14 ዓመታት ተፈርዶበት እስር ቤት የሚገኘው ውብሸት ታዬ የሲኤንኤንን ሽልማት አሸነፈ

(ዘ-ሐበሻ) ታዋቂው የሚዲያ ተቋም ሲኤንኤን (Cable News Network) በየዓመቱ የሚያዘጋጀው የመልቲ ቾይዝ የአፍሪካ ሽልማት ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ተካሄደ። በዚህ የሽልማት ስነስርዓት ላይ በ እስር ቤት የሚገኘው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ አሸናፊ መሆኑን ዘ-ሐበሻ ሽልማቱን በትዊተር በመከታተል ካገኘችው መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

በተለያዩ ዘርፎች ሲኤን ኤን የአፍሪካ ጋዜጠኞችን በየዓመቱ የሚሸልም ሲሆን ከዚህ ዓመት ተሸላሚዎች መካከል ኢትዮጵያዊው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ሽልማቱን ያገኘው Free Press Africa Award በሚለው ዘርፍ ነው።

በእስር ቤት ከ2 ዓመት ከ4 ወር በላይ የሆነው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ይሰራበት በነበረው አውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ላይ ሽብርተኝነትን የሚያበረታታ ጽሁፍ ጽፈሃል በሚል 14 ዓመታት ተፈርዶበት እስር ላይ ይገኛል። የዛሬውን የሲኤን ኤን ሽልማት እርሱ እስር ላይ በመሆኑ ባለቤቱ መምህርት ብርሀን ተስፋዬ እና ልጁ ፍትህ ውብሸት በደቡብ አፍሪካ ኬፕ ታውን ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር በመገኘት መቀበላቸውን ዘ-ሐበሻ በትዊተር በመከታተል ያገኘችው መረጃ ያመለክታል።

ለጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ መታሰር ለሕወሓት/ኢሕአዴግ ደህንነቶች ጥቆማውን በመስጠት ደረጃ ማንን ትጠረጥራላችሁ? እኛ እያጣራነው ያለነው ጉዳይ አለ፤ እናንተ ግን አስተያየታችሁን በአስተያየት መስጫው ያስቀምጡ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ፋኖውን ባለ ጀብዱ ተዋወቁት -   ኃይለ ኢየሱስ አበጀ

17 Comments

  1. ለዉብሸት መታሰር ዳዊት ከበደን እጠረጥራለሁ። ምክንያቱም ከሐገር የወጣበት ሁኔታ እና ከወጣም በኋላ እየሰራ ባለዉ የወያኔ አገልጋይነቱ ነዉ።

  2. ከዳዊት ከበደ ሌላ ማንም ሊሆን እንደማይችል የማይታበል ሃቅ ነው

  3. ይህማ ግልጽ ነው ዳዊት ከበደ ይሆናል የሚል ጥርጣሬ ነው ያለኝ

  4. If D. kebede was clean and innocent he could have worked hard for Wubeshet release, his silence and not to lift a finger makes him guilty as such.

  5. Our heart goes out with his family. Remain strong truth will set our brother, your husband and father, son Wobishet free. Justice will serve its purpose soon.

  6. The Bible has it’s David who slew the giant Goliath, but we have a david who betrays his own friend simply because Wubishet is not from his tribe. The name Judas fits this guy perfectly.

  7. ዘሀበሻን ጨምሮ ወሳኝ የሆኑ ሁሉም ድረገፆች: ኢትዮጵያ ውስጥ ሲታገዱ: አውሬ አምባ ግን ዘና ብሎ ይሰራል። አገር ቤት ያሉ ሰዎችን መጠየቅ ትችላላችሁ።

    ዳዊት ከበደ
    በውብሸት አበደ

Comments are closed.

Share