ከሙሉነህ ዮሐንስ
ቃጠሎ አንድ
አዲስ አበባ
ልዩ ስሙ ጃክሮስ በሚባል አካባቢ አ.አ ውስጥ በሚገኘው እጅግ ግዙፍ በሆነው የወያኔ ኤፈርት ሁሉን አቀፍ አስመጪና መላኪያ መጋዘን እና ፋብሪካ ክፍል በተቀነባበረ ሴራ በተለኮሰ እሳት በትንሹ እስከ 40 ሚሊዎን ብር የሚገመት ንብረት ወደመ፡፡ በርካቶችን ለእስራት እየዳረገ ነው፡፡
ቃጠሎ ሁለት
ወልቃይት
440 ኩንታል ጥጥ ወልቃይት ላይ ተቃጠለ። ጥቃቱ የወያኔን የንግድ ጥቅሞች ላይ ጉዳት ለማድረስ ነው የሚሉ ዘገባዎች ወጥተዋል።
ቃጠሎ ሶስት
ባህር ዳር
አመልድ (እየተጣራ ነው) እየተቃጠለ ነው የሚል መረጃ አሁን መጣ። ይህም የወያኔ/ብአዴን ተቋም መሆኑ ነው።
እናም በወያኔ ላይ አዲስና የተቀነባበረ ጥቃት እየተፈፀመ ከሆነ መቆሚያ አይኖረውም። ምክንያቱም ጥቃቱን ለማድረስ መስዋእትነት አያስከፍልም:: ጉዳቱ ግን ከፍተኛ ነው። ወያኔ ደግሞ ገንዘብ በጣም ታፈቅራለች…ይህ ያንኮታኩታቸዋል…ወየው ለማረት ወየው ለኤፈርት…
በሌላ በኩል በባህርዳር የተከሰተውን ቃጠሎ ተከስቶ ከፍተኛ ተኩስ ማምሻውን እየተሰማ መሆኑን ከስፍራው የመጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ::
ዝርዝር መረጃዎች እንደደረሱን እናቀርባለን
ግንቦት0 እኔነኝ ያደረኩት ለማለት እየተቁነጠነጠ ነዉ። ዘዴውን ኮለኔል ፍፁምን መላበለን እያሉ ነው። ምናልባትም ጋድ ኮለኔል ፍፁም በአዳዲስ የግንቦት0(tpdm)ፎቶዎች ብቅ ሌል ይችላል።