ሰበር ዜና – በምዕ. ወለጋ በቤተ ክርስቲያን ላይ በሚፈጸመው ግፍ ፓትርያርኩ መንግሥትን አሳሰቡ

የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ጉዳዩን በጥብቅ ይነጋገርበታል
በመንግሥት ባለሥልጣናት ስለሚፈጸሙ በደሎች ከአህጉረ ስብከት የሚቀርቡ አቤቱታዎች የፍትሕ አካሉን አፋጣኝ ውሳኔ ያገኙ ዘንድ ቅ/ሲኖዶሱ ግፊት እንዲያደርግ አጠቃላይ ጉባኤው ዐደራ ጥሎበታል
አህጉረ ስብከት ያቀረቧቸውን የአስተዳደር፣ የፍትሕና የጸጥታ አካላት በደሎችና ተጽዕኖዎች አጣርቶ መፍትሔ የሚሰጥ÷ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት፣ ከሃይማኖት ተቋማት ጉባኤና ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የተውጣጣ ኮሚቴ እንዲዋቀር አጠቃላይ ጉባኤው በአቋም መግለጫው ጠይቋል
‹‹ይህ ዐይነቱ ጊዜ የማይሰጠው ችግር ወደ ሌላ ከመዛመቱ በፊት አፋጣኝ መፍትሔ ማግኘት አለበት፡፡›› /የ፴፪ኛው አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የአቋም መግለጫና የውሳኔ ሐሳብ/
‹‹ድርጊቱ የመቻቻልን ሕግ እያፈረሰ ነው፤ በአካባቢው ያለው መንግሥታዊ አስተዳደር ሊያስብበት ይገባል፡፡›› /ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ/

በምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት በቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ ባለው ፈታኝ ችግር በአካባቢው ያለው መንግሥታዊ አስተዳደር ሊያስብበት እንደሚገባ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አስጠነቀቁ፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ማሳሰቢያውን የሰጡት የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ከጥቅምት ፬ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ጀምሮ ለሰባት ቀናት ሲያካሂድ የሰነበተውን ፴፪ኛ ዓመታዊ ስብሰባው ዛሬ፣ ጥቅምት ፲ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ባጠናቀቀበት ወቅት ባሰሙት የመዝጊያ ንግግር ነው፡፡

‹‹በምዕራብ ወለጋ ዐይን ያወጣ፣ ይሉኝታ የሌለው ግፍ እየተፈጸመ ነው፤›› ያሉት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በካህናትና ምእመናን ላይ፣ በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚፈጸመው ግፍ ‹‹በዚያ አካባቢ መንግሥት አለ ወይ ያሰኛል?›› በማለት ነው በአስተዳደር፣ የፍትሕና የጸጥታ አካላት የሚፈጸመውን በደልና ተጽዕኖ የገለጹት፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የምንታገለው ለስርዓት ለውጥ ነው'' ፋኖ አበበ ሙላቱ

‹‹ድርጊቱ የመቻቻልን ሕግ እያፈረሰ ነው፤›› ያሉት ፓትርያርኩ በአካባቢው ያለው የመንግሥት አስተዳደር ሊያስብበት እንደሚገባ በቃለ ምዕዳናቸው አስጠንቅቀዋል፤ በጉዳዩ ላይ ከጥቅምት ፲፪ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ጀምሮ የሚካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በአጀንዳነት ይዞ በጥብቅ እንደሚነጋገርበትም አመልክተዋል፡፡

በሌላ በኩል ባለ36 ነጥቦች የአቋም መግለጫና የውሳኔ ሐሳብ በማውጣት ዓመታዊ ስብሰባውን ያጠናቀቀው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ፣ እንደ ምዕራብ ወለጋ ባሉ አህጉረ ስብከት በቤተ ክርስቲያን ላይ እየተከሠቱ ያሉ ችግሮች ፈታኝ መኾናቸውንና በቤተ ክርስቲያን የልማትና የመጠናከር ጥረት ላይ ተጽዕኖ ማድረሳቸውን በአቋም መግለጫው ላይ በአጽንዖት አስፍሯል፡፡ የምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከትን ሪፖርት በአብነት የጠቀሰው መግለጫው፣ በሀገረ ስብከቱ፡-

በየትምህርት ቤቱ የሚማሩ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የኾኑ ወጣቶች እምነታቸውን የሚያስለውጥ ዘዴ በመጠቀም ቅስቀሳ የማካሄድ፤
በጠመንጃ አፈ ሙዝ እያስፈራሩ የድብደባ ወንጀል የመፈጸም፤
በቤተ ክርስቲያን ስም የተተከለውን የዕጣን አዙርና የዓመታውያን በዓላት ማክበርያ ቦታዎችን እየነጠቁ ለሌላ እምነት ተከታዮች አሳልፎ የመስጠት፤
የተሠራውን ቤተ ክርስቲያን ለማፍረስ ሙከራ የማድረግ፤
ባልተጠበቀ የትንኮሳ መንገድ እየተጓዙ እስከ ነፍስ ግድያ የሚያደርስ ከባድ የወንጀል ድርጊት በእምነታችን ተከታዮች ላይ እንዲደርስ የማድረግ፤
ከባድ የወንጀል ድርጊት በሕገ ቤተ ክርስቲያኗ በቃለ ዐዋዲው የቤተ ክርስቲያናችንን መተዳደርያ ደንብ ላይ የተቀመጠውን ድንጋጌ ይልቁንም ሕገ መንግሥቱን እንደሚጥስ አመልክቷል፡፡ የሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት በጉዳዩ ላይ የሕግ ክትትል እያደረገ መኾኑ ቢታወቅም፣ ይህ ዐይነቱ ጊዜ የማይሰጠው ችግር ወደ ሌላ ከመዛመቱ በፊት አፋጣኝ መፍትሔ ማግኘት እንዳለበት አሳስቧል፡፡ በመኾኑም ቅዱስ ሲኖዶስ በምልአተ ጉባኤው፣ በምዕራብ ወለጋ ሀ/ስብከት የተከሠተውንም ኾነ ከሌሎች ተመሳሳይ ችግር ካለባቸው አህጉረ ስብከት የሚቀርብለትን አቤቱታ በመቀበል በሚመለከተው የፍትሕ አካል እንዲያስወስን ታላቅ ዐደራ ጥሎበታል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ለትምህርት ጥራት ልዩ ትኩረት በመስጠት ዕውቀት መር ትውልድ ለመፍጠር ይሰራል

የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ‹‹የሃይማኖት መቻቻል›› በሚለው የአጠቃላይ ጉባኤው መርሐ ግብር ላይ ‹‹የብዝኃነት አያያዝ፣ አክራሪነት/ጽንፈኝነት ዝንባሌዎቹና መፍትሔዎቹ›› በሚል ርእስ በሦስት ተወካዮቹ አማካይነት ሰፊ ገለጻ ማቅረቡን ያስታወሰው የአቋም መግለጫው፣ ‹‹በሃይማኖት መቻቻል ዙሪያ የደረሰውና እየደረሰ ያለው ጥፋትና ጉዳት በማስረጃ የተደገፈ ኾኖ ሲቀርብ ጉዳዩ በሚመለከተው የፍትሕ አካል እየተመረመረ እንደሚወሰን፣ በሌላም በኩል እንደ አሁኑ የቤተ ክርስቲያኒቱን ህልውና የሚፈታተን ችግር ሲያጋጥም በኢትዮጵያ የሃይማኖት ጉባኤ በኩል እየቀረበ መፍትሔን ማግኘት እንደሚችል›› በተወካዮቹ መገለጹን አትቷል፡፡

በዚሁም መሠረት ክትትሉ እንዲቀጥልና ለችግሮቹ እልባት እንዲደረግላቸው÷ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት፣ ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተውጣጣ ኮሚቴተዋቅሮ ጉዳዮቹ እንዲጣሩና የመጨረሻ መፍትሔ በአስቸኳይ እንዲሰጣቸው ይደረግ ዘንድ ቅዱስ ሲኖዶስ የአፈጻጸም ውሳኔ እንዲሰጥ ጉባኤው በክፍተኛ ድምፅ ጠይቋል፡፡

http://haratewahido.wordpress.com/

3 Comments

  1. Well, Well,, The patriarch is now started talking!!! Why? Because the Protestants are taking away his followers. This is a power struggle, where the hell they have been all this time? The percentage of Protestants have increased from nothing to 20% in the past 20 years. The previous illegal patriarch was nothing but the main enemy of the church and the current one is a memeber of TPLF, does anyone rally believe what he is talking about? This is just a political propaganda to get support form the Ethiopina Orthodox Church followers. Aba Mathias was a bishop of Jerusalem when thousands of Ethiopina Christians massacred in Harder, Jimma and in many other towns. Why didn’t he speak out at that time?

  2. @Berhanu Tamiru
    It is important to deal with reality than finger pointing about past.The issue is what we need to do now. If you are a type of man who dreams about past and out of touch with the reality then go head with your dozen complains.

  3. Not yet. God will not accept Eli’s and his Childers service. First of all reading, writing graduating from theology universities or colleges or having the name priest, deacons pastor, Professor, or doctor behalf of Almighty God did not bring anything. All churches on the planet Earth are spiritual demons church it doesn’t belong to almighty God the God of Israel. Never. Never who cares Demon is Demon . What shall we do now? Tell us you employee you hired business men who you marchandizing by the name of God. God is the past, present and forever so why now …….? Funny religious on Earth. Where do we find like those fathers? Sick of it

Comments are closed.

Share