22ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 96 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ47ኛው ክስ ላይ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ እንዲሁም ሁኔታ ከቀረጥና ነፃ መብት ገብቶ ለግል ተጠቃሚ በተላለፈው ሲሚንቶ መክፈል የነበረበትን ብር 1,461,331.13 /አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ስልሳ አንድ ሺህ ሶስት መቶ ሰላሳ አንድ ብር ከአስራ ሶስት ሳንቲም/ የገቢ ግብር ባለመክፈሉ በፈፀመው ህግን በመጣስ ግብርን አለመክፈል ወንጀል ተከሷል።

65ኛ ክስ
በ17ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 102/1/ እና 96 ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ64ኛ ክስ ላይ የተመለከተው ህግን በመጣስ ግብርን ያለመክፈል የወንጀል ድርጊት ሲፈፀም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በወንጀል ተከሰዋል።

66ኛ ክስ
በ22ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
የገቢ ግብር አዋጅ ቁር 286/94 አንቀጽ 97/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ47ኛው ላይ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ እንዲሁም ሁኔታ ከቀረጥና ታክስ ነፃ መብት ገብቶ ለግል ተጠቃሚ በተላለፈው ሲሚንቶ መክፈል የነበረበትን ብር 1,461,331.13 /አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ስልሳ አንድ ሺህ ሶስት መቶ ሰላሳ አንድ ብር ከአስራ ሶስት ሳንቲም/ የገቢ ግብር ባለመክፈሉ በፈፀመው አሳሳች መረጃ ማቅረብ ወንጀል ተከሷል።

67ኛ ክስ
በ17ኛ ተከሳሽ ላይ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 102/1/፣ 97/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ።
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከላይ በ66ኛ ክስ ላይ የተመለከተው አሳሳች መረጃ ማቅረብ የወንጀል ድርጊት ሲፈፀም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ ተከሷል።

68ኛ ክስ
በ22ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 49 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ47ኛው ክስ ላይ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ እንዲሁም ሁኔታ ከቀረጥ ነፃ መብት ገብቶ ለግል ተጠቃሚ በተላለፈው ሲሚንቶ ካገኘው ገቢ ላይ መክፈል የነበረበትን ብር 4,902,285.69 /አራት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ሰማንያ አምስት ብር ከስልሳ ዘጠኝ ሳንቲም/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ባለመክፈሉ በፈፀመው ህግን በመጣስ ግብርን አለመክፈል ወንጀል ተከሷል።

69ኛ ክስ
በ17ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 56/1/ እና 49 ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ።
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከላይ በ68ኛ ክስ ላይ የተመለከተው ህግን በመጣስ ታክስን አስታውቆ ያለመክፈል ወንጀል ድርጊት ሲፈፀም የደርጅቱ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በፈፀመው ህግን በመጣስ ታክስ ያለመክፈል ወንጀል ተከሰዋል።

70ኛ ክስ
በ22ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 50/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በ47ኛው ክስ ላይ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ እንዲሁም ሁኔታ ከቀረጥ ነፃ መብት ገብቶ ለግል ተጠቃሚ በተላለፈው ሲሚንቶ ካገኘው ገቢ ላይ መክፈል የነበረበትን ብር 4,902,285.69 /አራት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ሰማንያ አምስት ብር ከስልሳ ዘጠኝ ሳንቲም/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ባለመክፈሉ በፈፀመው አሳሳች መረጃ ማቅረብ ወንጀል ተከሷል።

71ኛ ክስ
በ17ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 56/1/፣ 50/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከላይ በ70ኛ ክስ ላይ የተመለከተው አሳሳች መረጃ ማቅረብ የወንጀል ድርጊት ሲፈፀም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ ተከሷል።

72ኛ ክስ
በ9ኛ እና 20ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1997 ዓ.ም ስራ ላይ የዋለውን የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ/3/፣ 684/1/2/6 እና /7/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሾች ከላይ በተመለከቱት 48ኛ እና 52ኛ ክሶች በተጠቀሱት ከባድ የወንጀል ድርጊቶች ለመንግስት መክፈል የነበረባቸውን ግብር 1,490,103.97 ብር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ 5,093,734.61 ብር በድምሩ በር 6,583,838.558 /ስድስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሰማንያ ሶስት ሺህ ስምንት መቶ ሰላሳ ስምንት ብር ከሃምሳ ስምንት ሳንቲም/ የሆነውን የመንግስት ገንዘብ ህጋዊ አስመስለው በማቅረባቸው በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት ከወንጀል የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብለና በወንጀሉ መርዳት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።

73ኛ ክስ
በ16ኛ እና 21ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1997 ዓ.ም ስራ ላይ የዋለውን የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1//ሀ/3/፣ 684/1/2/6 እና /7/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሾች ከላይ በተመለከቱት 56ኛ እና 60ኛ ክሶች በተጠቀሱት ከባድ የወንጀል ድርጊቶች ለመንግስት መክፈል የነበረባቸውን ግብር 5489670 ብር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ 17,328,345.99 ብር በድምሩ ብር 22,818,016.62 /ሃያ ሁለት ሚሊዮን ስምንት መቶ አስራ ስምንት ሺህ አስራ አድስት ብር ከስልሳ ሁለት ሳንቲም/ የሆነውን የመንግስት ገንዘብ ህጋዊ አስመስለው በማቅረባቸው በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት ከወንጀል የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብና በወንጀሉ መርዳት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።

74ኛ ክስ
በ17ኛ እና 22ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1997 ዓ.ም ስራ ላይ የዋለውን የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ/3/፣ 684/1/2/6 እና /7/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ።
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሾች ከላይ በተመለከቱት 64ኛ እና 68ኛ ክሶች በተጠቀሱት ከባድ የወንጀል ድርጊቶች ለመንግስት መክፈል የነበረባቸውን ግብር 1,461,331.13 ብር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ 4,902,285.69 ብር በድምሩ ብር 6,363,616.82 /ስድስት ሚሊዮን ሶስት መቶ ስልሳ ሶስት ሺህ ስድስት መቶ አስራ ስድስት ብር ከሰማንያ ሁለት ሳንቲም/ የሆነውን የመንግስት ገንዘብ ህጋዊ አስመስለው በማቅረባቸው በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት ከወንጀል የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብና በወንጀሉ መርዳት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።

75ኛ ክስ
በ20ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 49 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ።
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ሆኖ ሲሰራ ከ1998 ዓ.ም እስከ 2004 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ካደረጋቸው የንግድ እንቅስቃሴዎች ከሰበሰበው ገቢ ላይ ለመንግስት ገቢ ማድረግ የነበረበትን የተጨማሪ እሴት ታክስ ብር 37,895,645.90 /ሰላሳ ሰባት ሚሊዮን ስምንት መቶ ዘጠና አምስት ሺ ስድስት መቶ አርባ አምስት ብር ከ90/100 ሳንቲም/ ለመንግስት አሳውቆ መክፈል ሲገባው አስታውቆ ባለመክፈሉ በፈፀመው ህግን በመጣስ ታክስ ያለመክፈል ወንጀል ተከሷል።

76ኛ ክስ
በ9ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 56/1/ እና 49 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በ20ኛ ተከሳሽ ላይ በቀረበው 75ኛ ክስ የተመለከተውን ህግን በመጣስ ታክስን አስታውቆ ያለመክፈል ወንጀል ድርጊት ሲፈፀም የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ በመሆኑ በፈፀመው ህግን በመጣስ ታክስ ያለመክፈል ወንጀል ተከሷል።

77ኛ ክስ
በ20ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 50/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በ75ኛ ክስ በተጠቀሰው ጊዜ ለግብር አስገቢው ባለስልጣን በህግ በተደነገገው የሂሳብ ጊዜ ገቢ መደረግ የሚገባውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ብር 37,895,645.90 /ሰላሳ ሰባት ሚሊዮን ስምንት መቶ ዘጠና አምስት ሺህ ስድስት መቶ አርባ አምስት ብር ከ90/100 ሳንቲም/ አስታውቆ መክፈል ሲገባው ሊከፍል የሚገባውን ሳይገልፅ በመቅረቱ በፈፀመው አሳሳች መረጃ ማቅረብ ወንጀል ተከሷል።

78ኛ ክስ
በ9ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 56/1/፣ 50/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በ20ኛ ተከሳሽ ላይ በቀረበው 77ኛ ክስ የተመለከተው አሳሳች መረጃ ማቅረብ የወንጀል ድርጊት ሲፈፅም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በወንጀል ተከሷል።

79ኛ ክስ
በ20ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 96 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከ1998 እስከ 2004 ዓ.ም ባሉት የግብር ዓመታት ካከናወናቸው የንግድ እንቅስቃሴዎች ብር 32,666,482.23 /ሰላሳ ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት ሺህ አራት መቶ ሰማንያ ሁለት ብር ከ23/100 ሳንቲም/ ለመንግስት አስታውቆ መክፈል ሲገባው አሳውቆ ባለመክፈሉ በፈፀመው ህግን በመጣስ ግብርን ባለመክፈል ወንጀል ተከሷል።

80ኛ ክስ
በ9ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 102/1/ እና 96 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከላይ በ20ኛ ተከሳሽ ላይ በቀረበው 79ኛ ክስ የተመለከተው ህግን በመጣስ ግብርን ያለመክፈል የወንጀል ድርጊት ሲፈፀም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በወንጀል ተከሷል።

81ኛ ክስ
በ20 ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 97/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በግብር ከፋይነት የሚታወቅ ድርጅት ሆኖ የንግድ ሥራ እያከናወነ በህግ ከተፈቀደው አሰራር ውጭ የሂሳብ አያያዝ መርሆዎች ከሚፈቅዱት በተለየ መልኩ በመስራት ከ1998 እስከ 2004 ዓ.ም ባሉት የግብር ዓመታት በአጠቃላይ ብር 32,666,482.23 /ሰላሳ ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት ሺህ አራት መቶ ሰማንያ ሁለት ብር ከ23/100 ሳንቲም/ አስታውቆ መክፈል ሲገባው ሊከፍል የሚገባውን ሳይገልፅ በመቅረቱ በፈፀመው አሳሳች መረጃ ማቅረብ ወንጀል ተከሷል።

82ኛ ክስ
በ9ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ 286/1994 አንቀጽ 102/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከላይ በ20ኛ ተከሳሽ ላይ በቀረበው 81ኛ ክስ የተመለከተውን አሳሳች መረጃ የማቅረብ ወንጀል ድርጊት ሲፈፅም ስራ አስኪያጅ በመሆኑ በወንጀል ተከሷል።

83ኛ ክስ
በ9ኛ እና በ20ኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1997 ዓ.ም ሥራ ላይ የዋለውን የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 32/1/ሀ/3/፣ 684/1/2/6/ እና /7/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፋቸው።
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሾች ከላይ በተመለከቱት ከባድ የወንጀል ድርጊቶች ከ1998 እስከ 2004 ዓ.ም ድረስ ለመንግስት መከፈል የሚገባውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ብር 37,895,645.90 /ሰላሳ ሰባት ሚሊዮን ስምንት መቶ ዘጠና አምስት ሺህ ስድስት መቶ አርባ አምስት ብር ከ90/100 ሳንቲም/፣ የገቢ ግብር 32,666,482.23 /ሰላሳ ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት ሺህ አራት መቶ ሰማንያ ሁለት ብር ከ23/100 ሳንቲም/ በድምሩ ብር 70,562,128.23 /ሰባ ሚሊዮን አምስት መቶ ስልሳ ሁለት ሺህ አንድ መቶ ሃያ ስምንት ከ23/100 ሳንቲም/ ከግብርና ታክስ ስወራ የተገኘ ገንዘብን ህጋዊ አስመስለው በማቅረባቸው በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት ከወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብለና በወንጀሉ መርዳት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።

84ኛ ክስ በ23ኛ ተከሳሽ ላይ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 49 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ሆኖ ሲሰራ ከ1998 ዓ.ም እስከ 2004 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ካደረጋቸው የንግድ እንቅስቃሴዎች ከሰበሰበው ገቢ ላይ ለመንግስት ገቢ ማድረግ የነበረበትን የተጨማሪ እሴት ታክስ ብር 1,384,683.67 /አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰማንያ አራት ሺህ ስድስት መቶ ሰማንያ ሶስት ብር ከ67/100 ሳንቲም/ ለመንግስት አሳውቆ መክፈል ሲገባው አስታውቆ ባለመክፈሉ በፈፀመው ህግን በመጣስ ታክስ ያለመክፈል ወንጀል ተከሷል።

85ኛ ክስ በ23ኛ ተከሳሽ ላይ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 50/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በ84ኛ ክስ በተጠቀሰው ጊዜ ለግብር አስገቢው ባለስልጣን በህግ በተደነገገው የሂሳብ ጊዜ ገቢ መደረግ የሚገባውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ብር 1,384,683.67 /አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰማንያ አራት ሺህ ስድስት መቶ ሰማንያ ሶስት ብር ከ67/100 ሳንቲም/ አስታውቆ መክፈል ሲገባ ሊከፍል የሚገባውን ሳይገልፅ በመቅረቱ በፈፀመው አሳሳች መረጃ ማቅረብ ወንጀል ተከሷል።

86ኛ ክስ በ23ኛ ተከሳሽ ላይ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 96 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ ከ1998 እስከ 2004 ዓ.ም ባሉት የግብር ዓመታት ካከናወናቸው የንግድ እንቅስቃሴዎች ብር 3,859,605.26 /ሶስት ሚሊዮን ስምንት መቶ አምሳ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ አምስት ብር ከ20/100 ሳንቲም/ ለመንግሥት አስታውቆ መክፈል ሲገባው አሳውቆ ባለመክፈሉ በፈፀመው ህግን በመጣስ ግብርን ባለመክፈል ወንጀል ተከሷል።

87ኛ ክስ በ23ኛ ተከሳሽ ላይ
ወንጀሉ
በ1994 ዓ.ም የወጣውን የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 97/1/ እና 3/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሽ በግብር ከፋይነት የሚታወቅ ድርጅት ሆኖ የንግድ ሥራ እያከናወነ በህግ ከተፈቀደው አሰራር ውጭ የሂሳብ አያያዝ መርሆዎች ከሚፈቅዱት በተለየ መልኩ በመስራት ከ1998 እስከ 2004 ዓ.ም ባሉት የግብር ዓመታት በአጠቃላይ ብር 3,859,605.26 /ሶስት ሚሊዮን ስምንት መቶ አምሳ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ አምስት ብር ከ26/100 ሳንቲም/ አስታውቆ መክፈል ሲገባው ሊከፍል የሚገባውን ሳይገልፅ በመቅረቱ በፈፀመው አሳሳች መረጃ ማቅረብ ወንጀል ተከሷል።

88ኛ ክስ
በ23ኛ ተከሳሽ ላይ
ወንጀሉ
በ1997 ዓ.ም ሥራ ላይ የዋለውን የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 684/1/ እና 7/ለ/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከላይ በተመለከቱት ከባድ የወንጀል ድርጊቶች ከ1998 እስከ 2004 ዓ.ም ድረስ ለመንግስት መከፈል የሚገባውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ብር 1,384,683.67 /አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰማንያ አራት ሺህ ስድስት መቶ ሰማንያ ሶስት ብር ከ67/100 ሳንቲም/፤ የገቢ ግብር ብር 3,859,605.26 /ሶስት ሚሊዮን ስምንት መቶ አምሳ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ አምስት ብር ከ26/100 ሳንቲም/ ከግብርና ታክስ ስወራ የተገኘ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ በማቅረቡ በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀመው ከወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ የሙስና ወንጀል ተከሷል።

89ኛ ክስ በ2ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 417/1/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የህግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ ሆኖ ሲሰራ በለገጣፎ ከተማ በካርታ ቁጥር L/X/L/D/3139/00 በስሙ ተመዝግቦ በሚገኘው የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ላይ የመኖሪያ ቤት ዲዛይን እንዲያሰራለት 23ኛ ተከሳሽን በመጠየቅ ተከሳሹም በጥያቄው መሰረት የመኖሪያ ቤት ዲዛይኑን በማሰራት ዲዛይኑ የተሰራበትን የአገልግሎት ዋጋ በድምሩ ብር 23,000.00 /ሃያ ሶስት ሺህ/ እ.ኤ.አ በ18/10/2012 እና በ06/04/2013 ለተከሳሹ የከፈለለትና ተከሳሹም ይህንኑ ጥቅም ያለምንም ክፍያና ተገቢ ምክንያት የተቀበለ በመሆኑ በፈፀመው ዋጋ ያለውን ነገር ያለክፍያ ወይም ያለበቂ ክፍያ ማግኘት የሙስና ወንጀል ተከሷል።

90ኛ ክስ በ23ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 428 ላይ የተመለከተውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ በ89ኛ ክስ ላይ በተመለከተው ሁኔታ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የህግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ ለሆነው 2ኛ ተከሳሽ በለገጣፎ ከተማ በስሙ ተመዝግቦ በሚገኘው የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ላይ የመኖሪያ ቤት ዲዛይን እንዲያሰራለት በጠየቀው መሰረት የመኖሪያ ቤት ዲዛይኑን ካሰራለት በኋላ ዲዛይኑ የተሰራበትን የአገልግሎት ዋጋ በድምሩ ብር 23,000.00 /ሃያ ሶስት ሺህ/ በራሱ ወጪ የከፈለለት በመሆኑ በፈፀመው ዋጋ ያለውን ነገር ያለክፍያ ወይም ያለበቂ ክፍያ መስጠት የሙስና ወንጀል ተከሷል።

91ኛ ክስ በ24ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 808/ሀ/ ላይ የተደነገገውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ የጦር መሳሪያ አያያዝና አጠቃቀም ደንብ ተከትሎ ፈቃድ ከሚሰጥ አካል አስፈቅዶ መያዝና መጠቀም ሲገባ ከሚመለከተው ፈቃድ ሰጪ አካል ሳያስፈቅድ የመኖሪያ ቤቱ በ21/12/2005 ዓ.ም በፍ/ቤት ትዕዛዝ ብርበራ በተካሄደበት ወቅት፡-
1ኛ/ የውግ ቁጥር 473955 የሆነ ታጣፊ ክላሽ ጠመንጃ፣ 2ኛ/ የውግ ቁጥር 2306 የሆነ ባለ ሰደፍ ክላሽ ጠመንጃ፣
3ኛ/ የውግ ቁጥር ኤፍ.ኤ 990 የሆነ ኡዚ ጠመንጃ 4ኛ የውግ ቁጥር 22009411 እስታር ሽጉጥ፣
5ኛ/ አንድ የጭስ ቦምብ ከነፊውዙ እና 6ኛ/ በርካታ የተለያዩ ጥይቶችን ይዞ በመገኘቱ
በፈፀመው እንዲይዝ ያልተፈቀደለትና ፈቃድ የሌለው የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት ወንጀል ተከሷል።

92ኛ ክስ በ24ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 419/1/ሀ/ እና /ለ/ ላይ የተደነገገውን መተላለፍ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከግንቦት ወር 1983 ዓ.ም ጀምሮ መስሪያ ቤቱን እስከለቀቀበት የካቲት ወር 2005 ዓ.ም ድረስ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የውስጥ ደህንነት ሰራተኛ በኋላም አማካሪ ሆኖ ሲሰራ ከብር 1600 /አንድ ሺ ስድስት መቶ ብር/ እስከ ብር 6000 /ስድስት ሺህ ብር/ ያልተጣራ ወርሃዊ ደመወዝ ይከፈለው የነበረ ሲሆን ከዚሁ ህጋዊ ገቢው ጋር የማይመጣጠን፤ በአዲስ አበባ ከተማ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 17 ቀበሌ 25 ክልል ውስጥ በካርታ ቁጥር ሊዝ ዕጣ 8155/94 በኖርቴክ ቁጥር 992478 በተሰጠው 175 ካ.ሜትር ቦታ ላይ የገቢ ምንጩ ሊያሰራው የማይችለውን ለጊዜው ግምቱ ያልታወቀ G+3 ዘመናዊ ህንፃ ቤት ሰርቶ በወር 50 ሺ ብር እያከራየ በመገኘቱ በፈፀመው ምንጩ ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ ይዞ መገኘት የሙስና ወንጀል ተከሷል።

93ኛ ክስ በ24ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 407/1/ሀ/ እና /2/ ላይ የተመለከተውን መተላለፍ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የውስጥ ደህንነት ኃላፊ ሆኖ በሚሰራበት ወቅት የተሰጠውን የስራ ሀላፊነትና ስልጣን በግልፅ ተግባር አላግባብ በመገልገል በመንግስት ጥቅም ላይ ጉዳት በማድረስ የማይገባ ጥቅም ለራሱ ለማግኘት በማሰብ፣ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 17 ቀበሌ 25 ክልል ውስጥ በርካታ ቁጥር ሊዝ ዕጣ 8155/94 በኖርቴክ ቁጥር 992478 175 ካ.ሜትር ቦታ በህጋዊ መንገድ ተሰጥቶት እያለ በዚሁ ቦታ ላይ ቤት ለመስራት ፕላንና የግንባታ ፍቃድ ወስዶ በሚሰራበት ወቅት ከ1996 እስከ 2003 ዓ.ም ድረስ ስልጣኑን ተገን አድርጎ ከተሰጠው ቦታ ጎን የሚገኘውንና የሊዝ ግምቱ 2,923,267.50 /ሁለት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሃያ ሶስት ሺ ሁለት መቶ ስልሳ ሰባት ብር ከ50/100/ የሆነ 375 ካ.ሜትር የመንግስት ቦታ አጥሮ በመያዝ ቤት የገነባበት በመሆኑ በፈፀመው በስልጣን አለአግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል ተከሷል።¾

ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ የዛሬ ኦክቶበር 23 ዕትም

9 Comments

  1. the fascist ethnicist woyane will continue to eliminate the willing serevants like melaku fanta until all are dead.

  2. We are not better than them, we are not doing better than them, we are not united so we are lost too; at least we don’t even talk cross over ethnicity.

  3. What to they wait for? had it been they found such a kind of huge facts and figures for the genuine journalists of Ethiopian, the court would have been immediately decides 100 years in jail or life time.

  4. This is what Weyane looks like at least. All of this thieves were the part of Weyane for long time and when they dissagree their friends exposed them. I’m glad that I never trusted and liked Weyane leba……

  5. TPLF is out to tarnish the image of Melaku Fenta as they could not find any evidence they came up with this allegation of Adultery with a woman of three children Woyanes knew Ethiopians hate ZEMUT that is why they accuses Melaku for sleeping with a married woman.
    The only crime of Melaku was standing against Corrupted Tigrians who smuggled goods with out paying taxes and became rich over night
    Sorry for Melaku he fall on the mouth of vengeance Tigrians

    • @Daniel, althought it is difficult to say at this time that the minister committed crime, the cases brought against him are valid in context of many civil codes. It remindes us general David Petreus’s case. The difference would be the authentisity of evidence in Mr Melaku’s case. But again, there is another case in here that some amount of money that his alleged woman should have paid to the state is exempted. Dont you think this allegation constitute corruption? Also I don’t think the race card applies here because many of cellmates are of Tigri origin. Just my thought:)

  6. If wizero mekedas open her legs melaku Fante got the right to dip his dick in her.the married woman willing to fuck him,so what?this is fuckn bullshit,if I meet a woman which I like and willing to fuck,I will fuck her regardless her marriage status.plus her husband should thanks me for take care of his woman.And look at the guy,he is handsome,any woman will open her legs for him any time.his got straight nose,defetea hair,fair skin,probably good maresha……perfect man

Comments are closed.

Previous Story

ስብሃት ነጋ በመርሳት ችግር (ዳመንሺያ) በሽታ ተጠቂ እንደሆኑ ተገለጸ

black lion hospital
Next Story

ጎበዝ ምንድን ነው ነገሩ? – ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ለ7 ሰዓታት በመብራት እጦት ሥራ አቁሞ ነበር

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop