ፋኖውን ባለ ጀብዱ ተዋወቁት –   ኃይለ ኢየሱስ አበጀ

267956408 3114595192195589 8405850104787358094 nፋኖ አጋዬ አድማስ የተወለደው ምዕራብ አርማጭሆ ነው። ትግሉን የጀመረውም ከ፲፭ (15)ዓመት በፊት በዚያው በአርማጭሆና በጠገዴ ሲኾን በዋነኝነት የትግልን ስልት የተማረው ከጀግናው አርበኛ ጎቤ መልኬ ነው። እርሱም የጎቤ መልኬ ቀኝ እጅ በመባል ይታወቃል። ይዋጓል እንደ ገብርዬ የሚባልለት ግስላ ነው።

የፋኖው መሪ ጀግናው አጋዬ አድማስ አራሽ ነው፤ ለዚያውም እርሻው የለማለት ገበሬ። በጦርነት ጊዜ ደግሞ እሳት የላሰ ወታደር።

በጭና፣ በቦያ ግንባር፣ በዛሪማ፣ በአድርቃይ፣ በደባርቅ፣ በደብረ ዘቢጥና በተለያዩ ዐውደ ውጊያዎች እየተዘዋወረ ታላቅ ጀብዱ ፈጽሟል። በተለይ በደብረ ዘቢጥ የተገኘውን ድል የመራው እርሱ ነበር።

ፋኖ አጋዬ አድማስ “ከመከላከያ በፊት እኛ እንሞታለን፤ ተቆጥሮ የተሰጠንን ሥራ ቆጥረን ነው የምናስረክበው…..” የሚል ባለመርሕ ሲኾን ራሱን ለሀገሩ አሳልፎ የሚሰጥ ቆራጥ ጀግና ነው። የጦርነት ጀግንነቱን፣ ብስለቱን፣ ድፍረቱን፣ ተኳሽነቱን፣ ስልቱን…… የጦር ጓዶቹ ይመሰክሩለታል።

የመከላከያ ሠራዊት አዛዦች “ጓዶችህን መሣሪያ እናስታጥቅልህ” ባሉት ጊዜ በልበ ሙሉነት የመለሰላቸው እንዲህ ሲል ነበር።

“የለም፤ ጓዶቼ የሚታጠቁት ከጠላት ማርከው ነው የመከላከያን መሣሪያ አናባክንም” በማለት ትንታጉ ወደ ጦርነት ዐውድማው እሳት ኾኖ ገባ። ወዲያው እንደ እሳት ይልሳቸው ገባ። ያለውም አልቀረ በርካታ መትረየስ፣ ስናይፐርና ክላሽ በመማረክ ጓዶቹን አስታጠቀ።

የደብረ-ዘቢጡ ጦርነት ጊዜ ባለቤቱ ወልዳ አላያትም ነበርና ወደ ማይጠብሪ ሲመለስ እያት ብለው ለምነውት ነው ያያት። በክርስትናው ጊዜም አልተገኘም። ጀግና ከሀገሩ ጋር በፍቅር ሲወድቅ እንዲህ ነው።

ለዚህ ጀግንነቱ ከኹለት ሳምንት በፊት የጎንደር ከተማ አስተዳደር የዞብል ክ/ከተማ ሥራ አስኪያጅ አቶ ገ/ሚካኤል አየልኝ የመኖሪያ ቤት አስረክበውታል። ባለቤቱና እናቱ አመስግነው ተረክበዋል። እርሱ ግን እዚያው ግንባር ሥራ ላይ ነበረ።

ክበርልን ጀግናችን!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.