ለትምህርት ጥራት ልዩ ትኩረት በመስጠት ዕውቀት መር ትውልድ ለመፍጠር ይሰራል

244544166 6725697637448150 1101479595057771660 n
“በኢትዮጵያ ለትምህርት ጥራት ልዩ ትኩረት በመስጠት ዕውቀት መር ትውልድ ለመፍጠር እንሰራለን” ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ባዋቀሩት ካቢኔ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።
ከሹመታቸው በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ “በኢትዮጵያ የትምህርት ተደራሽነትን ለማስፋትና ጥራቱን ለማስጠበቅ በልዩ ትኩረት ለመስራት ተዘጋጅተናል” ብለዋል።
በተለይም በትምህርት ስርዓቱ ላይ የሚታዩ መሰረታዊ የጥራት ችግሮችን ለይቶ “መፍትሔ መስጠትና የዜጎችን ህይወት ማሻሻል ተቀዳሚው ተግባራችን ይሆናል” ብለዋል ሚኒስትሩ።
በኢትዮጵያ የትምህርት መስክ “እውቀት መር ትውልድ ለመፍጠር ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን” ብለዋል።
”የዚህን አገር ትምህርት በመሰረታዊነት መልኩ መቀየር የምንችልበትና ጥራቱን አሁን ካለበት በጣም በከፍተኛ ደረጃ የወደፊቱን ዕውቀት መር የሆነ ኢኮኖሚ ሊያግዝ የሚችል አዲስ ትውልድ በሰፊው መፍጠር አለብን” ሲሉም ገልጸዋል።
የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከቶች ቢኖሩም በአገርና በህዝብ ጉዳዮች ያለ ልዩነት መስራት ግዴታ መሆኑንም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ አሁን የተጋረጠባትን ፈተና እንድታልፍ ከፖለቲካ ልዩነት በላይ በአገር ጉዳይ አብሮ መቆም እንደሚጠይቅ ጠቅሰዋል።
የአገር ሉዓላዊነትና ቀጣይነት ጉዳይ ሚዛን የሚደፋ በመሆኑ “አገርን ከችግር ማሻገር የሁላችንም ሃላፊነት ነው” ሲሉ ገልጸዋል።
የተፎካካሪ ፓለቲካ ፓርቲ አመራር አባላት በተለያዩ ሃላፊነቶች መሾማቸው የኢትዮጵያ ፖለቲካ “በመተመማን ላይ የተመሰረተ ትብብር ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑን በተግባር እያሳየ ነው” ብለዋል።
የፖለቲካ አመለካከት ልዩነቶች እንዳሉ ሆነው በአገር ጉዳይ ግን በጋራ መቆምና ችግሮችንም በጋራ መፍታት የጋራ ሃላፊነት መሆኑን ተናተናግረዋል።
(ኢዜአ)

8 Comments

 1. እኔ የሃበሻው ፓለቲካ ጭራሽ አይገባኝም። ጠ/ሚሩ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ስልጣን መስጠቱ ማለፊያ ሃሳብ ሆኖ እያለ አሁንም ያለ ማቋረጥ የሚያላዝኑ የውጭና የውስጥ እናውቃለን ባዪች ምን እንደሚፈልጉ የሚረዳኝ አልሆነም። ለአሥር ጊዜ ተሰብስቦ ያለምንም ስምምነት የተበተነው ተመድ እንዲህ በአጭር ጊዜ ውስጥ በተደጋጋሚ በአንድ ሃገር ጉዳይ ሲሰበሰብ ይህ የመጀመሪያው ነው። በአሜሪካ እየተገፋ የሚንደፋደፈው ተመድ ጥርስ አልባ የሆነ ለሃያላን መንግስታት ሃሳብና እይታ ብቻ እሺ ባይ ለመሆኑ ያለፈውም ሆነ የአሁኑ ተግባራቸው ያመላክታል። በተመድ ሥር በልዪ ልዪ ስም የተዋቀሩት የበጎ ተግባር ድርጅቶችና ሰራተኞቻቸው ሁሉ በሃገሮች ጉዳይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ጣልቃ የሚገቡ ለመሆናቸው ሥራቸው ይመሰክራል። እኔ ግን ብዙ የማልረዳው የውጭ ሃገራትን ባህሪ ሳይሆን የሃበሻው የእርስ በርስ ጥልፊያና መሻኮት ነው። ለምሳሌ ኤርሚያስ ለገሰ፤ ሃብታሙ አያሌው፤ መ/ር ዘመድኩን በቀለና ቴዎድሮስ አስፋው የመሳሰሉት ሰዎች የሚያካፍሉን ሃሳቦች ሁልጊዜ አፍራሽ መሆናቸው ያስደነግጠኛል። ማንም መንግስት በአንዲት ሃገር ውስጥ ሙሉዕ የሆነ የለም። ሁሉም በጉደልት የሚንቀሳቀስ ነው። ዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን ከመጣ በህዋላ የተደረጉ ለውጦችን ለማየት አለመቻል ግራ አጋቢ ነው። አዎን ሰዎች ይገደላሉ፤ ይፈናቀላሉ፤ ይራባሉ፤ ይሰደዳሉ ሌላም ብዙ የፍትህ ችግሮች ይታያሉ። ግን የዚህ ሁሉ መንስኤ የጠ/ሚሩ መንግስት ነው ብሎ ማሰብ እብደት ነው። ሰው በስራው ይመዘናል። እሳትን በዚህና በዚያ እየጫሩ የሚያናክሱን የትህነግ ሃይሎችና አጋሮቻቸውን እንዴት እነዚህ ጸሃፊዎች መኮነን ተሳናቸው? ደግሞስ የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስቴር መሆን ችግሩ የቱ ላይ ነው? የትላንት የኦነግም ሆነ የሌሎች ተፎካካሪ ድርጅት አባላት በፓርላማውና በልዪ ልዪ ስልጣን ውስጥ መካተታቸው እሰይ ያሰኛል እንጂ እንዴት የተረሳና የተቀበረ የፓለቲካ ቆሻሻን ሰው እየቆፈረ እገሌ እኮ እንዲያ ነበር አሁንም ነው ተብሎ ይወራል? ሰው በባህሪው ተለዋጭ ነው። ያኔ የነበረውን የፓለቲካ እይታ ዛሬ ላይኖረው ይችላል። ቢኖረውስ ተቻችሎ ለመስራት ከመረጠ የዚያን ፓለቲከኛ ስም ካለፈ ታሪኩ ጋር ነገሮችን በማያያዝ ጭቃ መቀባቱ ለማን ይጠቅማል?
  የሃበሻው ፓለቲከኞችና እኛ ብቻ እናውቃለን የምንል የዘርና የቋንቋ ሰካራሞች ቆም ብለን ልናስብ የሚገባን ነገር ቢኖር የአንድ ቤት እየተቃጠለ የሌላው ቋሚ ይሆናል ብሎ ማሰብን ነው። አብሮ ተደጋግፎ ለመኖር የማይፈልግ ህብረተሰብ ፈራሽ ነው። ዛሬ በአፋርና በአማራ ክልል ዘራፊው፤ ገዳዪና የእርሻ በሬ እያረደ የሚያበላው ወያኔ ትግራይ ውስጥ የተለማመደውን የግፍና የአመጽ ተግባር ነው እያዘነበ ያለው። የትግራይን ህዝብ ዋሻው አድርጎ መጡብህ እያለ በማስፈራራት እንድንተራረድ የሚያደርገን ለራሱ ጥቅምና ስልጣን ነው። የትግራይ ልጆች ከዚህ ድርጅት ራሳቸውን አላቀው በራሳቸው ህሳቤ ለመኖር እስካልተነሱ ድረስ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚያንፏቅቅ የፓለቲካ ወረርሽኝ በመሆኑ ጉዳቱ ሰማይ ጠቀስ ነው። ባጭሩ ሃገሪቱ እልፍ ችግር ያለባት፤ ህዝቦቿ በተለያየ ሃሳብና እይታ ለዘመናት የተሞኙ በመሆኑ አሁን ያለውን እድል ተጠቅሞ ቀጣዪ የፓለቲካ እይታና የምርጫ ውድድር ከፍ ያለ ደረጃ እንዲደርስ የየግላችን አስተዋጽኦ ማድረግ እንጂ ሃዘን በሌለበት ለቅሶ፤ ዘፈን በሌለበት ዳንኪራ መምታት እብድ ያሰኛል። አሁን ጠ/ሚሩ ላዋቀሩት መንግስት ጊዜ በመስጠት ከየት ተነስተው ወዴት እየወሰድን እንዳለ ለማየት ጊዜ መስጠት አስፈላጊ ነው። በሆነ ባልሆነው የፓለቲካ መቦጫጨቁ ይቁም። በቃኝ!

 2. ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ Congrats!! እንኩሃን አንተ በርካታ ዓመታት በትምርት ስራ ላይ ያሳለፈ ይቅር ምንም እውቀት የሌላቸው የፓርቲ ታማኞች ተመድበው ትምህርት ሚኒስቴርን የሚያክል ለአገር ዕድገት መሰረት የሆነ የትምህርት ተቋምን በይስሙላ ሲመሩ ነበር፡፡ የፓርቲ ስራ የሚሰራበት ተቋም ስለነበረ የትምህርት ጥራት በጣም የወረደበት ሻጥርን ሙስና ሲሴርበት የነበረ ተቋም ነበር፡፡ ምንአልባት ከሃይለስላሴ ዘመን እና በተወሰነ መልኩ ደርግ አገዛዝ በኃላ ገለልተኛ ሰው ለዚህ ሚኒስቴር ኃላፊነት ቦታ ሲመደብ የመጀመሪያ ነው፡፡ ለከውጪ አገር ልምድ ያለቸውን በማከል ፕሮፌሰሩ ስራው ሊያቅታቸው ባይችልም ከስር የሚመደቡ ምክትል ሚኒስቴሮች እንዲሁም የዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንቶችም ፍፁም ለለውጥ ሊጥሩ የሚችሉ አና ሚኒስትሩን ሊያግዙ የሚችሉ መሆን አለባቸው ተቋማቱም ሊፈተሹ ይገባሉ፡፡
  በቀጣይ ሚኒስቱሩ ሊያደርጓቸው የሚገቡ ለመጠቆም ያህል፣
  1. በምክትል ሚኒስቴር ማዕረግ፣ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንቶች እና ሌሎች አግባነት ባለቸው ስራ ኃላፊነት መደቦች ላይ እውቀትን፣ ልምድን እና ተነሳሽነት መሰረት ያደረገ ምድባ እንዲደረግ ማድረግ‹
  2. በመንግስት አጠቃላይ የ10 ዓመት ፕላን መሰረት ከዚህ በፊት የነበሩ ዕቅድና አፈፃፀሞችን በአስቸኳይ መገምገም መከለስ
  3. ቀጣይ Strategy plan መቅረፅ ወይም ያለውን በመፈተሸ መከለስ፡፡ ጥራትን መሰረት ባደረገ መልኩ output, outcome & impact ላይ ያተኮረ ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልጋል፡፡
  4. ያለውን የድርጅት መዋቅር መፈተሸና አግባብነት ያለው ምድባ ማድረግ፣
  5. ተቋማት ዲግሪና ሰርተፊኬት አለአግባብ የሚሰጡበት እንዳይሆን ሲስተም መዘርጋት፡፡ ሙስናና እና የግል ተጠቃሚነትን የሚዋጋ ስርዓት መዘርጋት፡፡ ሙስናና የሚጠየፍ culture መፍጠር/ጊዜ ሊወስድ ቢችልም/ ተጠያቂነትንም መዘርጋት፡፡
  6. የፈታና ስርቆትን 12 ክፍል መልቀቂያ ጭምር ማስቀረት እና ለዩኒቨርሲቲ የሚመደቡ ተማሪዎች ፍፅሙ ፍላጎታቸውን እና ውጤታቸውን መሰረት ባደረገ መልኩ እንዲመደቡና የዝምድ እና ሙስና ስራን መዋጋት፡፡ ይህ እንዲፈፀም System መዘርጋት ለዚህም አቅጣጫ በማስቀመጥ ከስር ያሉ ኃላፊዎች ስራቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ማድረግ፡፡ የአብይ አስተዳደርም በቅርብ ማገዝ አለበት፡፡
  7. ለዚች ደሃ አገር ከአጠቃለይ ህዝቡ 70% ወጣት እና productive work force በሆነባት አገር በትምህር ሂደቱ ላይ ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልጋል፡፡ ሁሉም በወሬ የሚያሳልፍብትን ጊዜ ትቶ ለለውጥ መጣር አለባት ምክንያቱም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መልኩ ቢያንሱ ልጆቹ የዚህ ሂደት ተጠቃሚ እና ተጎጂ ስለሚሆኑ፡፡ አንዳንዱ በተሻለ ትምህርት ቤት እና በህዝብ ሃብት ውጪ አገር ልኮ ማስተማር ቢችልም/ይህ መቼም ይቀራል ተብሎ ቢገመትም/
  ስለዚህ ለለውጥ ሁሉም በመነሳት ፕሮፌሰሩን ሊያግዝ ይገባል፡፡ ስንት ዓመት ይህቺ አገር በወሬ፣ የፖርቲ ሹመት፣ የዘር ሹኩቻ ወዘተ ታመሰች፡፡ ሁሉም ነገር በቃ ሊባል ይገባል፡፡ ሰራዊቱ እና ህዝቡ ለአገር መስዋትነት እዛህ ሲታገል እዚህ ያለው በመስራት ለአገሩ አስተዋፅኦ ሊያደርግ ይገባል፡፡ በጊዜ ወይም ሰዓት ላይ ያለውም ሙስናና ብክነትም ሊፈተሸ ይገባል፡፡ ማን መንግስት መ/ቤት ነው በሰዓቱ ገብቶ ባለጉዳዩን የሚያስነግድ እና ስራውን የሚወጣ፡፡ ቢያንስ 30 ደቂቃ ዘግይቶ መግባት እና ቀድሞ መውጣት እንዲሁም ከገቡ በኃላ ፈጥኖ ስራ አለመጀመርም እንዲሁም በመሃል መግባት መውጣት ሰዓት ማባከን የተለመደ ነው፡፡ መንግስት ይህን ሁሉ ነገር መፈተሸ መ/ቤቶችም ውስጣቸውን መፈተሸ አለባቸው፡፡ ስንት ችግር አለ፡፡ ለስሙ እኮ የፀረ-ሙስና ኮምሽን ተብሎ በተቋም ደረጃ አለ Functional ባይሆንም፡፡ ስሊዚህ ገና ብዙ ስራ አለ፡፡
  ለማንኛውም መልካም የለውጥ እኛ የስራ ጊዜ ለምኒሰትሩ እና ለሁሉም ለለውጥ ሊሚጥሩ ሚኒስቴሮች፡፡ እስከዛሬ የነበረው መጥፎ ጠባሳ ይበቃል፡፡
  ኢትዮጵያ ለዛለለም ትኑር!!

 3. ስንት ነው ደሞዝ ሚከፍሉሽ?ኤርሚያስ ለገሰ፤ ሃብታሙ አያሌው፤ መ/ር ዘመድኩን በቀለና ቴዎድሮስ አስፋው የመሳሰሉት ሰዎች የሚያካፍሉን ሃሳቦች ሁልጊዜ ልክ ናችው ልክ እንዳንተ ጥገኛ አደሉም በራሳቸው ነው ሚተማመኑት አልያም አይከፈላቸዉም አንተ ..።

  • እንዳንተ ያሉ ወስላቶች ናቸው አሁን ላለንበት ችግር ያደረሱን። በእድሜ ዘመኔ ጥሬ ግሬ ከማገኘው ሌላ የመንግስት ተቀጣሪ ወይም ተላላኪ ሆኜ አላውቅም። ያው የተሳዳቢ ነገር በገደል ላይ ፈረስ እንደመጋለብ ሆኖብህ እንጂ! ሁልጊዜ የፓለቲካ ኡኡታ እረፍት የለሽ የስድብ ጋጋታ በመሰንዘር ለመሰማት መሞከር እብደት ነው። የጅላ ጅል ነገር አንድን á‹­á‹ž አንድን አንጠልጥሎ እንደሚባለው። በጆኒያና በኬሻ መካከል የስም እንጂ የይዘት ልዪነት የለም። ሁለቱም የተሰጣቸውን እቃ ይይዛሉ። የአንተም የላይ ሃሳብ እንዲሁ ነው። መያዣ ብቻ ነህ! የእኔ ችግር ሁልጊዜ የነቀፌታ ጻሃፊዎች ሳያስቡት Doomsayer and Alarmist ሆነዋል። ረጋ ብለው በጎ ነገርንም ቢያካፍሉን መልካም ነው ባይ ነኝ። አቶ ኤርሚያስም ሆነ አቶ ሃብታሙ በህይወት ለመሰንበት የከፈሉትን ዋጋ ጠንቅቄ አውቃለሁ። የእኔ ሃሳብ ሁሌ ያልተነሳን እሳት ሳይነሳ እሳትን በቅጠል የሚለውን እይታቸውን እንጂ በስም ከተጠቀሱት ከአንድም ጋር ችግር የለብኝም። ማንም ምንም ቢሆን ሁልጊዜ ልክ የሆነ ሰው የለም። ለዚያውም በሃበሻው ፓለቲካ?

 4. ይድረስ ለ”ስቱፒድ” ከላይ በተስፋ እና የተስፋ ጭላንጭል (Yetesfa chilanchile) የተሰነዘሩት አስተያየቶች ለወቀሳ የሚቀርቡ ሳይሆን ትምህርት እና አስተዋይነትን የሚያስመዘግቡ ቁም ነገር ያዘሉ አስተያየቶች መሆናቸውን “ስቱፒድነትህ” አስወግደህ ልትቀበልው ይገባል። በበኩሌ አስተያየታቸውን የሰነዘሩት ደሞዝ እየተከፈላቸው ሳይሆን የሚያምኑበትን እና እውቀታቸውን ለሌላው እያከፈሉ ነው ብየ ሳምን፤ እንደአንተ የኤርማያስ ለገሰ፤ ሃብታሙ አያሌው ፍርፋሪ ለቃሚዎች ፤ እንዲሁም አንተ መ/ር ዘመድኩን ብትለውም በበኩሌ ጠላትነህ በቀለ እና ለቲዊድሮስ አስፋው እንደአንተ እግር አጣኢዎች እና ካልሲ አልባሾች አይደሉምና ለትክክለኛ አስተያየታቸው ክብር ስጥ። በተጨማሪም ጌታቸው ረዳ ተከዜ በረሃ አንድ የአይጥ ጉድጓድ እና በርዳታ የሚዘረፍ አንድ ጣሳ የአሚሪካን ስንዴ ዱቄት አይነፍግህምና እዚያው የሰጡህን የስንዴ ዱቄት ቮሚት አድርግ።

 5. ስቱፒድ አይዞህ ክጻፍከው ምንም የሚወጣለት የለም የሚዲያ አርበኛ እይተቧደነ የቴክስት ሚሳየል እየተወራወረ ስለሆነ ወደ ኣእምሮህ ሳታደርስዉ ፈገግ ብለህ እለፈው። የሚገርመው አትሳደብ ብለው ጽፈዉልህ አሻሺለው ሲሰድቡህ ሳይ እኔም ፈገግ ብዬ እልፋለሁ እስቲ ደግ ጊዜ ያምጣ። አለም መጥታ የጎደለውን ትሞላበታለች አይክፋህ።

 6. The argument that tries to justify the very hypocritical, cynical and dangerously deceptive politics of EPRDF/Prosperity as a democratic and legitimate way of doing politics simply because it appointed very few politically dead and morally bankrupt individuals of so called opposition parties is absolutely a political stupidity and moral degradation !

 7. Who is this stupid guy, TPLF ur name is clearly shows how far u stupied u are, no game on politics of Ethiopia rather u pray to to go ur soul either to satenael or ???

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.