March 1, 2017
6 mins read

የጭለማ ዘመን ከኢትዮጵያ ማህጸን ደጋግሞ የመፍለቁ ሚስጢር ምን ይሆን? – ሸንቁጥ አየለ

 

-ዘመነ መሳፍንት ኢትዮጵያን 179 አመታት በጨለማ ዘመን ዉስጥ አስሮ አኖራት::በርካታ ሀገራት በተለይም ምዕራባዉያን ወደ ቀጣይ እድገት የተሸጋገሩበትን የግንዛቤ ለዉጥ የጨበጡት እና መሰረታዊ የአስተሳሰብ ለዉጥ ያመጡበት ወቅት ይሄዉ ኢትዮጵያ በዘመነ መሳፍንት ጨለማ ዉስጥ ስትዳክርበት የነበረዉ ዘመን ነዉ::

-ኢትዮጵያ በታላቁ አጼ ቴዎድሮስ ራዕይ እና ተጋድሎ በዳግማዊ አጼ ሚኒሊክ የማግባባት ጥበብ እንደ ሀገረ ከተሰባሰበች ብኋላ ከማህጸኗ የሚፈልቀዉ አስተሳሰብ አሁንም ወደ ጨለማ ዘመን የሚጎትታት ሆኗል::ህዝቡን እንደ ዘመነ መሳፍንት በብዙ ንጉሶች እና ገዥዎች ለመቀጥቀጥ እና ሀገሪቱን ለመበተን የሚጮህ ከፉ መንፈስ ጉልበት ያገኘ ይመስላል::

-የኢትዮጵያን ህዝብ እግዚአብሄር ኢትዮጵያ ብሎ የጠራዉ አንድ ህዝብ ነዉ::መልኩ እና መልከዓምድሩን ባህሪዉን እና ማንነቱን ሁሉ መጽሀፍ ቅዱስ ዘርዝሮ የዘገበለት ህዝብ ነዉ:: ሆኖም የኢትዮጵያ ምሁር እና ፖለቲከኛ ተብዬዉ ኢትዮጵያዊነትን እንኳን በተባለዉ ደረጃ ሊያከብረዉ ቀርቶ በኢትዮጵያዊነቱ ላይ ነጋ ጠባ እንደተጨቃጨቀ ይሄዉ አመታታ አለፉ:: አንዱ ጎሳ ከሌላዉ ጎሳ የተለዬ እንደሆነ የሚሰብኩ እና ጥላቻን የሚዘሩ ፖለቲከኞች ምድሪቱን ቀስፈዉ ከያዟት ይሄዉ 50 አመታት አለፋቸዉ:: ወደ ፊት በማዬት የነገን የጋራ በረከት ብሎም በመላዉ አለም እየፈለቀ ያለዉን የቴክኖሎጂ ጸጋ ህዝባቸዉ እንዲጠቀምበት ከማድረግ ይልቅ ኢትዮጵያዉያን ለታላቅ የመጠፋፋት መንፈስ እንዲነሳሱ ልዩነት እና ጥላቻን ሰባኪ በዝቷል::

-ቢልጌት እና ታላላቅ የምድራችን ተጽእኖ ፈጣሪዎች እንደሚተነብዩት የሰዉ ልጅ በ2025 ዓም አጠቃላይ የህይወት እንቅስቃሴዉ በቴክኖሎጂአዊ ቀመር በእጅጉ ይለወጣል:: ይሄ የሚሆነዉ ታዲያ አሁን በቴክኖሎጂዉ ላይ በጥልቀት ሳያሰልሱ እየሰሩ ባሉ ህዝቦች እና ሀገራት ዘንድ ነዉ::

-ኢትዮጵያስ? የኢትዮጵያ ጉዳይ እማ አሁንም ወደኋላ መጎተት ሆኗል::ቴክኖሎጂ ላይ መስራት እና ከቴክኖሎጂ ጋር ህዝቡ መተዋወቁ ቀርቶበት የሚግባባበት የጋራ ሀገር; የጋራ መንፈስ እና ቃላት እንኳን አጥቷል::አሁን ያለዉ ትዉልድ እርስ በርሱ ሊግባባ ቀርቶ ቀድመዉ ከነበሩ የታሪክ ተዋንያን ጋርም ተጣልቷል:: የተሰራለትን ሀገር በምስጋና ተረክቦ የተሻለ ዲሞክራሲያዊ ሀገር አድርጎ ለመስራት በመግባባት ከመስራት ይልቅ ሀገሩን በመከራ ዉስጥ አልፈዉ የገነቡ አባቶችን ምላሱን እያወጣ መሳደቡን ቀጥሏል::የሰፈነዉ ሀገራዊ መንፈስ እጅግ አስጨናቂ እና አስፈሪ ነዉ::

-ይሄን ያስተዋለ እና ጭቅጭቅ የሰለቸዉ አንዳንድ ሰዉ ታዲያ አብረን መኖር ካልሆነልን ለምን አንለያይም ሲል ሀሳብ ያቀርባል:: ግን ጥያቄዉ የኢትዮጵያ ሰዉ ቢለያይስ አሁን በሀገር ደረጃ ያለዉ የመለያዬት እና የጥላቻ መንፈስ ወደ እዬ ነገዱ አይወርድም ወይ? ደግሞስ እዉነት ለመለያዬት ኢትዮጵያኖች ቢወስኑ እርስ በርስ የሚያጫርሳቸዉ ብዙ ነገር የለም ወይ? አንዳንዱ እንደሚያስበዉ እያንዳንዱ ቁራጭ መሬት እያንጠለጠለ መሮጥ ይቻላል ወይ? ይሄኛዉ መሬት የዚያኛዉ ጎሳ/ነገድ ብሎ እርኩስ መንፈስ የሰፈረበት ወያኔ እንደከለለዉ ሀገሩ ሲፈርስ ህዝቡ ተስማምቶ ይሄ የኔ ያኛዉ ያንተ ብሎ ምድሪቱን መከፋፈል ይችላል ወይ?መለያዬትስ አብሮ ከመኖር ቀላል ነወይ? ከቶስ ኢትዮጵያ ብትፈራርስ አትራፊ ወገን አለ ወይ? አሁን ነገር እና ጥላቻ የሚጎነጉነዉን ፖለቲከኛ እና ምሁር አብሮ መኖር ያላስማማዉ መለያዬት ሊያስማማዉ ይችላል ብሎ ማሰብ ይቻላል ወይ?

ዋናዉ ጥያቄ ግን እንዲህ የጭለማ ዘመን ከኢትዮጵያ ማህጸን ደጋግሞ የመፍለቁ ሚስጢር ምን ይሆን?

eth cry
Previous Story

የጭለማ ዘመን ከኢትዮጵያ ማህጸን ደጋግሞ የመፍለቁ ሚስጢር ምን ይሆን?

Next Story

እኛ በኛ እንኩራ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop