December 31, 2017
10 mins read

አቶ ቆራጥ ውሳኔ – ዳዊት ዳባ

Saturday, December 30, 2017

ያለህው በርቀት ሲሆንና የመረጃ ምንጭ ያደባባይ ብቻ ሲሆን የነገሮች አካሄድና በትክክል እንዲገባህና እውነቱን ከውሸት ለመለየት በጣም የተለየ ጥበብን ታሳድጋለህ። ብዙዎቻችን ይህንኑ ነው የምንጠቀመው። ይሰራልም።

ትግሉ የግለሰብ አቋም ከመሆን እርቆ ሄዷል። የግለሰብ ብቻማ አይደለም በድርጅት ስራ አስፈፃሚ ደረጃም ከህዘብ ፍላጎት በተቃራኒ ቆራጥ ውሳኔ በማድርግ እየፎከርክ መግዛቱን ህዘብ ገና ትግሉን ሲጀምር አንዴ አይደለም ደግሞ ደግሞ ያሸነፈው ነው:፡ ደረጃ በደረጃ ሲታይ  ምንም አይነት ውሳኔ ወስኖ ተፈፃሚ ለማድረግ የየድርጅቶቹን አባላት አወንታ ማግኘት አለበት። ወደሗላ መለስ ብለን እናስታውስ ይህን ማለፍ አቅቶት ስንቴ ከላይ የመጣ ውሳኔ “ወደቆሻሻ መጣያ” ተብሎ ተመላሽ እንደሆነ። የአባላት ፍላጎት ከህዘብ ፍላጎት ጋር መመሳሰል ከጀመረ ደግሞ ቆየ። አሁን ደግሞ ትግሉ  የየክልልም ቢሆን መንግስታዊና አልፎም የፓርላማ ቅርፅ ይዟል። ይህንን ሁሉ አለፈ ብንል እንኳ “አቶ ቆራጥ ውሳኔ” ህዘብ አይቶት ቢያንስ ማለፊያ አድርጎ ሊወስደው ይገባል። አለበለዚያ በንጋታው ወስዶ ያደባይልሀል። ኢትዬጵያ ውስጥ ወደሗላ ላይመለስ የተለወጠው ነገር ይሄ ነው።  አገዛዙ አርጅቷል የመግዛት አቅሙን አሟጦ ጭርሷል የተባለው በማስፈራራት አልሰራ ስላላ ነው።

“ አሸነፈ” የሚባል ወያኔ ከዚህ በሗላ ያለም። ላልቆረጠለት ይቁረጥ። ወያኔ ሁለት ምርጫ ነበረው። አንደኛው ለጊዜውም ቢሆን አንፃራዊ ጥንካሬ ወታደራዊና ድህንነቱ አካባቢው አለ ስለተባለ የሀይሉን መንገድ ቁርጦ ሄዶበት እድሉን መሞከር ነበር። ይሄንኛወን መንገድ አስቦት አስቦት የማይሆን ስለሆነ አልመረጠውም።  ሄዶበት ቢሆን ሞቱ ፈጣን። ጦሱም ግን ቀላል አልነበረም። በትንሹ በመቶሺዎች መግደልንና በብዙ መቶ ሺዎች ማሰረን ይሻል። ያም ሆኖ አይሳካም። ሁሉ ነገር ለማፍረስና ከባዶ ለመስራት ትልቅ ሆኖል። ልታፈርሰው ያማይቻልህ አይነት። ሁለተኛው መንገድ አልጋ ላይ ተኝቶ ቁርባን ተቀብሎ፤ ኑዛዜውን አድርጎ ድምፅ አጥፍቶ የማይቀረውን ሞት መሞት ነው።  “ጊዜ መግዛት”  ለማን ይጠቅማል?። የሚል ጥያቄ መጠየቅ ተገቢ ነው። በኔ እይታ ለረጅም አመታት በተደጋገመ ሁኔታ “ጊዜ መግዛት” ለወያኔ ፋይዳ ነበረው። አሁን ግን ለውጥን ለሚራምደው ጠቃሚነቱ ያደላበት ሁኔታ ነው ያለው። ለዚህ ብዙ ምክንያቶች አሉ።

ከዚህ ተነስቶ የኢህአዲግን  የተንዛዛ ስብሰባ ባጭሩ ግም ለግም ተያይዘህ አዝግም ነው ማለት ይቻላል።  እዚህም እዛም ቁምነገር ለወሬ ያህል ተወርቷል። አጀንዳ ጠብቆ ማውራት፤ መደማመጥ ሁሉ አስቸጋሪ ነበር።  ተጨቃጭቀዋል፤ የሚፎክረው ፎክሯል። የሚያስፈራራው አስፈራርቷል። የሚያረጋጋው አረጋግቷል። የሚሸመግለው ሸምግሏል። በሂደቱ አጠቃላይ ያገሪቷን እውነታ አንስተው አይተውታል። መፍትሄ ብለው ስልጣኑን መልቀቅ ድረስ ተጋግተዋል። ታወራና ታወራና። ታዳምጥ ታዳምጥና። ሀሳብ ትሰጥ ትሰጥና። በመጨረሻ ግን ስብሰባ ስለሆነና ማለቅ ስላለበት አለቀ ትላለህ። ሊተገበር በማይችል፤ አቅሙ በሌለህ ሀሳብ ተስማማን ትላለህ። እንዲሁ በህዝብ ተቀባይ ልታደርገው በማትችለው እንደውም ደፍረህ ህዝብ ፊትና አባላት ፊት ይዘህው ለመሄድ በማትችላቸው አሳብ ተሳማማን ብለህ ትወጣለህ። ይህ ለሁሉም ድርጅቶች ነው። ሊሆን የሚችለው ይህው ነው። ጨርሰው ሲወጡ በተምታታ ስሜት ውስጥ ሆነው ነው። ባንድ በኩል ነገ ስብሰባ ስለሌለ እፎይ የማለት ነገር አለ። በሌላ በኩል የደቀቀ ሞራል። የቀፈፈ ስሜት። አንዳንዱ የማይቀረውን የስርአቱን ሞት ብቻ አይደለም የራሱን ሞት ሁሉ ቁልጭ ብሎ ሊያየው ይችላል። አሸናፊነትም ተሸናፊነት የለውም። ብቻ ምክንያቱ በማይገባቸው የመጨረሻ ተጠላልተውና ተፀያይፈው ይወጣሉ።

ከስብሰባው ውጪ ለነበረ  ጠልፎ ሲያዳምጥ ካልነበረ ማን ምን አቋም እንዳራመደ፤ ማን ሲባሽር እንደነበርና ማን ማንን እንደከዳ ለማወቅ አይቻልም። ባደባባይ ተቃውሞ አሰምቶ የተመለሰ ሁሉ አሸናፊ ነው ባይባልም ተቃውሞ እንደወጣ የቀረም ሁሌ  አሸናፊ አይደለም። እዛው ሆኖ መታገል ፍቱን እንደሆነ ግን ተሞክሮ የተረጋገጠ ነው። በዛ ላይ የዚህ አይነት መላ ምቶች ብዙ ጊዜ የተሳሳቱ ሆነው በሗላ መታዘብ ችለናል። አንድ ነገር ግን በድጋሚ አሁንም መታወቅ ያለበት አሸናፊ ሊሆን የሚችል “ወያኔ”  የለም። ከዚህ በሗላ መቼምም አይኖርም።

በሌላ በኩል ደግሞ አሸናፊ እንጂ ተሸናፊ የትኛውም ድርጅት ለወያኔ እድሜ አይሆነውም። ተቃዋሚዎችን ሙልጭ አድርግው ሲያጠፉ “እነዚህ ሰዎች እብዶች ናቸው ወይ በሗላ ስልጣኑን ላማስረከብም ለመሻሽም እኮ  ያስፈልጋሉ። በተወሰነ ደረጃም የህዝብ ተቀባይነት ሊኖራቸው ይገባል” እያለ አጥብቆና ደጋግሞ የሚያማርር ሰው አውቃለው”። ይህ ሰውዬ ወያኔ ነው እንዴ! እል ነበር።  ምን እያለ እንደሆነ የገባኝ በቅርብ ነው።

እነዚህ አጋር ድርጅቶች ህዝብ ማን እንደነበሩ ስለሚያውቃቸው እንኳን ተሸንፈው  አሸናፊ ሆነውም ቀላል አይደለም። ከነሱ ከሚቋጨው የትኛው አይነት ስምምነት ይልቅ ከህዘብ መሪዎች ከነመራራ ጋር ባነሰ የሚያደርገው ስምምነት ተቀባይ ለማድረግ ቀላል ነው። አገርንም  ማረጋጋትም ሆነ ዘላቂ ጥቅምና  ድህንነታቸውን ለማስጠበቅ የተሻለ ነበር።

ችግሩ ያስፈሪ ሰውም አይመስለኘኝም። አሁን ያሉት ያላስፈሩ በምን ታምር ነው ከዚህ የባሱ አስፈሪዎችን መፍጠር የሚቻለው። ግንባር ላይ ባለ  ምልክት በሉት። በአረመኔነት፤ በገደሉት ብዛት፤ በጦረኛነታቸው፤ በያዙት የስልጣን ቦታ፤ ባሰቃዩት ንፁሀን ብዛት፤ ባከማቹት ሀብት…..ተዘርዝሮ አያልቅም።  ችግር የሆነው  አቶ ቆራጥ ውሳኔ ሳይሆን ውሳኔውን ዝም ብሎ የሚቀበል፤ አጋር ፤ተከታይና ህዘብ ዛሬ ላይ አለመኖሩ  ነው።

ፅፌ ከመልቀቄ በፊት ኢህአዲግ ስብሰባውን አስመልክተው የፃፉትን አነበብኩት። ሀሳቤን ሊያስቀይረኝ አልቻለም። ሰለዚህ ይህን ፅሁፍ መጀመርያ ባሰለሁት መልቀቁን መርጫለው። በተስማሙበት የወጣ መሆኑን እንድጠራጠር አድጎኛል። ፉከራ በዝቶበታል። ጉራ ብቻ ሆኖብኛል።

 

 

2 Comments

  1. ህወሀት ላለፉት 17 ቀናት ቀን ቀን ከሎሌ ድርጅቶቹ ኦህዴድ እና ብአዴን ጋር ሌሊት ሌሊት ደግሞ ከእነ ስብሀት ነጋ እና ጌታቸው አሰፋ ጋር ጥልቅ ስብሰባ ያደርግ ነበር፡፡ እነ ገዱ እና ለማ የሚያቀርቡትን ሎጂክ ሲያዳምጥ ውሎ ሌሊት ማርከሻውን ሲያበጅ ያድራል፡፡ በመሆኑም ህወሀት የደረሰበት የመጨረሻ አማራጭ በእጁ ያለውን ወታደራዊ ኃይል አሟጦ መጠቀም እና ማደናገሩን መቀጠል መሆኑን ከሥራ አስፈጻሚ ስብሰባው መግለጫ መረዳት ይቻላል፡፡ ለዚህም ማስረጃው፡-
    1/ መግለጫውን ከማወጁ በፊት በመከላከያ ሠራዊቱ እና በክልል ፖሊሶች ያለውን እምነት ስለአጣ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች የትግራይን ሚሊሺያ የፌዴራል ፖሊስ እና የመከላከያ ዩኒፎርም አልብሶ ማስገባቱ እና በተለይ በኦሮሚያ ሰፊ የእስር ዘመቻ መጀመሩ ነው፡፡ ከዚህም ሌላ በድፍረት የትግራይ ሚሊሺያዎችን የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይል መለዮ አልብሶ የክልሉን መሪዎችን ለማስግደል መንቀሳቀሱ እየተሰማ ነበር፤
    2/ ኢህአዴግ/ህወሀት በመግለጫው የሁሉም እህት ድርጅቶች ከፍተኛ አመራሮች ግምገማ አድርገው መሪዎቻቸውን እንዲበውዙ የሚያስችል ውሳኔም አሳልፏል፡፡ በዚህም መሰረት ገዱ አንዳርጋቸውን በአለምነው መኮንን፣ ለማ መገርሳን በኩማ ደመቅሳ ወይም አባዱላ ገመዳ የመተካቱ ሂደት የማይቀለበስ የህወሀት አቋም መሆኑን መረዳት ይቻላል፣ ከስብሰባው መጠናቀቅ በኃላ እነ ለማ እና ገዱ ዝምታ ውስጥ መሆናቸው ነገሩ ከአቅማቸው በላይ ስለመሆኑ ማስረጃ ነው፡፡ ለማ፣ ዓብይና እና ገዱ ወደፊት የሚጠብቃቸው እስር ወይም ሞት መሆኑም ይነገራል፤
    3/ ህወሀት በዚህ የመጨረሻ የአገዛዝ ዘመኑ ሊያሳካቸው ከሚፈልጋቻቸው ነገሮች መካከል ዋናው የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ በስፋት በግል አካውንቱ ማዞሩን መቀጠል ሲሆን በቀሪው ጊዜ የአገሪቱ የገንዘብ ክምችት ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሩ ሥር ይሆናል፡፡ ለዚህም ማስረጃው ጥቅምት 30 ቀን 2010 ለደህንነት ምክር ቤቱ ስብሰባ በቀረበው ጽሁፍ ተራ ቁጥር 1.4 ላይ አንዳንድ ኢንቬስተሮች እና ባለሀብቶች ገንዘባቸውን ወደ ውጭ እሸሹ እንደሆነ ማብራራቱ ነው፡፡ እነዚህ ኢንቬስተር ተብየዎች ወይም ባለሀብቶች የህወሀት ሰዎች መሆናቸው ጸሀይ የሞቀው ጉዳይ ነው፣
    4/ የበረከት እና የአባ ዱላ ወደ ሥራ መመለስ ህወሀት ቀደም ሲል አማራ እና ኦሮሞን ለማፈን ስልት የሚቀይሱ ብሩህ የሴራ ፖለቲካ ሰዎችን ማጣት እንደሌለበት ያመለክታል፡፡ እነዚህ ሶዎች ደግሞ ላለፉት 26 ዓመታት ህዝብን ለማደናገር የሚረዱ ስልቶችን ሲቀይሱ ስለቆዩ ምንም እንኳ በረከት በህዝብ የተጠላ ቢሆንም በርከት ያለ ጥፋት የሚያደርስ ስልት ማበጀቱ አይቀርም፡፡

Comments are closed.

Previous Story

መራር እውነቶች። ወያንያዊ ነው። – ዳዊት ዳባ።

Next Story

ፍንክች አይሉም እኛም ፍንክች አንዳንል ያስፈልጋል – ሉሉ ከበደ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop