June 29, 2017
3 mins read

በዛሬው እለት ወገራ ላይ ውጊያ አለ

ከሙሉነህ ዮሐንስ

(ሰኔ 22 2009) ትናንት በላክነው ማስጠንቀቂያ ወያኔ ወደ ሰሜን ጎንደር የተለያዩ ቦታወች ሰራዊት እየላከ ስለመሆኑ ገልፀን ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስበን ነበር። ሰላማዊ ህዝቡን ማሸበር የያዘው ወያኔ የገበሬውን መሳሪያ ነጠቃ ሙከራ ያደርጋል። በዚህ የተበሳጩት ገበሬወች የወያኔን አገልጋይ ሰራዊት ገጥመዋል። ከገበሬወቹ መካከል ዋስትና እንሰጣቹሃለን ምህረት ግቡና በሰላም ኑሩ ብለው ለመሸምገል የሞከሯቸውን ሁሉ የጥቃቱ ኢላማ አድርገው ነበር።

ይህን ጥቃት የመከቱት ገበሬወች ወደ በርሃ ወርደዋል። አስደንጋጭ ምት የደረሰበት የወያኔ ሰራዊት እየተተራመሰ ሲሆን አሁንም ቢሆን ህዝቡ እራሱን በንቃት መጠበቅ አለበት። የግጥሚያውን ልዩ ቦታና የጎበዝ አለቆቹን ስም ከመጥቀስ ተቆጥበናል። በዚህ ግንባር ከተሳተፉት የጎበዝ አለቆች መካከል ባለፈው አመት አምባጊዮርጊስ ላይ ወያኔ በህዝቡ ላይ የፈፀመውን የጅምላ ጭፍጨፋ አፀፋ በመመለስ እጅግ ስመጥር የሆነ ጀግና ይገኝበታል።

ይህ በ እንዲህ እንዳለ ትናንት የሚከተለው መልዕክት ተላልፎ ነበር::

በሰሜን ጎንደር አንባ ጊወርጊስ አካባቢ፣ ወደ ቆላ ወገራ እና እንቃሽ ውስጥ ድረስ ለሚንቀሳቀሱ የጎበዝ አለቆች ሙሉ መረጃ ለመሰብሰብ እና የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ ያስችለኛል በማለት ወያኔ በከፍተኛ ሁኔታ አስቦና ወጥኖ ይበጀኛል ያለውን ዘዴ እየሞከረ ነው።

አካባቢውን ጠንቅቀው ከሚያውቁት እና ታማኝ ናቸው ተብለው በተመረጡ ወታደሮቹ ልክ አርሶ አደር በመምሰል የኮንትሮባንድ ጥይት ሻጭ በማስመሰል ረከስ ባለ ዋጋ እየሸጡ በድብቅ በያዙት ዘመናዊ የኤሌክትሮኒስ መሳርያዎች በመታገዝ ስለላውን ለማድረግ ተልእኮ ተሰጥቷቸው መሰማራታቸው ተደርሶበታል። ትንሽ ቁጥር ያላቸውን ባንዳዎች ሙሉ ለሙሉ የአካባቢውን ማህበረሰብ በሚላበሱ ዘዴ በጭነት በአይሱዚ መኪና ልኳል፡፡ እናም ይህ መልእክት ቶሎ ይተላለፍ።

Go toTop