መራር እውነቶች። ወያንያዊ ነው። – ዳዊት ዳባ።

 

Tuesday, December 26, 2017

ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ያለው መንግስታዊ  (ወያንያዊ) ችግር እንጂ  በህገ መንግስቱ ምክንያት የተፈጠረ ችግር አይደለም። አሁንም ኢትዬጵያ ውስጥ ያለው ችግር ወያንያዊ እንጂ ባለው አከላለል ምክንያት የተፈጠረ ችግር አይደለም። አሁንም ኢትዬጵያ ውስጥ ወያንያዊ ፍጅት እንጂ የእርስ በእርስ ፍጅት የለም። እንደገና አሁንም ኢትዬጵያ ውስጥ ወያንያዊ እንጂ የድንበር ግጭት አይደለም ያለው። የሱማሌ ህዝብ የኦሮሞ ህዝብ ላይ። የአማራ ህዝብ የትግሬ ህዝብ ላይ። የትግሬ ህዘብ የአማራና የኦሮሞ ህዝብ ላይ፤ የኦሮሞ ህዝብ የአማራ፤ የትግሬና የሱማሌ ህዝብ ላይ የሰማነው ሁሉ  በወያኔዎች ቀድሞ የተቀደ የተመራና የተፈፀመ ፍጅት ነው። እውነቱ ይሄ ነው።

ገዢው ፓርቲ ውስጥ ያለው አለመግባባትና ፍጥጫ ዋናው ምክንያት ወያንያዊ የበላይነት አለ የሚልና ባለው የበላይነትን ተጠቅሞ በመንግሳታዊ ስልጣን ጀርባ በመደበቅ ወያኔ ፍጅት በህዝብ ላይ መፈፀሙ ነው።  ዜጋው ሰላማዊ በሆነ መንግድ ለጠየቃቸው መብቱ የሆኑ ጥያቄዎች ባግባቡ መፍትሄ እንዳይሰራላቸው ይህ ክፍል ጋሬጣ ስለሆነ ነው። ይህ ክፍል መንግስታዊ ሽፋንን ተጠቅሞ ከዜጋው ጋር አላስፈላጊ ትግልና ብሽሽቅ ውስጥ ስለገባ ነው። የተፈጠረው ክፍፍል ወያንያዊ የበላይነት መቀጠል አለበት በሚሉና ይህ ነገር በዝቷል ገደብ ሊበጅለት ይገባል ባሉት መካከል ነው።

ኢትዮጵያ ውስጥ አምርሮ መብቱን እየጠየቀ ያለው የኦሮሞ ህዘብ ነው። የወያንያዊውን ስርአት ህልውና አደጋ ላይ የጣለው የኦሮሞ ህዝብ  ነው።  የገዘፈ፤ መራርና የሚሰቀጥጥ መሰዋትነት እየከፈለ ያለውም የሄው ህዘብ ነው። እዚህ ህዝብ ላይ ፍጅት መፈፀሚያ ምክንያት ለመስራት ሲባል በአለፉት ሁለት አመታት በሂደቱ  መሰዋት የተደረጉ  ብዙ ንፁሀን ትግሬዎች፤ አማሮቸ፤ የሱማሌና፤ አፋሮ ዜጎቻችን አሉ። ያም ሆኖ ወያንያዊ ፍጅቱ በወናነት ያነጣጠረው  የኦሮሞ ህዘብ ላይ ነው። ይህ ፍጅት በቀጣይ በሰፊው ሊፈፀም የታቀደውም የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ዜጎቻችን ላይ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ቀኛዝማች አባ ናዳ፤ (ቀኛዝማች ድልነሣሁ ጠንፉ) የኢትዮጵያ ጀግናና ዲፕሎማት - ከኪዳኔ ዓለማየሁ

ሰለጠነ የሚባለው ማህበረሰብ ቀውስን ለቀናትና ለሳምንት መቋቋም እያቃተው የሚፈጠሩ አስገራሚ ክንውኖችን  አይተናል። ታዝበናልም። አገራችን ለሁለት አመታት ባላቋረጠ ቀውስ ውስጥ ነች። መጎዳቱና መጠቃቱ አገራዊ ብቻ አይደለም ለተወሰነው የአገሪቷ ክፍል ህዝብ ጎጆ ቤታዊ ሆኗል። በእርግጥ ለጊዜው ቀውሱ በቀጥታ ያልነካውና የጭካኔው ድላ ያላረፈባቸው እርቀው ያሉ አንዳንድ ዜጎጃችን ችግሩን በቀጥታ ተጎጂ እንደሆነው የማህበረሰብ ክፍል  ሊረዱት አለተቻላቸውም። ጎንደርና አንቦ ላይ ያለ ህዘብ ግን ችግሩ መንግስታዊ መሆኑን ለማየት ችግር የለበትም። አልፎም ባንዳንዶች ሚዛናዊ ነን ለማለት ሲባል ብቻ ጥፋቱን ከፊሉን ለተጎጂውም የማካፈል ነገር አለ። እውነታው ዛሬ መንግስት የሚባለው አካል አገራችን ውስጥ እየፈፀመ ያለውን ለንደን ወይ ኒዬዎርክ ላይ በክፊል ቢፈፀም  እዚህ አዛም በሚፈጠር ትናንሽ ግጭት የሚያልፉት አይሆንም ነበር። አገሮቹ በጠቅላላ ተቃጥለው ይጠፋ ነበር።

ሌላው መዋሸቱ  ለፖለቲካ ፍጆታ ስለተፈለገ ነው። የድንበር፤ የእርስ በእርስ ግጭት፤ ህገ መንግስቱ በሉት ክልሉ ላይ…የቆዩ ፖለቲካዊ ልዩነቶች አሉ፤ እንከኖችና መሻሻል የሚገባቸው እንደገና ሊታዩ የሚጋባቸው ነገሮች የኖሩ ይሆናል። እዚህ ላይ መከራከር ይቻላል። ነግር ግን  አሁን ኢትዬጵያ ውስጥ ካለውና እየሆነ ካለው ነገር ጋር እነዚህ ቁም ነገሮች የቀጥታ ግንኙነት የላቸውም። የቀጥታ ግንኙነት ያለው ከጭቆና፤ ከአድሎ፤ ነፃነት ከመሻት ጋር ነው። የቀጥታ ግንኙነት ያለው ከመንግስታዊ ሽብርተኛነት ጋር ነው። ይህንን አይደለም የአገራችንን የየለት ሁኔታ በቅርበት የሚከታተሉ ፖለቲከኛች ዘፈኞቻችንና ገጣሚዎቻችን ያውቃሉ። በግጥምና በዘፍን ፍፁም አንድ ስለመሆናችንና ስለመዋሀዳችን  ተመንጥቆ ሰማየ ሰማያት ያስቀመጡትን ያህል ግን ወገንታዊ መሆን አልቻሉም። መዝፈን መግጠም ይቻላል የሚሉትን መኖር ግን ለነሱም አሳጭ ሆኗል።  እንደውም በመሀበረሰባችን ውስጥ የሚታየው የወገንታዊነት ደረጃ ጤናማ ከሆነው ደረጃ በታች ነው። አሳፋሪ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት በአበዳሪዎች የዕዳ ወጥመድ ተይዟል!!! ‹‹የጫካው ኢኮኖሚ ምንም ይሁን ምን፣ አንበሣ በፍፁም ሣር አይበላም!!!›› - ሚሊዮን ዘአማኑኤል

እሳት ከሰማይ አውርዶ እንዲቃጠሉ የሚጠየቀውን  ምህላ ስለሚከብድ  እንተወው። አንዱ ገጣሚው ችግሩን ከመንግስት ጫንቃ ላይ ሲያወርደውና ሌላ ቦታ ሲወስደው አብረን እንይ እስቲ።

ባውድማው ላይ እኛን የሚያዋጉን

እዳር ሆነው እኛን የሚሞቁን፤

ቀዩን ከነጭ ከሰርገኛ

ወትሮ የሚለዩ እነሱ መለኞ።  ይህን ላዳመጠ ችግሩ መንግስታዊ አይደለም።

አሳሳቢው  የእስካሁኑ አልበቃ ብሎ ፍጅቱን በቀጣይ በሰፊው ለመፈፀም እቅድ ውስጥ የተገባው ቀላል የማይባል ምን አልባት እውነቱን ቢናገር ፍጅቱን ለማስቆም ይቻለው የነበረ የማህበረሰብ ክፍል እዚህ ጉዳይ ላይ በአመለካከት ደረጃ  የትጋር እንዳለ ስላወቁና መበረታት ስለሆናቸው ነው። ቢመርም ይህ እውነታ ነው።

ሌላው በአገራችን ፖለቲካ ነክ በሆነ ጉዳይ ላይ ለመናገር ሚሚ ስባቱ፤ ዳዊት ከበደ፤ እርእዬትና አማረ አረጋዊ የመሳሰሉት …..አይነቶቹ ብቻ ሲቀሩ። ይህ ይሆን ዘንድ የጋዜጠኞች ፍጅት ስለተፈፅመ ብቻ አይደለም። እውነታው ያንድን ዘር ፍፁም የበላይነት ለማስጠበቅ ሲባል ሁለንተናዊ በሆነ ቀስ በቀስ ሲካሄድ የነበረ መንግስታዊ ሌሎችን የማጥፋት ዘመቻ ስለነበረ ነው። እውነቱ ይሄ ሆኖ ባለበት ተመርጠው የቀሩትን እያዳመጠ ማመን የሚፈልግ ማመን መብቱ ነው።  በምንም መንገድ ሰርዓታቸው የሚጎዳበትን  ነገር የዚህ አይነት ሜዲያዎች እንደማይንግሩን ግን እሙን ነው። ችግሩ ወያንያዊ ነው መቼም አይሉህም።

ዜጋው ግን፤- ክትናንት ዛሬ ነፃነትን የምንናፍቀው ብቻ ሳይሆን ሊኖረው የሚያውቅበት መሆኑን አሳይቷል።  ኢትዮጵያዊነት፤ አንድነትና ፍቅር መቼም ቢሆን ችግር እንዳልነበረ ዳግም አስረግጧል። እፈሩ ሲል ይህ ማንነቴና ኑሮዬ ነው እያለ ነው ያለው።

ዜጋው ግን፤-  ይህ ሁሉ ፍጅት፤  የሚያስተዛዝቡ ሁኔታዎች በበዙበት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይህ ወያኔያዊ ስርዓት ሳይፈርስ ትግሉን ላያቆመው ተማምሎ ሰላማዊ ትግሉን አበርትቶ ቀጥሏል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ግልጽ ደብዳቤ ለሃይሌ ገብረሥላሴ (ከአበበ ገላው)

 

ዜጋው ግን፤-በብዙ ሺዎች ተገለው በሚሊዮኖች ተፈናቅለው፤ በሚሊዬኖች እየተሳደዱ ባለበት  ክህፃን እስከሽማግሌ፤ ከገበሬ እስከ ምሁር ፍጅት ወያንያዊ መሆኑን ያውቃል።  ወለም ዘለም በሌለበት ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ  ይህንኑ ብቻ ይናገራል።

ዜጋው ግን፤- መሰረቱ የህዘብ አወንታ የሆነ የተገደበ ስልጣን ግድ መሆን አለበት እያለ ነው። እኩልነት ላይ የተመሰረተ ዜግነት፤ ነፃ የፍትህ ስርአት፤ ነፃ ፓርላማ፤ ነፃ ምርጫ ይቻላል እያለ ነው።   ከዚህ ያነሰ በጭራሽ አንወሰድም ነው እያለ ያለው። ደግሞ ወደዚህ የሚያደርሰውን ትክክለኛ መንገድ  ነው የያዘው። መዳረሻው ይህ እንደሚሆንና ጉዞው ወደዛ  እንደሆነ ግልፅ ብሎ መታየት በመጀመሩ ይህንን መስካሪው እየጨመረ የሄደበት እውነታ  ሀቅ ነው።

 

 

 

 

 

1 Comment

  1. Ethiopians in DC are living in democratic country , but they are under undemocratic illiterate thugs . ETHIOPIANS MUST EMANCIPATE THEMSELVES FROM THE BONDAGE OF DC THUGS AND HOOLIGANS .

    YOU ARE IN AMERICA , THE LAND OF THE FREE
    SAY NO TO DC HOOLIGANS INTIMIDATION AND BLACKMAIL

    SAY NO TO MERCHANTS OF POLITICS

    ESPECIALLY , OUR ARTISTS MUST OPENLY SAY NO TO OLD ILLITRATE THUGS IN DC AND ENVIRONS

Comments are closed.

Share