ገንዳው – በእውቀቱ ሥዩም (አሜሪካ እንደመጣ የፃፈው)

/

እዚህ አሜሪካ – በሀገረ ማርያም – በጊዚያዊ ቤቴ – ጊዚያዊ በረንዳ
ቆሜ ሳነጣጥር
አየሁኝ መንገድ ዳር – ተገትሮ ያለ የቆሻሻ ገንዳ
ዳቦው እንደ ጉድፍ
ወተቱም እንደ እድፍ
ልብሱም እንደ ቅጠል
በገንዳው ከርስ ውስጥ ይረግፋል እንደ ጠል ::
ያሜሪካ መልኳ
አይደለም ህንፃዋ ሰማይ የሚነድለው
አይደለም መንገዷ – እንደ ቆለኛ ቅል የተወለወለው
አይደለም ፖሊስዋ – ዝሆን የሚያህለው
ያሜሪካ መልኳ ጎልቶ የተሳለው
በገንዳዋ ላይ ነው እመንገድ ዳር ባለው
ባገሬ ሰማይ ስር
ሰው ጠኔ ገፍትሮት ሲውድቅ በመደዳ
ያሜሪካ ንስር
ላንዲት ስኒ ሆዱ በጋን እያስቀዳ
እዚያ ማጣት እዳ
እዚህ ማትረፍ እዳ
እዚያ ባዶ መሶብ
እዚህ ሙሉ ገንዳ
ከእለታት አንድ ቀን
በሰማያት እና በምድሪቱ ድንበር
ከእኛ ጎታ አጠገብ የቆሻሻ ገንዳ ተቀምጦ ነበር
የሰማይ አማልክት አላጋጭ ቀልደኛ
“ራበን መግቡን” ስንላቸው እኛ
ብዙ መና ጋግረው ሲያዘንሙ ከሰማይ
የእኛን ጎታ ስተው ከተቱት ገንዳው ላይ::
ከቶ ለምን ይሆን
ያፍሪቃ ህፃናት በደቦ ሚያልቅሱ
የወተቶች አዋሽ – የርጎ ሚሲሲፒ – በበዛበት ዓለም – ጤዛ የሚልሱ
የሹራብ ተራራ – የቡልኮ ጋራ – በበዛብት ዓለም – ጭጋግ የሚለብሱ
የምድር ጠቢባን
ለዚህ ግዙፍ ምስጢር – መልስ አገኝ ብላችሁ – ጠፈር አታስሱ
አሜሪካ ያለው – የቆሻሻ ገንዳ – ግጣሙ ሲከፈት – ወለል ይላል መልሱ::
– በእውቀቱ ሥዩም (September 16, 2013. Maryland | USA)

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሕግ የበላይነት ሳይረጋገጥ መነሳት የለበትም የሚል ተቃውሞ የገጠመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተነሳ

3 Comments

  1. ^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^
    ያን…ቆሻሻ ገንዳ ደግመህ ካገኘኸው እኛ ሀገር ና! በለው!
    ሀገረ ኢትዮጵያ ሰው አመለኛ ነው
    ከሩቅ ወርዋሪ ገንዳው ክፍት አፍ ነው
    አመድና ጫት ሁሌም ቃሚ ነው፤
    የኩሩ ሀገር ልጆች ዕድገትን የናቁ
    በዱር በገደሉ እየሄዱ አለቁ
    ቀለበት ማሳለጫ መንገድ ጠንቅቀው አያውቁ
    ነፈሰም ጎረፈ አይሞቅ አይበርዳቸው
    እሥሩ ይኖራሉ ገንዳው ነው ተስፋቸው፣
    ሰው ቆሻሻ ሲለቅም አንበሳው ሰው በላ
    ይህንን ዕድገት ያለ ሞኝ ነው ተላላ
    ከዚያ ሀገር ገንዳ ጨርቅ ዳቦ ወተት
    በእኛ ሀገር ገንዳ አመድ ወረቀት ጫት
    ጥጋብ በሬድዮ በኢቲቪ ከመንፋት
    አቁማዳ አንግቶ ከልመና ዕድገት
    ሀብታም ከማዳነቅ ድሃን ነው ማበርታት
    ለግል ጥቅምና ዝና ህዝብን ከማባላት
    ሰውን በሀገሩ ክብር ሰጥቶ ማብላት
    ዘረኝነት ጎጠኝነት ይቀበር በገንዳው ሙሉበት
    የእኛን ሀገር ገንዳ ተሞክሮ ካላቸው ኮርጅ በሉት
    መሃይምነት ድንቁርና ነው አፍሪካን የገዛት !!።
    በለው! ከሀገረ ካናዳ በቸር ይግጠመን

  2. I salute! In rememberance; Tens of millions makes a country, Much – a bond of Exs and famtree Walking zipped dudes of mistery; Eden Garden’s folks of Wistry; A wistry of garden, but Eden; Dom of boredom, when is Freedom to come; To the land of Kam and Sem; That of Eve and Adam.

Comments are closed.

Share