በመደብ ትግል የሚያምኑ በመደብ ትግል ይደመሰሳሉ – ሸንቁጥ አየለ

ይሄን ጽሁፍ ከማንበብዎት በፊት ቀንጨብ አድርገዉ የሚከተለዉን ቪዲዮ ይመልከቱት::

https://www.facebook.com/FITIH1/videos/1734771353446693/?hc_ref=NEWSFEED

-ሁለት መደቦች አሉ::አንዱ የህዉሃት መደብ ነዉ::ሌላዉ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ መደብ:: የዚህ ጽንሰ ሀሳብ እና የርዕዮተ አለም ማጠንጠኛዉ አቢዮታዊ ዲሞክራሲ ነዉ::

-እነዚህ ሁለት መደቦች ተቃራኒ ናቸዉ::በፍጹም አብረዉ ሊኖሩ አይችሉም::አጥፊና ጠፊ ናቸዉ::
-የግድ አንዱ መደብ ገዥ እና የበላይ በመሆን ሌላዉን መደብ መሰባበር እና ማጥፋት አለበት::ህዉሃት የሚያደርገዉ ይሄንኑ ነዉ::ህዉሃት የመደብ ትግል ላይ ነዉና ተቃራኒዉን መደብ ከማጥፋት ለደቂቃ አይቦዝንም::
-የህዉሃት የጦር ሀይልና የፖሊስ ሰራዊት የህዉሃት መደብ ጠባቂ ነዉ::ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ደም የተቃባ ሀይል ነዉ::

አንዳንዱ የመደብ ትግል የማይገባዉ አንዳንድ ከወያኔ መደብ ተመዘዉ የሚወጡ ሰበዞችን እንደ ተቃዋሚ እየቆጠረ አብሮ ይሮጣል::ወይም ከነሱ ጋር አብሮ ሊደራጅ ከፍ ዝቅ ይላል::

-እዉነታዉ ግን አንድ ነዉ:: በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የመደብ አስተምህሮት የተጠመቀ እና ብሎም አቢዮታዊ ዲሞክራሲን ተቀብሎ አንድ ሰሞን እንኳ አብሮ የሮጠ ሁሉ ያዉቀዋል:: ይሄም ጥሬ ሀቅ የህዉሃት መደብ እና የኢትዮጵያ ህዝብ መደብ አጥፊና ጠፊ መሆናቸዉ ነዉ::አብረዉ አይኖሩም::ህዉሃት ይሄን ቀመሩን የቀመረዉ ገና ፓርቲዉ ሲመሰረት ነዉ::ኢትዮጵያ የምትባል ሀገርን ክዶ እና የኢትዮጵያ ህዝብም የመደብ ጠላት መሆኑን አዉጆ ነዉ::ይሄን ጥሬ ሀቁን በአቢዮታዊ ዲሞክራሲ ጀቡኖ በአደባባይ እየለፈፈ 45 አመታት ሙሉ የህዉሃት መደብ ብቻ ህልዉ ሆኖ መኖር እንዳለበት እያስተማረ ነዉ::
-ለዚህ አቢዮታዊ ዲሞክራሲ ድስኩሩ የሚንበረከኩ ሚሊዮን ገልቱዎች እና አድርባዮች አላጣም:: የወጡበትን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያጠፉለትን እና የኢትዮጵያን ህዝብ መደብ ለመደምሰስ የሚተጉ ብዙ አድርባዮች አፍርቷል::አንዳናዶቹም እስከ ሚኒስቴር ደርሰዉ: ፕሬዝዳንትም ሆነዉ የኢትዮጵያን ህዝብ መደብ በማስጠፋት እና የህዉሃትን መድብ በማለምለም ሂደት ዉስጥ ከተሳተፉ ብኋላ ጉምቱ ተቃዋሚ ነን ይሉሃል::ያኔም እነሱም ወደ ኢትዮጵያ ህዝብ መደብ ገብተዋል እና ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር አብረዉ ይቀጠቀጣሉ:: ካስፈለገ ይራባሉ ወይም ይገደላሉ አለዚያም ይደብደደባሉ:: ወያኔ ይሄን የአቢዮታዊ ዲሞክራሲ መርሁን አንድም ቀን በሚዲያ ከመናገር ቦዝኖ አያዉቅም::
-ምህረት የለም::ርህራሄ የለም::በአቢዮት ሂደት ዉስጥ ምንም ቆሞ ማስተዋል የለም::ተቃራኒዉ መደብ ያለምንም ማመንታት ይቀጠቀጣል:: ተቃራኒዉ መደብ ያለምንም ማመንታት ይደመሰሳል::አሁን ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ መደብ እየደመሰሰ ነዉ:: አሁንም ለ45 አመታት የቀጠለዉ አቢዮት ተቃራኒዉን መደብ መደምሰሱን ቀጥሏል:: እንግዲህ ይሄን ሀቅ የማያዉቅ ፖለቲከኛ ወይም በልቡ ምን ግዴ ብሎ የወያኔን መደብ ተቀላቅሎ የወያኔን መደብ እያለመለመ የኢትዮጵያን ህዝብ መደብ ሲቀጠቅጥ የባጀ የወያኔ አገልጋይም በመጨረሻ ተቃዋሚ ሆኖ ሲሰለፍ የሚገጥመዉ የመደብ ድምሰሳ መከራ አንድ ነዉ::

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሚጠብቀኝ አይተኛም?  (ከአሁንገና ዓለማየሁ)

-በቪዲዮዉ ላይ እንደሚታየዉ ፖሊስ ህዝብ ሲደመሥስ ነዉ::ሆኖም ከዚህ የከፋዉ እና የላቀዉ የኢትዮጵያን ህዝብ መደብ የመደምሰስ ስራ የሚከናወነዉ በሌሎች ስፍራዎች ነዉ:: በስርቤትስ? በሌላ ቦታስ? በኢኮኖሚያዊ ዉሳኔስ? በማህበራዊ እና ተቋማዊ ሂደቶችስ ዉስጥ?በፍትህ እና በህግ ቦታስ?በህዝቦች መስተጋብራዊ ሂደትስ ዉስጥ? በኢትዮጵያ ነገዶች እና ማህበረሰቦች መሃከል በሚፈጠር የርስ በርስ መጠፋፋትስ? በዚህ ሁሉ ስፍራ በኢትዮጵያ ህዝብ መደብ ላይ ያለ ርህራሄ ድምሰሳ ይደረግበታል::

-ግን ሽፋን ያስፈልጋል::እናም ሽፋን ይሰጠዋል::ሽፋኑን እና እዉነቱን መረዳት ያቃተዉ ወይም ምን አገባኝ እያለ ወያኔን የተቀላቀለ ከወያኔ መደብ ጋር በመሰለፍ የኢትዮጵያን ህዝብ መደብ ይደመሣል::ለምሳሌ ወያኔ የኦሮሞ ጉጉ ፖለቲከኞችን ለማታለል የአማራ መደብ ጠላት ብላ ታዉጃለች:: ልክ አሁን የሶማሌ ጉጉ ፖለቲከኞችን ከራሷ ጎን ለማሰለፍ የኦሮሞ መደብ ጠላት ብላ እንዳወጀችዉ ማለት ነዉ:: የሆኖ ሆኖ ግን ወያኔ ጠቅልላ ስታወርደዉ ያላት አንድ የመደብ ጠላት የኢትዮጵያ ህዝብ ነዉ::ሌላዉ ነገር ሁሉ ማምታቻ ነዉ::

– እናም አንዳንዱ ተቃዋሚ ሲመረዉ: አለዚያም ሲባንን የወያኔ ተቃዋሚ ሆኖ ይከሰታል::ሆኖም እርሱም በወያኔ የመደብ ጠባቂ ሀይል ያለ ርህራሄ ይደመሰሳል::የኦሮሞ ተቃዋሚዎች አማራን ጎዳን ብለዉ ከወያኔ ጎን ቢሰለፉም በመጨረሻም የደረሰባቸዉ እጣፋንታ በወያኔ መደምሰስ ነዉ::አሁን የሶማሌ ፖለቲከኞች ኦሮሞን ጎዳን ብለዉ ከወያኔ ጎን ቢሰለፉም የመጨረሻዉ እጣ ፋንታቸዉ በወያኔ መደምሰስ ነዉ::ትልቁ ልዩነት እያንዳንዱ ለወያኔ ድምሰሳ እራሱን በማመቻቸት ማቅረቡ ብቻ ነዉ::

– ወያኔ አንድም ቀን በመደብ አቋሙ ላይ ተደራድሮ አያዉቅም::ወይም በአደባባይ ሲዋሽ ተሰምቶ አያዉቅም::በርግጥ የተለያዬ የማስመሰያ ስያሜ ሊሰጠዉ ይችላል::የብሄር ብሄረሰቦችን እኩልነትን ማረጋገጥ ብሎ የራሱን መደብ የበላይነት እንደሚያራምደዉ ማለት ነዉ:: አማራ ትምክህተኛ: ኦሮሞ ጎጠኛ: ጉራጌ ኪራይ ሰብሳቢ: ሶማሌ ተገንጣይ: እያለ ልዩ ልዩ ስም በመስጠት የኢትዮጵያን ህዝብ መደብ አፈር ያልሰዋል::ስሩን ይነቅለዋል::ግን ሲጠቀለለ አቢዮታዊ ዲሞክራሲ ይሄዉ ነዉ:: ከ45 አመታት በፊትም ሆነ ዛሬ የአቢዮታዊ ዲሞክራሲ ትርጉሙ ይሄዉ ነዉ::

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሚናወቻቸውን የተለዋወጡት አቡነ ኤርምያስና አቶ ታየ ደንድአ

-አንዳንዱ አስቂኝ ፖለቲከኛ ዛሬ የተቃዋሚ መሪ ሆኖ ወያኔ ሲቃወም በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ የመናገሩን ያህል ከዛሬ 30 አመታት በፊት ወይም ወያኔ ወደ ስልጣን ሲመጣ የወያኔን ሻንጣ ተሸክሞ የወያኔን መንበረ ስልጣን እያደላደለ የኢትዮጵያን ህዝብ መደብ ሲደመሥስ እና ሲያስደመሥስ ነበር::እንዲህ አይነት ስነ ሰብዕና የተላበሱ ተቃዋሚዎች በራሱ በሚዲያ ሲጠየቁ የሚመልሱት መልስ ወይም በጽሁፎቻቸዉ የሚደሰኩሩት ዲስኩር ለህዝብ ያላቸዉን ንቀት ያሳያል::”ወያኔ ያኔ ከሞላ ጎደል ዲሞክራሲያዊ ነበር” ብለዉህ ቁጭ::ወይም ደግሞ “ወያኔን ያኔ አናዉቀዉም ነበር ብለዉህ እርፍ::” ያኔም ከደጋፊ ሞቅ ያለ ጭብጨባ::

– የኢትዮጵያ ሰዉ ተቃወምኩልህ ያለዉን ሁሉ ተከትሎ የሚሮጥ ባይሆንም ከህዝቡ መሃከል ተቃዋሚ ነኝ ላለ ሁሉ የሚያጨበጭቡ በብዛት አሉ:: እንዲህ አይነት ተቃዋሚዎች ወያኔን የሚያክል ባለ ጽኑ የፖለቲካ መርህ ሀይል ታግለዉ ነጻ ሊያወጡን መታሰቡ እና ደጋፊዎቻቸዉ ለእነዚህ ሰዎች ማጨብጨባቸዉ በራሱ አጀብ ያስብላል:: እዉነታዉ ግን ወያኔ የሚመራበትን አቢዮታዊ ዲሞክራሲ እና የኢትዮጵያን ህዝብ በጠላት መደብነት ፈርጆ የመንቀሳቀስ ጽኑ ፍልስፍናዉን አንድም ቀን በአደባባይ ሲዋሽ አልተስተዋለም::ለ45 አመታት::

-ሁለት መደቦች አሉ ይልሃል ወያኔ:: አንዱ የህዉሃት መደብ ነዉ::ሌላዉ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ መደብ:: የህዉሃት መደብ ህልዉ ሆኖ የኢትዮጵያ ህዝብ መደብ ምዉት ነዉ::ህያዉ ልሁን ካለ ግን ወደ ሙትነት ያለ ርህራሄ ይሰደዳል::ሆኖም ሂደት ነገሮችን ይገለብጣቸዋል:: የመደብ ትግል የህልዉና ትግል ጉዳይ ነዉና አንዱ ወገን አሸነፍኩ እፎይ የሚልበት ጉዳይ አይደለም:: እናም የኢትዮጵያ ህዝብ መደብ ነገ ህያዉ ይሆናል::ያኔም የወያኔ መደብ ስሩ ይነቀላል::የራሱ የወያኔ አቢዮታዊ ዲሞክራሲ ህሳቤ እራሱ ላይ ይተገበርበታል::መጽሀፍ ቅዱስ እንደሚያብራራዉ በሰይፍ የሚያምኑ በሰይፍ የጠፋሉ እንዳለዉ::በፖለቲካ ርዕዮተ አለምም በመደብ ትግል የሚያምኑ በመደብ ትግል ይደመሰሳሉ እንዲሉ የመደብ ትግል ተንታኝ አስተንታኖች::

ተጨማሪ ያንብቡ:  እኔ የምፈልገው ኢሕአዴግ ወርዶ ማየት ብቻ ነው! (ከበፍቃዱ ዘ ሃይሉ )

1 Comment

  1. ” ወያኔ የሚመራበትን አቢዮታዊ ዲሞክራሲ እና የኢትዮጵያን ህዝብ በጠላት መደብነት ፈርጆ የመንቀሳቀስ ጽኑ ፍልስፍናዉን አንድም ቀን በአደባባይ ሲዋሽ አልተስተዋለም::ለ፴፭ ዓመት።
    **-አንዳንዱ አስቂኝ ፖለቲከኛ ዛሬ የተቃዋሚ መሪ ሆኖ ወያኔ ሲቃወም በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ የመናገሩን ያህል ከዛሬ ፴ ዓመት በፊት ወይም ወያኔ ወደ ስልጣን ሲመጣ የወያኔን ሻንጣ ተሸክሞ የወያኔን መንበረ ስልጣን እያደላደለ የኢትዮጵያን ህዝብ መደብ ሲደመሥስ እና ሲያስደመሥስ ነበር።
    ***”– የኢትዮጵያ ሰዉ ተቃወምኩልህ ያለዉን ሁሉ ተከትሎ የሚሮጥ ባይሆንም ከህዝቡ መሃከል ተቃዋሚ ነኝ ላለ ሁሉ የሚያጨበጭቡ በብዛት አሉ። እንዲህ አይነት ተቃዋሚዎች ወያኔን የሚያክል ባለ ጽኑ የፖለቲካ መርህ ሀይል ታግለዉ ነጻ ሊያወጡን መታሰቡ እና ደጋፊዎቻቸዉ ለእነዚህ ሰዎች ማጨብጨባቸዉ በራሱ አጀብ ያስብላል።”
    ** ቁርጠኛ አመራርና ሕዝባዊ ትግል የለም የጎንዮሽ የመንደርተኞች ልፊያ እንጂ ያልነው ይህንኑ አደለምን!?
    ድንቄም ዴሞክራሲያዊ(ብሔርተኝነት)አብዮት!?

Comments are closed.

Share