ቴዲ የኩዋስ ሜዳ ልጅ ነው – (ሄኖክ የሽጥላ -ገጣሚው)

/

(ሄኖክ የሽጥላ -ገጣሚው)

ከምን ልጀምር? እንደው ይጨንቃል፤ ደሞ ዝም ቢሉት ያንቃል። አሁን ይሄን የምጥፈው ለማስተማር ነው ለማካረር? በልጅነቴ አንድ አብሮ አደጌ በጣም የሚወዳቸው እናቱና አባቱ እየተጋጩ ቢያስቸግሩት፥ ሄኒ አሁን አንተ በኔ ቦታ ብትሆን ማንን ትጠላለህ? ብሎ የጠየቀኝ ትዝ አለኝ። ማንን ልጥላ? ለማን አግዤስ ማንን ላውግዝ?
ማንንስ ልውቀስ? ማንንስ ልጥቀስ? ሲደብር።
በእውነትም ይደብራል። ለካ ያራዳ ልጆች ወደው አይደለም ድብርት የሚለውን ቃል የሚያዘወትሩት። እንደነሱ ፍቅር፤እንደነሱ መተሳሰብ፤ እንደነሱ ንጽህናን ማን አውቆት። ለካ ያም እንዳይጎዳ ፤ ይሄም እንዳይከፋው ፈልገው ነው፤ በቃ ተወው እሱ ደባሪ ነው፤ ብለው የሚያልፉት። ምነው ያራዳ ልጅ በሆንኩ።

በPDF ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ተጨማሪ ያንብቡ:  የደብረ ብርሃኑ ስብሰባ ብልጽግና በሰሜን ሸዋ ዞን ጨርሶ እንዳበቃለትና እንደተንኮታኮተ የሚያስተምር ነበር

5 Comments

  1. ሄኖክ በጣም እየቀለደ እያሳሳቀ የሚያስተምር ጽሁፍ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ የምንጋጭበት ምንጩ ወይ አለማወቅ ነው ወይም አንተ እንዳስከመጥከው ከእኔ በላይ ላሳር የሚል ገገማ ነት ነው፡፡ በተለይ የኢትዮጵያን ትግል የጎዳ ይህ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡ በሽታው እንዳለባቸው የገባቸው ሰዋች ፡ በዚህ ጽሁፍ ራሳቸውን ማየት ቢችሉ መልካም ነው፡

  2. Henok
    you not only good poem writer, you written veer good article too. thank you for that. when i read or heard your work we are breathing.

  3. Thank you yeshitela .i think tamage would learn more from his mistake.if tamage think to make Weyanes happy by attacking teddy Afro he is reading from the wrong book.unles he purposely do it to destruct esat the people media from thier wonderful job.we know that tamage is one of the guys who are supported by the weyane right hand alamoudi .but using the people media and doing fever for weyane is immoral.any attempt of attacking teddy Afro will have big ramification.tamage stop being wolf in the sheep clothing.esat is not etn which is used to be weyane friendly media and as a result shutdown immediately .

  4. ሄኖክ ጽሁፍህ መልካም ጥበብ የተሞላበት መካሪ ነው፡፡ ታማኝ እንደስሙ ታማኝ ምርጥ የኢትዮጵያ ልጅ ነው፡፡ ታማኝ የዋለልን ውለታ ብዙ ነው፡፡ በቅርቡ ያለውን ብናይ ኢሳትን ኢሳት እንዲሆን ትልቅ አስተዋጽዎ ያረገ ነው፡ የኢሳት ተደማጭነት እና ተወዳጅነት ሌት ተቀን ደከመን ሰለቸን ሳይሉ በሚሰሩት ምርጥ ጋዜጠኞች ላይ የተመሰረተ ቢሆንም፡ ሲንገዳገድ ለማቆም ግን ታማኝ ህዝቡን ገንዘቡን እንዲሰጥ ድርሻውን እንዲወጣ በማስረዳት በማነቃቃት ብሎም ገንዘብ በመለመን ደም ስሩ እስኪገተር እግሩ እስኪቀጠቀጥ ያለመታከት እያገለገለን ያለ ታማኝ ወንድማችን ነው፡፡ ሁላችንም ከኢትዮጵያዊ እጅ ለአገር የሚሰጥ ገንዘብ መለመን እንዴት ያለ አሰልቺ ስራ መሆኑን እናውቃለን፡፡ ታማኝ ግን በስለት የወለደችው ልጅዋ የታመባት እናትን ይመስል፡ ለኢሳት ለምኖዋል ተማጽኖናል ሀላፊነታችንን እንድንወጣ አስገንዝቦን ኢሳትን አቁሞልን ለህዝባችን መተንፈሻ አስገኝቶዋል፡፡ ውለታውን የኢትዮጵያ አምላክ በዘር ማንዘሩ ይክፈል፡፡ ቴዲ ! ቴዲ ደሞ ምርጥ የኢትዮጵያችን ስጦታ ነው፡ ቴዲ በያስተሰርያል ኢትዮጵያዬ አይነጋም ወይ ሌቱ እያለ የዘላለም ጸሎት እና ምልጃ ሰቶናል ፡፡ እንዲሁም መሪዋቻችን ሲፈቱ ዘመን ጀመርነው ይኽው ታርቀን ብሎ ባይሰሙትም እኛ ስንጣላ ጠላት ይስቃል ብሎ የመከረ የልጅ አዋቂ ነው ፡፡እንዲሁም ሰው ራሱን ለገንዘብ አሳልፎ በሚሰጥበት ዘመን ገንዘብንም በክብራቸው የማይለውጡ ቆራጦች እንዳሉ ያስተማረ ጅግና ነው፡፡ በተጨማሪም የማንም ለፍዳዳ ሰላይ ነፍሰ ገዳይ በሚኒሊክ ታሪክ ሲያላግጥ ሚኒሊክ የማንም መሀይም መቀለጃ መጻፍ የመጻፍ መለማመጃ በሆኑበት ሰአት ምሁሩ ፈርቶ ሆዱ እየተቃጠለ ዝም ብሎ ባየበት ሰአት ሚኒሊክ ጥቁር ሰው ብሎ የተነቀነቀ ዜማን ከኢትዮጵያ ጫፍ እስከጫፍ የተሰማን ዜማ የሸለመን የክፉ ቀን ደራሽ የብሶት አስተንፋሽ ልጃችን ነው፡፡ ቴዲ በሸመንደፈር አክራሪነትን አብርዶዋል ፡፡ ሄኖክ እንዳልከው የተመረጠ ነው፡፡ አሁንም መድሀኒያለም መርጦት እንኩዋን ኢትዮጵያን አፍሪካን ሊያስጠራ ነው ፡፡ይህ የቴዲ ስጦታ ለእኔ ለአንዲት ከሩቅ ሆኜ ጥበብን ለምረዳ ይህን ያህል ከገባኝ ለታማኝ በመቶ እጥፍ ይገባዋል፡፡ ገብቶትም ምርጥ ዝግጅት ለቴዲ ሰርቶዋል ማየት ለምትሹ ጁን እስራዘጠኝ ያታማኝን ዝግጅት እዩና ተረዱ፡፡ ሄኖክ ደሞ በራስህ የምንወደው የሎሬት ጸጋዬ የሩቅ ነጸብራቁ የሆንክ ደፋር በሳል ገጣሚያችን ነህ፡፡ ሄኖክም እንደቴዲ የክፉ ቀን ደራሽ የሆኑ ግጥሞችህ ግራ በተጋባን ጊዜ የሀበሻ ለቅሶን ለቀህ መጽናናትም መረዳትም ሆነኽናል፡ አንተም እንደቴዲ ከላይ የወደቀብህ ቅባት እንዳለ፡ በኢሳት ፕሮግራም ህዝብ በተሰበሰበበት ሙስሊሙን እና ከርስቲያኑን የሚያያይዝ ግጥም በቅጽበት በመጻፍ የሰጪውን ማንነት አሳይተኸናል፡፡ ሄኖክ እደግልን ተመንደግ፡፡ አሁን በሁለቱ ወዳጆችህ መሀል ድልድይ ሆነህ የናት እና የአባቴ አይነት ጸብ ሆነብኝ ብለህ በፍቅር ሳትወግን ለመምከር መነሳትህ መልካም ነው፡፡ ሶሶታችሁም ለእኛ ብርቅዬ የክፉ ቀን ደራሽ የምንሳሳላችሁ ናችሁ፡፡ ለዘላለም ተያያዙልን አንድነታችሁ ለዘላለም ይጽና፡፡ እናንት ስላላችሁን በጣም ታድለናል፡ እንዲህ ጥበብ በየለቅሶ ቤቱ ራስዋን በሸጠችበት ዘመን ከህዝብ ጎን ቆማችሁ ያኮራችሁን መንፈሳችሁ የተሳሰረ ሶስት ምርጥ ወንድሞቻችን ኑሩልን፡፡አድናቂያችሁ፡፡ ለዘላለም ዘራችሁ ይባረክ፡፡ አሜን!!

Comments are closed.

Share