የአንጋፋው ድምፃዊ ተሾመ አሰግድ 61ኛ ዓመት ልደት በዓል ተከበረ

/

(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ አቆጣጠር መስከረም 1 ቀን 1945 ዓ.ም የተወለደው ስመጥሩውና ሃገር ወዳዱ ድምፃዊ ተሾመ አሰግድ በሚኒሶታ 61ኛ ዓመት የልደት በዓሉ አድናቂዎቹ በተገኙበት ትናንት እሁድ መስከረም 5 ቀን 2013 ዓ.ም አከበረ።

(ተሾመ የ61ኛ ዓመቱን ኬክ ሲቆርስ)

“አዲስ ዓመት በመጣ ቁጥር ልደቴም ስለሆነ ጭምር ልዩ ትዝታ አለኝ የሚለው” በኢትዮጵያ ስመ-ጥር ከሆኑ ድምጻዊያን መካከል የሆነውና ብዙዎች “ኢትዮጵያዊው ስቲቭ ዎንደር” የሚሉት ተሾመ አሰግድዶ በተወለደ በ5 ወሬ ዓይነ ስውር መሆኑን በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 2 ላይ በሰጠው ቃለ ምልልስ መናገሩ ይታወሳል።
የመጨረሻ አልበሙን ካወጣ 20 ዓመት ያለፈው ይህ ድምጻዊ እስካሁን ስንት ካሴቶችን ሰርተሃል በሚል ጥያቄ አቅርበንለት “ጥቂት ካሴቶችን አውጥቻለው:: ትዝታና ባቲ በሚባለው የሙዚቃ ቅኝት በፊሊፕስ አሳታሚነት በ1960ዎቹ አንድ ሸክላ አውጥቼ ነበር:: ከዛ በተረፈ ያልተሳካለት አንድ ካሴት ሰርቼ ነበር:: ከዛ ወዲህ ግን ጅቡቲ ለ5 አመታት ከቆየው በኋላ ከሮሀ ባንድ ጋር በመሆን ‘የኩባያ ወተት”ን ሰራሁኝ:: ይበልጥ ከሕዝብ ጋር ያስተዋወቀኝም ይሄ ሥራ ነው:: በሌላ በኩል ከነራሄል ዮሐንስ; አሰፉ ደባልቄ እና ኬኔዲ መንገሻ ጋር አንድ ካሴት; እንዲሁም ከማርታ አሻጋሪ; በዛወርቅ አስፋው እና ኤልያስ ተባባል ጋር በመሆን አንድ ኮሌክሽን ሰርቼ ነበር:: በራሴ በኩል 2ኛውን ሙሉ ካሴቴን “ደርባባዬ’ን አውጥቼ ነበር:: ብዙም በሕዝብ ዘንድ አልገባም:: ግን አልፎ አልፎ ሰዎች ያውቁታል::” ሲል ከዚህ ቀደም ለዘ-ሐበሻ መናገሩ ይታወሳል።

የድምፃዊው ተሾመ አሰግድ 61ኛ ዓመት የልደት በዓል በሚኒያፖሊስ ቲስ ፕሌስ ሲከበር የድምፃዊው አድናቂዎች ተገኝተው የነበረ ሲሆን ድምጻዊውም በተለያዩ ጣ ዕመ ዜማዎቹ ልደቱን ሊታደሙ የመጡትን አድናቂዎቹን ሲያዝናና አምሽቷል። ተሾመ በሃገራችን ስለ እውነት ከቆሙ ጥቂት አርቲስቶች መካከል ግንባር ቀደሙ ነው።
http://youtu.be/sqqirjOxp0U

ተጨማሪ ያንብቡ:  ‹‹ጋዜጠኞች ከእስር ቤት እንደወጡ በአንድ የፖለቲካ ድርጅት ጥላ ስር ሲሰባሰቡ መመልከት ያሳዝናል›› ዳዊት ከበደ [ጋዜጠኛ]

1 Comment

  1. የተሼን 60ኛ አመት በሰዊድን ከኔ ቤተሰብ ጋር ነበር ያክበርነው።አሁን ደግሞ በዚህ ሁኔታ መከበሩ በጣም አስደሰቶኛል።ተሼ እንኩዋን ደስ ያለህ ይሄንን ያስተባበራችሁትመ ምሰጋና ይድረሳችሁ።

Comments are closed.

Share