October 6, 2013
1 min read

የጣሊያን ፖሊስ ስደተኞችን ሲቀጠቅጥ የሚያሳይ ቪድዮ (ኢትዮጵያውያንም አሉበት)

8081

የሚከተለውን አሳዛኝ ቪድዮ ይመልከቱ” ኢትዮጵያን ለወረራ መጥቶ በጀግኖች አባቶቻችን ተዋርዶ የሄደው የጣሊያን ሰራዊት ልጅ ልጆች ዛሬ ደግሞ ስደተኛ ዜጎችን ሲቀጠቅጡ የሚያሳይ ቪድዮ በቴሌግራፍ በኩል ወጥቷል። በርከት ያሉ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት ዜጎች ሱዳንን አልፈው፤ የሰሃራ በረሃን አቋርጠው ወደ ሊቢያ ከገቡ በኋላ በመርከብ ተጭነው በረጅም ስቃይ ታጅበው ጣሊያን ይገባሉ። ጣሊያን ሲገቡ ደግሞ እንዲህ ያለው አሳፋሪ ድብደባ ይደርስባቸዋል። ይህ ቪድዮ በቴሊግራፍ መጽሄት  ከተለቀቀ ቆየት ያለ ቢሆንም ሰሞኑን በጣሊያን በስደተኞች ላይ የደረሰውን አደጋና፣ አድኑን እያሉ ሌሎች ጀልባዎች እየተቃጠለች ያለችውን ጀርባ ጥለዋቸው በመሄዳቸው ለበርካታ ዜጎች ሞት ምክንያት የሆነውን አደጋ በማስታወስ በ2011 ዓ.ም የሆነውን ቪድዮውን ይመልከቱና ይፍረዱ። በነገራችን ላይ የዘ-ሐበሻ ጋዜጣና ድረ ገጽ ዋና አዘጋጅ በሰሃራ በረሃና በሊቢያ በስደት ያሳለፈ በመሆኑ ወደፊት ስለመንገዶቹና ኢትዮጵያውያኑ ስለሚገጥማቸው ፈተናዎች የሚያጫውተን ነገር ይኖራል።

5 Comments

  1. እኔ በበኩሌ በኢጣልያኖቹ ምንም አልፈርድም:: እኛ ነን እኮ የሄድንባቸው:: ወደ ሃገራቸው ያለማስገባት ሙሉ መብት አላቸው እኮ በትክክለኛው ስናስበው:: በአለም አቀፍ ደረጃ የፈረመችው የስደተኞች ጉዳይ አስገድዷት እንጂ:: ወገኖቼ ችግሩ ያለው እዛው እኛው ሀገር ነው:: ከኢጣልያኖቹ የበለጠ ሃብት አለን ግን አልተጠቀምንበትም:: ወደ ጥሬ ገንዘብ የተለወጠውን ሃብት ደግሞ ሙሰኞቹ ለግላቸው መንደላቀቂያ አድርገውታል:: ይንደላቀቁ ችግር የለም ግን ከመንደላቀቅ በላይ እያባከኑት ነው:: ዝም ብላችሁ እስኪ በሙስና በአንድ ሰው እጅ ያውም በተራ ባለስልጣን እጅ ተያዙ የሚባሉ በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ብሮችን አስቧቸው:: በዛች ድሃ ሃገር ለአንድ ፕሬዝዳንት በወር 400,000 ቢር የሚያወጣ ቤት ሲከራዩላቸው:: ለሃገር ንብረት ያለማሰብ እንጂ ህጉ ላይ እራሱ እንዲህ አይነት ከሚቀመጥ መንግስት ቤት ገዝቶ ይሰጣቸዋል ቢባል እኮ በጣም በጣም የተሻለ ነው::
    የኢትዮጵያ ስፋት ከጀርመን በሶስት እጥፍ ይበልጣል የህዝብ ብዛት ግን እኩል ናቸው:: ይህ ማለት ደግሞ ኢትዮጵያ ብዙ ልናለማቸው የምንችላቸው ባዶ ቦታዎች አሏት ማለት ነው:: ያንን ደግሞ መንግስት ማረግም አይፈልግም ኢትዮጵያዊው እንዲያለማበትና ለዜጋው የስራ እድል እንዲፈጥርበት አይፈልግም:: በተቃራኒው ግን ለውጭ ዜጎች ያው በነጻ እንደመስጠት ያክል መሬቱን ይሰጣቸዋል: ትራክተርና ሌሎች ለዚያ ግብአት የሚውሉ መሳሪያዎችን ደግሞ ከታክስ ነጻ እንዲያስገቡ ይፈቅድላቸዋል:: መንግስት እራሱ ደግሞ ያልለሙ ቦታዎችን ከመጠቀም ይልቅ (ያውም ጥቅም ላይ አውሎአል ከተባለ) ስራ ላይ የዋሉ የለሙ ቦታዎችን በማፍረስ ነው ‘አለማሁ’ የሚለን:: ለዚህ ጥሩ ማሳያ ደግሞ የዋልድባን ጥንታዊውን ገዳም ማፍረሱና ከመንግስት ምንም አይነት ድጋፍ የማይፈልጉትንና በራሳቸው አልምተው የሚተዳደሩ ዜጎችን (መነኮሳትን) ከገዳሙ ማባራሩና ስራ አጥ ማድረጉ:: አዲስ አበባ ላይ ብዙ ዜጎች ንጹህ ላባቸውን አንጠፍጥፈው የሰሩትን ቤቶቻቸውን ማፍረሱ:: ባልተጠና እቅድ እራሱ የገነባቸውን በቢሊየኖች በሚቆጠሩ ብሮች የሰራውን የመንገድ ስራ ምንም አገልግሎት ሳይሰጥ ማፍረሱ: ወዘተ ከብዙዎቹ የሀገር ንብረት አውዳሚነቱን ከሚያሳዩን ጥቂቶቹ ናቸው::

    ከላይ እንደጠቀስኩት ሀገሪቱ ብዙ ያልለሙ ቦታዎች አሏት ያንን ለውጭ ዜጎች በነጻ እንደሚያድለው ሁሉ ለሃጋሩ ተወላጆች ቢሰጥና ልክ ለውጭ ዜጎቹ የስራ መኪኖቻቸውንና ሌሎችንም እቃዎቻቸውን ከታክስ ነጻ እንደሚያስገባላቸው ያንን እድል ለዜጎቹ ቢሰጥ የሃገሬው ዜጋ ብዙ መስራት ይችላል ለብዙዎችም ብዙ የስራ እድል መፍጠር ይችላል:: የሚያገኘውን ንብረት ደግሞ በሃገሩ ገበያ ላይ ነው የሚሸጠው:: ያ ደግሞ ሌላው ጥቅም ነው:: እየሆነ ያለው ግን ከዚህ በተቃራኒ ነው:: ንጹህ ላብህን አፍስሠህ ባገኘኸው ንበረት እራሱ ጠመንጃ ይደቀንብሃል:: ጠመንጃ ደቅኖብህ ያፈርስብሃል:: አይሆንም ብለህ መከራከር አትችልም በራስህ ንብረት:: ብትከራከር ግን አሸባሪ ተብለህ እስር ቤት ትወረወራለህ:: ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የሚሰደዱት ሃገርቤት ውስጥ ያለው ይህ አይነት ድርጊት አስመርሯቸው ነው:: የምንሰደድባቸው ሀገሮች ደግሞ እኛን የመቀበል ግዳጅ የለባቸውም:: ”ባለቤቱ የናቀውን ….” እንደሚባለው:: ኢጣልያኖቹን ከመታዘብና በነሱ ላይ ጥርስ ከመንከስ ይልቅ ስልጣን ላይ ያለው መንግስት ለህዝብ እንዲሰራ ጥረት ማረግ ነው:: በተናጠል ሳይሆን ሁሉም ዜጋ በአንድነት ለአንድ አይነት ጥያቄ መጮህ ነው ያለበት:: ወዴት እንጩህ? ወደ ውጭ መንግስታት አይደለም እነሱ የኛን መበላላት ስለሚፈልጉ ከነሱ መልስ አይኖርም:: የመጀመሪያው አማራጭ ሁሉም ዜጋ ጥያቄው አንድና አንድ ብቻ ሆኖ ስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች ወደልባቸው እንዲመለሱ መማጸን:: ስልጣን ላይ ያሉት ልበ ደንዳኖች ናቸው እሺ አይሉም ትሉኝ ይሆናል እኔ ግን በዛ አልስማማም ምክንያቱም መጀመሪያ እኛም እኮ አንድ አልሆንም:: የአንዱ ህመም ለሌላው ሊሰማው ይገባል:: የጎረቤቴ ቁስል የኔም ቁስል ሊሆን ይገባል:: የዘርና የሃይማኖት ልዩነቶቻችንን እናስወግድ:: ሁላችንም አንድ ኢትዮጵያውያን መሆናችንን ብቻ ለአእምሯችን እናሳምነው:: በነጻነት በሃገራችን ላይ የምንኖር ከሆነ ሌሎች ሁሉ ይኖሩናል ሁሉንም ነገር በነጻነት ማከናወን እንችላለን:: ባሁኑ ሰአት ኢትዮጵያ ውስጥ ወደ 33 የፖለቲካ ፓርቲዎች አሉ መሰለኝ:: ይህ ግን ለምን አስፈለገ? እንደዚህ አይነት ብዙ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያስፈልጉት እኮ well established የሆነ system ላለው ሀገርና በየተወሰነ term ስልጣን የሚለቅ ክፍል ሲኖር ያንን ቦታ እኔ መረከብ እችላለሁ በሚባልበት ሁኔታ ነው:: እኛ እኮ በመጀመሪያ ደረጃ system የለንም:: ስልጣን ላይ የሚወጣው ፓርቲ ከሁለት term ወይም የፖለቲካ ፓርቲዎቹና ህዝቡ ተስማምቶ ከሚያስቀምጠው የጊዜ ገደብ በላይ ስልጣን ላይ እንደማይቆይ እርግጠኞች ስንሆን ብዙ ተወድዳሪ ፓርቲ የሚያስፈልገው:: በመጀመሪያ ግን ሁልካችንም አንድ እንሁን ሁሉም ፓርቲ ወደ አንድ ይምጡ ህዝቡንም አንድ ያድርጉት:: ከዛ ደግሞ ስልጣን ላይ ያለውን በፍቅር ወደኛ እናምጣው:: አሁን በሃገር ደረጃ ያለው ህግ ባብዛኛው ጥሩ ነው:: ችግር ተግባር ላይ 1% እንኳን አይተገበርም:: ስለዚህ ትንሽ ማስተካከያ ካስፈለገ ህጉ ላይ ያ ተደርጎበት ሀገሪቱን ወደመታደግና ዜጎችን ከስደትና መከራ ወደመታደግ ብንገባ መልካም ነው እላለሁ:: ኢጣልያ ሲገቡ በመርከብ ያለቁትንና ሌሎችንም በየቦታው በስደት ምክንያት ህይወታቸው እያለፈ ያለውን ወገኖቻችንን ነፍሳቸውን በገነት ያሳርፍልን:: ፈጣሪ ስደት በዚህ ይብቃችሁ ይበለን ለዚህ ደግሞ ከኛ የሚጠበቀውን ማድረግ ይኖርብናል:: ሁላችን በፍቅር ከሆንን መንግስትን እዛ ፍቅር ውስጥ ማስገባት የማንችልበት ምንም ምክንያት የለም እነሱም ሰዎች ናቸውና:: በቅድሚያ ልዩነቶቻችንን አስወግደን እርስ በርሳችን እንተባበር:: አንድ ወገናችን ሲበደል በጭፍን መንግስትን ከመደገፍ ይልቅ ለተበደለው ወገናችን ከልባችን እንዘንለት::

  2. አፍሪካውያን በተለይም ምስራቅ አፍሪካውያን ለምን ይሰደዳሉ? ለሚለው ጥያቄ መልሱ አጭር ነው:: ሃብታቸውን ገንዘባቸውን ፍለጋ ነው መልሱ::
    ______________________________________________________________
    የፍሪካውያን ሃብት የሚገኘው ባአውሮፓ ባንኮች ውስጥ ነው:: ማን እዛ ወሰደው ለሚለው ጥያቄ አሁንም መልሱ አጭር ነው:: ምእራባውን ከአፍሪካ አምባገነኖች ጋረ በመመሳጠር የአፍሪካውያንን ሃብት በየቀኑ እየወሰዱት ነው::
    _________________________________________________________
    ስለዚህ ሃብትን ወስዶ ስደተኛን አልቀበልም ማለት አይቻልም::

  3. be wegen sekaye ye medeset, be wegenu sekaye ye politica fejotawen yemetekem tewuled yalewu…diaspora becha newu…..plz bewegen cheger polotica ateseru……toxic diaspora ye Ethiopia ezeb telek cheger nachu….ke toxic diaspora ye terefen benor,,,gay and lisbi becha newu….ye hager telatocheee

  4. Dear “ethiopianreview” host, the fact of the matter is completely different. The migrants you see on this video are about 1500 tunisians who fled their country to lampedusa in 2011 when their country was in complete chaos. Can you please check out the following clip which further elaborates the story: http://www.youtube.com/watch?v=b8XwcnW_iXw
    Please correct the unsubstantiated claim in your report, which states that there were some ethiopians too during this incident. It is completely baseless and fictitious.

Comments are closed.

Previous Story

ግንቦት ሰባት፤ ብርሀኑ፤ አንዳርጋቸው፤ የኤርትራ ነገር? ከተከሌሚካኤል አበበ

semayawi press
Next Story

በጎጃም ከሚያዝያ እስከ ነሐሴ ባሉት ወራት 8 አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል፤ ሰማያዊ ፓርቲ ማብራሪያ ጠየቀ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop