October 26, 2016
13 mins read

በተስፋ መቁረጥ ኦነግ ሲጋለጥ

ከሃምሳ ዓመት በላይ ኢትዮጵያን ለመሰባበር ታጥቆ የተነሳው የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦነግ) ነኝ የሚለው አሸባሪና ቅጥረኛ ቡድን ፣ ሲዳክርበት ከነበረው አሮንቃ ውስጥ ሆኖ አሁን ተስፋ በቆረጠ መልኩ አቋሙን በይፋ ቁልጭ አድርጎ በአደባባይ አውጥቷል።ይህ ቀደም ሲል በሶማሊያና በአረቦች እርዳታ ኢትዮጵያን ለመሰባበር ጫካ ገብቶ ሳይሳካለት ቀርቶ በየአገሩ ተበታትኖ የነበረ ቡድን ፣ከዛሬ ሃያ አምስት ዓመት በፊት በወያኔ ጥላ ስር ተሰብስቦ የወደቀ ዓላማውን ከቤተመንግሥት ተግባራዊ ለማድረግ ሲል ኢትዮጵያን ለማፈራረስ በሚያስችለው ቻርተር አውጭነት ተሳትፎ እንደነበረና በሽግግርም ስም የሥልጣኑ ተቋዳሽ እንደነበረ የሚታወቅ ነው።“ሌባ ሲሰርቅ ይስማማል ሲካፈል ይጣላል” እንደሚባለው ከሽግግሩ በዃላ በቅርምቱ ድርሻ ላይ በተነሳ አለመግባባት ከወያኔ ጋር ተጣልቶ አገር ጥሎ ወደመጣበት የውጭ አገር ጓዳ እንደገባ የሚታወቅ ነው። ከጥቂት ዓመታት ወዲህ በወያኔና በሻብያ መካከል በተፈጠረው የጥቅም ግጭት አሥመራ ከተማ ቢሮ ከፍቶ የመንቀሳቀስ ዕድል አግኝቶ የተበታተነ ሃይሉን ለማሰባሰብና የዘረኛ መርዙን መርጨት ከጀመረ ውሎ አድሯል።ይህን የመሰለውን አገር አጥፊና የውጭ ቅጥረኛ ቡድን የሚረዱት የኢትዮጵያን አንድነትና ሰላም የማይሹ ታሪካዊ ጠላቶቿና በወረራና በዘረፋ የተካኑት የውጭ አገሮች ጭምር ናቸው። በጣም የሚያሳዝነው በኢትዮጵያ መሬት ተወልዶ፣አድጎና ተምሮ ለቁም ነገር የበቃውም ዜጋ ለዚህ አደገኛ ቡድን ጆሮውን መስጠቱና ለራሱም የሚተርፈውን የጥፋት ነጋሪት አዋጅ በትእግስት ማዳመጡ ነው።በሌላም በኩል አንዳንድ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንታገላለን የሚሉ ቡድኖች ለምሳሌም እንደግንቦት ሰባት አይነቶቹ ከዚሁ ዘረኛ የኦነግ ቡድን ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘው፣ “የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው”፣ወይም ወያኔን ለመጣል ከጸሃይ በታች ካለ ጋር እንስማማለን በሚል ጮርቃ ስልት ከኦነግና ከመሳሰሉት ጸረ ኢትዮጵያ ሃይሎች ጋር ተሰልፈው ማየቱ ብዙዎችን ያሳሰበ ቢሆንም አሁን የቆሙበትን ዓላማ ከጥያቄ ውስጥ ያስገባዋል።ከአሁን በዃላ እያምታቱ የሚጓዙበት ሰዓት አይደለም፣ከወሳኝ ሰዓት ላይ ደርሰናል። ጠላታችንን አውቀናል ፣በአገር ቤት ወያኔና ደጋፊዎቹ፣በውጭ ደግሞ ኦነግና የኦነግ ደጋፊዎች ናቸው። በአገር ቤት በተቀጣጠለው ሕዝባዊ ትግል የኦሮሞና የአማራው ማህበረሰብ ለጋራ መብቱ ተቀራርቦ ሲታገል ያስበረገጋቸው የኦነግ መሪዎች ሕዝቡ ለምን ተቀራረበ፣ ኢትዮጵያን የመበታተን ተልእኮአችንን አከሸፈብን በሚል ቁጭት ሰሞኑን በእንግሊዝ አገር ዋና ከተማ ለንደን ውስጥ ተሰብስበው በተናገሩት ይፋ አድርገውታል።ያም አላማቸው ኢትዮጵያን መበታተን እንደሆነ ደጋግመው ሳያፍሩና ሳይፈሩ አረጋግጠዋል።የጥላቻ ዶር.የሆነውና የሱም አውታንቲ የሆነው ጁዋር ሙሃመድ የተባለው ተላላኪ የተናገሩትን በብዙሃን የዜና ማሰራጫዎች ያልሰማ ቢኖር ጥቂቱ ነውመሰማትም ያለበት ነው።ወያኔ ሳይቀር በአገር ቤት ሕዝቡን በሸምቀቆው ውስጥ ለማስገባትና ከተሳተፈበት ትግል እንዲርቅ ለማድረግ ቅስቀሳ አካሂዶበታል። እኔ ከሄድኩ የሚጠብቃችሁ ይህ ነው ብሎም ለማስደንበር ተጠቅሞበታል።በሌላ መልኩ ሲያዩት የኦነግን ስብሰባ ወያኔ ስፖንሰር ያደረገው ይመስላል።ታዲያ ኦነግን የትግል አጋሬ ነው የሚለው ግንቦት ሰባት ምን ዋጠው? አሁንም ተቃቅፎ ይሄዳል?በኦነግም ሆነ በሌሎቹ የነጻ አውጭ ነን ብለው ከጎኑ በተሰለፉት ቡድኖች ላይ ያለውን አቋሙን ግልጽ ማድረግ ይጠበቅበታል።ያንን ካላደረገ በገንዘብና በሃሳብ የሚረዳው ኢትዮጵያዊ ጉዳዩን በጥሞና መመርመርና አቋም መውሰድ ይገባዋል። በኦሮሞ ማህበረሰብ ስም የሚነግዱ ብዙ ድርጅቶች እንዳሉ አይካድም፤ በሌላውም ማህበረሰብ ስም እንዲሁ።ዓላማቸው አንድ ሲሆን የሚለያቸው ዓላማቸውን ለመተግበር የሚሄዱበት ስልት ነው።ይህ ያልገባው የዋህ ኢትዮጵያዊ በፊለፊት የገባውን ሌባ ወያኔን እየተቃወመ በጓዳ በር ልግባ የሚለውን ሌባ እንደቤተሰብ አይቶ አጅቦ መሄድ አይኖርበትም።ሌባ ሌባ ነው ብሎ ለንብረቱ ዘብ መቆም ይኖርበታል። በዚህም ሆነ በዚያ ኢትዮጵያን እንደ አንድ አገር፣ኢትዮጵያውያንን እንደ አንድ ሕዝብ የማያይ ቡድንም ሆነ ግለሰብ መልካም አቋም አለው ብሎ መገመትና ፣በዚያ ላይ ያለ ልዩነትን የዲሞክራሲና የእኩልነት መብት አድርጎ መቀበል ጅልነት ነው። ሰው በአገሩና በማንነቱ ላይ አይደራደርም።ይህ አገር የማዳን ትግልና አላፊነት የአንድ ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን ከጠባብነትና ከትንሽነት ይልቅ ትልቅነትን፣ከክልል እስረኝነት፣ይልቅ የሰፊ አገር ባለቤትነትን የሚሻ፣እንደአውሬ ሳይሆን እንደጤነኛ ሰው የሚያስብ ሁሉ የሚሳተፍበት ትግል መሆን ይኖርበታል። ከሃገር ወጥቶ መንደር ውስጥ መሰግሰግ የድህነትና የአውሬ ኑሮ ናፋቂ መሆን ነው።

አገር ሲባል መግለጫው ሰንደቅ ዓላማው ነው።ማንኛውም አገር የሚኖረው ሰንደቅ ዓላማ አንድ ብቻ ነው።ሌላ ባንዲራ ማውለብለብ ማለት የተለየሁ ነኝ ማለት ነው።የተለየሁ አገር ዜጋ ነኝ ብሎ የተሰለፈን ቡድን ማጀብ እራሱ የተለየህ ነህ ብሎ ማጽደቅና መቀበል ማለት ነው።ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ ነው ካልን የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ልንነፍገው አይገባም።የነውጠኞቹን ባንዲራ ተሸክሞ የሚነጉደውን የዋህ ከጥፋት ጎዳና እንዲወጣ መምከር እንጂ፣ በርታ እያሉ ከጎኑ ሊሰለፉለት አይገባም። የተለያዩ ቋንቋዎች ባህሎችና፣እምነቶች መኖር የሌላ አገር ዜጋ አያደርግም።እንደ ኢትዮጵያ ባለብዙ ቋንቋና ባህል እንዲሁም ሃይማኖት ባለቤት የሆኑ አገሮች ብዙ ናቸው።እነዚያ ግን በዛው ተዋረድ ተለያይተው እርስ በርስ ሲጋጩ አይታይም።በልዩነት አንድነትን፣በመከባበር መተባበርን መርጠው የእድገትና የሥልጣኔ ባለቤቶች ለመሆን በቅተዋል። የኦነግንና የመሰሎቹን፣ የዘር ትግል የሚያራምዱትን ቡድኖች እራሱ የራሳቸው ቋንቋ ተናጋሪ የሆነው በስሙ የሚነግዱበት ማህበረሰብ ሊታገላቸው ይገባል።አይሳካላቸውም እንጂ ቢሳካላቸው መልሰው የሚቀጠቅጡት መሆኑን ካሁኑ መገንዘብ አለበት።ብዙ የኦሮሞ ተወላጅ በኢትዮጵያዊነቱ የሚያምንና ለኢትዮጵያ አገሩም የደም ዋጋ የከፈለ ለመክፈልም ዝግጁ የሆነ ነው።በስሙ ስልጣን ይዘው መቀመቅ ሊከቱት የተነሱትን በየአገሩ ተበትነው በስሙ የሚነግዱትን ተዋርደው ሊያዋርዱት የሚቅበዘበዙትን ቅጥረኞች ወግዱ ሊላቸው ይገባል።በሰሞኑ የለንደኑ ስብሰባ የኦነግን ዓላማ የተገነዘቡት የኦሮሞ ልጆች በቁጣ ተነስተው ድምጻቸውን በማሰማት ላይ ናቸው።ኢትዮጵያዊነታቸውን አስመስክረዋል።ሌላውም እንዲሁ የዝምታንና የፍርሃትን አጥር አፍርሶ ኢትዮጵያዊነኝ ፣አትወክሉኝም ብሎ ሊያሳፍራቸው ይገባል። አሁን ጊዜው የመኖር ወይም ያለመኖር ነው።በኦነግና በመሰሎቹ ፣በወያኔና ባጃቢዎቹ የዘረኞች ካምፕ ውስጥ የሚከናወነው ደባ በተባበረ የኢትዮጵውያውያን ክንድ መሰበር አለበት።እነሱን ማሶገድ ማለት ኢትዮጵያን ከመበታተን፣ እራስን ከእልቂትና ከሽብር ማዳን፣ሁሉንም የሚያገለግልና የሚያረካ ስርዓት ማስፈን ማለት ነው።መቀራረብና መነጋገር የሚቻለው አንድ አይነት ዓላማና ፍላጎት ካለው ጋር እንጂ ልዩ ነኝ ከሚልና ሊያጠፋ ከመጣ ጠላት ጋር አይደለም።ስለሆነም ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ድርጅትም ሆነ ስብስብ ከኦነግና ከመሳሰሉት ጋር መደራደሩን ማቆም አለበት።ግንኙነቱ በግልጽ ያጥፊና የጠፊ እየሆነ መጥቷል።ለይቷል! እራስንና አገርን ከአደጋ ለማዳን ከሚሹት ጋር ውይይት ማድረግ እንጂ በስም ከሚለዩ ከጥፋት ሃይሎች ጋር መደራደር አይገባም።ትልቅ ስህተት ነው።ምርጫው ከጅንጀሮ ቆንጆ ነው።ትግሉ የወያኔን ስርዓት በኦነግ ወይም በተመሳሳይ ስርዓት ለመተካት አይደለም።መሆንም የለበትም።የዘረኞችን ስርዓትና ዓላማ የሚደመስስ ፣ዳግም አምባገነኖች የሚፈልቁበትን ምንጭ የሚያደርቅ መሆን አለበት። መጃጃል ይብቃ! የአንድነት ሃይሉ በዚህ ወሳኝ ወቅት መሰባሰብ አለበት!
ኢትዮጵያ በነጻነት ለዘላለም ትኑር!! ፣
አገሬ አዲስ

6 Comments

  1. Exactly we have to clear from the begining if they do.t belive with one flag they are not Ethiopian’s.

  2. አትተለሉ, ወደደችዉም ጠለችዉ ኦነግ የእየንደንዱ ኦሮሞ ደም ዉስጥ የተወአደ እዉነት እነ ንዱሕ ድርጅት ነዉ period.ይልቁንስ የተመራዘ አእምሮአችዉን አድዱነ የተጨነበችዉን የበርነት ዘመን በመተበበር ለመሰጠር ትጉ.የገራ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠለት አንድና አንድ ነዉ.አዑንም ብሆን ኦሮሞን የመተዉቅ፣የምትገል፣የምተሰደድ፣የምትዘረፍ መሬት አልበ የሚተደርግ ብቸ በጥቅሉ ነደነቱን የተነፈገ ኦሮሞን ጨፍልቀ የሚትጉአዝ ኢትዮጵያን ኦሮሞ አየዉቀትም.ሊኖርበት የሚፈልገዉ ኢትዮጵያ ነደነቱን ሙሉ አድርጋ የሚትቀበለዉን እንጅ ቨራርፋ ያምትታልለዉን አይፈልግም.

  3. ዘ ሐሻ ፔጅ ሁል ጊዜ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ሲያወራ ይታያል ይሰማልም፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ አንድ በመሆኗ ያገኘችውን ሰላም፣ ዲሞክራሲና ዕድገት ለማስረዳት አይሞክርም፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት በአንድነት ስም የሚሰራ ሴራ ስላለ ነው፡፡ ኢትዮጵያን ስንመለከታት ከዓለም ካሉት ሀገሮች በድህነትም ቢሆን ከመጨረሻዎቹ የምትመደብ ናት፡፡ ዲሞክራሲም ቢሆን ጽንሰ ሀሳቡ ተጀምረዋል እንጂ አድጎ አልጨረሰም፡፡ ሰላምም ቢሆን አንጻራዊ ነው አንጂ በአስተማማኝ ደረጃ ላይ አልደረሰም፡፡ እና ኢትዮጵያ አንድ ሆና ያተረፈችው ነገር ቢኖር ምንም ነው መልሱ፡፡ በቅኝ ግዛት አልተገዛንም ሊባል ይችላል ፡፡ ግን እሱም ቢሆን በኔ አመለካከት ጣሊያን በአምስት አመት የሠራውን የመንገድ ዝርጋታ ኢትዮጵያ በራሷ በ100 ዓመት አልሠራችም፡፡ የአንድነት ዲስኩር ነፊዎች ታዲያ በአንድነት ስም የራሳቸውን ዘረፋና የበላይነት ሲያረጋግጡ እንደኖሩ ወደፊትም ለማስቀጠል በሞተ አመለካከታቸው ዛሬም እንደ ደሮው የሚሳካላቸው መስሎአቸው ሲራወጡና የሌሌ ታሪክ ሲያወሩልን ይታያል፡፡ አንድነት የሚያምረው ሁሉም እኩል ስጠቀም ነበር፡፡ ባለፉት ዓመታት የአማራው የበላይነት በሁሉም ዘርፉ ገኖ ታይተዋል፡፡ ያንን የበላይነት ያገኘው በኢቲዮጵያ አንድነት ስም በሚነግደው ትርፍ ነው፡፡ ያንን ትርፍ ለማስቀጠል ዛሬም የኡፍኝት ልጅ ኡፍኝት እንዲሉ ልጆቻቸው የአባቶቻቸውን ሌጋሲ አስቀጣይ ለመሆን ዛሬ ላይ ሆነን ስናይ የሚያስጠላውን ፖለቲካው ሌላውም እነዲወደው ለማድረግ መራወጥን ተያይዘውታል፡፡ ለኢቲዮጵያ አንድ መሆንና አለመሆን ወሳኙ አክትቪስት፣ ፖለትከኛ ወይም የውጭ ሀይል አይደለም፡፡ የሀገርቱ ሁኔታ የህዝቦቿ ስሜት ወሳኝ ነው፡፡ አሁን ባለች ኢትዮጵያ ያሉት ብሔሮች ሁሉ ተደስተው አንድነት ምርጫቸው ሆኖ ያለምንም ገፊት በአንድነት ለመኖር ያላቸው ውሳኔ ካለ እሱ ውሳኔ ሊከበርላቸው ይገባል፡፡ ያለማንም ግፊት ኢት;ዮጵያዊነት አላዋጠኝም ያለ ብሔር ካለ ሪፈረንደም ተሰጥቶት የራሱ ምርጫ ከሆነ ሊለቀቅ ይገባል፡፡ እውነተኛ ዲሞክራሲ መገለጫው ይው ነው፡፡ በቅርቡም በእንግሊዝ አገር የተካሄደውም ሪፈረንደም የተሰጠው ሕዝብ ከእንግሊዝ ጋር ለመኖር በመወሰኑ የመገንጠል ጥቄው አጀንዳ ተዘጋ፡፡ በኢትዮጵያም የመገንጠል ጥያቄን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስቀረት መሰራት ያለበት እንዲህ አይነት ነገር ነው፡፡ ያኔ በራሱ ነጻ ፍላጎ አብሮ ለመኖር የወሰነውን ሕዝብ በሀይል ለመገንጠል የሚነሳ ካለ ትርፉ ድካም ብቻ ይሆናል፡፡ እንድ ላይ መኖር አልፈልግም የሚለውንም ሕዝብ በግድ ትኖራለህ የሚልም ካለ ትርፉ ድህነት፣ ጠላቻ፣ አለመረጋጋት ብቻ ነው የሚሆነውና በዚህ መልኩ ቢሰራ ውጤታማ ይኮናል፡፡

Comments are closed.

Previous Story

እነ ሳሞራ የኑስ አዲስ የቴሌቪዥን ጣቢያ ሊከፍቱ ነው

Girma Siefu
Next Story

ለኢትዮጵያ ፖለቲካ መሪነት ተቃዋሚ መሆን ብቻ አይበቃም!!! – ግርማ ሠይፉ ማሩ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop