ፍትሐዊ ያልሆነ ግብር ተተመነብን ያሉ ነጋዴዎች እርምጃ ተወሰደባቸው

ከነገዱት በላይ የሆነ ወይም ፍትሐዊ ያልሆነ ግብር ተተምኖብናል ያሉ ነጋዴዎች እርምጃ እንደተወሰደባቸው ተገለጸ፡፡ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የክልል ከተሞች፣ ፍትሐዊ ያልሆነ የግብር ተመን እንደተደረገባቸው የገለጹ ነጋዴዎች፣ ተቃውሟቸውን ሱቅ በመዝጋት እና አደባባይ በመውጣት ሲገልጹ እንደነበር ይታወሳል፡፡ የኢትዮጵያ ገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን በበኩሉ፣ የነጋዴዎቹን ቅሬታ እንደሚፈታ ሲገልጽ ቢቆይም፣ በመጨረሻ ግን ተቃውሞ ሲያሰሙ በነበሩ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ሊወሰድባቸው ችሏል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ ግብር እንደተተመነባቸው በመግለጽ ሱቅ እስከ መዝጋት የደረሰ የአድማ ተቃውሞ ሲተገብሩ የነበሩት የመርካቶ ነጋዴዎች የእርምጃው ግንባር ቀደም ሰለባ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከመርካቶ በተጨማሪም በፒያሳ አትክል ተራ፣ ሳሪስ፣ ኮልፌ እና በመሳሰሉት አካባቢዎች በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች የእርምጃው ሰለባ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ነጋዴዎቹ በገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን የተወሰደውን እርምጃ በመኮነን ተቃውሞ ቢያሰሙም ምንም ዓይነት መፍትኤ ሊያገኙ አለመቻላቸውን ለመረዳት ተችሏል፡፡ በነጋዴዎቹ ላይ የተወሰደው እርምጃ የገንዘብ እና የእስር ቅጣት ሲሆን፣ አብዛኞቹ ነጋዴዎች ግን በገንዘብ ቢቀጡም፣ የተወሰኑት ደግሞ በእስር ጭምር እንደሚቀጡ ታውቋል፡፡

ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ በተደረገ የቀን ገቢ ግምት ስሌት መሰረት፣ በነጋዴዎች ላይ የተተመነው ግብር ከፍተኛ እንነደበር በወቅቱ ሲገለጽ ነበር፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ነጋዴዎችም ምሬታቸውን በተላየዩ መንገዶች ሲገልጹ እንደነበርም አይዘነጋም፡፡ በወቅቱ የቀን ገቢ ተመኑ ሲሰራ፣ በነጋዴው ላይ ዋጋ እንደማይጨመር መንግስት አስታውቆ ነበር፡፡ ሆኖም ወደኋለ ላይ ግን ከፍተኛ የግብር ተመን ሲጣል ብዙዎችን አስደንግጦ ነበር፡፡ ከመደንገጣቸው የተነሳ በሽታ ላይ የወደቁ ሰዎች ስለመኖራቸው ታውቋል፡፡ መንግስት፣ የጀበና ቡና በምትሸጥ አንዲት ሴት ላይ፣ የ80 ሺህ ብር ግብር ተምኖ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ ተመኑን ተከትሎ ንዴት የገባቸው ነጋዴዎ፣ ንግድ ፈቃድ እስከመመለስ ደረጃ ደርሰው ነበር፡፡ (BBN)

ተጨማሪ ያንብቡ:  ባህርዳር ዙሪያ ጭስ አባይፓትሮል ተማረከ"ከ30 በለይ ተገደለ"!!
Share