August 26, 2013
6 mins read

በሚኒሶታ የተጠራው የአባይ ቦንድ ሽያጭ ሳይጀመር ተበተነ (አጠቃላይ ዘገባ)

ፖሊስ የአባይ ቦንድ ይሸጥበታል የተባለውን አዳራሽ ዘግቶ እየጠበቀ
በሚኒሶታ የተጠራው የአባይ ቦንድ ሽያጭ ሳይጀመር ተበተነ (አጠቃላይ ዘገባ) 1
(ዘ-ሐበሻ) “ይህ ድፍረት ነው፤ ይህ ሁሉ ኢትዮጵያዊ በሚገኝበት ከተማ ያውም ፖስተር ለጥፎ ኑ ቦንድ ግዙልኝ ብሎ መለጠፍ እብደት ነው።” ነበር ያለን በሚኒሶታ የጠራውን የቦንድ ስብሰባ ለማክሸፍ ከተሰባሰቡት ኢትዮጵያውያን አንዱ። “ቀድሞ የወያኔ ስብሰባ በዚህ ከተማ ሲደረግ በድብቅ ነበር። ፖስተር ለጥፈው ኑ! ሲሉን እኔ ይሄ ስድብ ነው፤ ወይም የሚሰሩትን አያውቁም ብዬ ነበር” በማለት ሃሳቡን አካፍሎናል።
የሚኒሶታ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ይሄድባቸዋል በተባሉ አካባቢዎች “የአባይ ቦንድ ቀን” በሚል እሁድ ኦገስት 25 ቀን 2013 ከቀኑ 2ሰዓት እስከ ምሽቱ 8 ሰዓት የቦንድ ሽያጭ የሚገልጽ ፖስተር ተለጥፏል። የዚህን ፖስተር መለጠፍ ያሉ በሚኒሶታ የሚኖሩ አክቲቪስቶች ባለፈው ረቡዕ በቴሌኮንፍረንስ ተገናኝተው እንዴት ይህን ስብሰባ እንደሚያሰናክሉ ተወያይተው ነበር። እንደከዚህ ቀደሙ ወያኔ ስብሰባ ሲጠራ ከውጭ ሆኖ መቃወም ያለፈበት ፋሽን መሆኑን ተስማምተው ስብሰባው ውስጥ ገብቶ ድምጽን ማሰማት በሚል ተስማምተው ቀኑ ተቆረጠ። በሌላ በኩልም በሚኒሶታ የሚገኙ የድምጻችን ይሰማ አባላቶች በከተማዋ በሚገኙ መስጊዶች አርብ ዕለት የአባይ ቦንድ ሽያጭን ለማክሸፍ የተነጋገሩ ሲሆን በዚሁ መሠረት ሁሉም ቀኑን በጉጉት ሲጠብቅ ቆይቷል።
“ወያኔ ገንዘብ አለው፤ 2 ቦታ ስብሰባ አዘጋጅቶ አንዱ ጋር ተቃውሞ ሲደርስበት በሌላው ቦታ ሲያደርግ ቆይቷልና ይህን ለማጥናት በቦንዱ ሻጭ አስተባባሪዎች መሃል የራሳችንን ሰዎች አስቀምጠን ጉዳያቸውን እንከታተል” ነበር ያለን አክቲቪስት ሰለሞን በላይ “ያሰብነው ተሳክቷል” ሲል ለዘ-ሐበሻ ገልጿል።
ከድምጻችን ይሰማ፣ ከክርስትና እምነት ተከታዮች፣ ከተለያዩ የፖለቲካ አቋም ካላቸው ወገኖች የተውጣጡ ኢትዮጵያውያን ስብሰባው ይደርግበታል በተባለው የሴንት ፖል ላኦ ኮምዩኒቲ አዳራሽ ደጃፍ የተገኙት ስብሰባው ይደረግበታል ከተባለው 2 ሰዓት ቀድመው ነበር። ስብሰባው ሊጀመር አንድ ሰዓት ሲቀረው ሕዝቡ የኢሕአዴግ ተወካዮችን ሲመለከት “ድምጻችን ይሰማ፤ ከአባይ በፊት የሙስሊሞች መብት ይከበር፣ እነበቀለ ገርባ ይፈቱ፣ እነእስክንድር ይፈቱ…” የሚል ድምጽ ማሰማት ሲጀምሩ ቦንድ ሽያጩን ከሚያስተባበሩት መካከል ወደ ሕዝቡ በመጠጋት ፎቶ ግራፍና ቪድዮ ለማንሳት ይሞክራል። ህዝቡም ፎቶ አታንሳን፤ ቪድዮ አትቅረጸን በሚል ልጁን ቢቃወሙትም አልሰማም አለ። በአማርኛ ቋንቋ እያናገሩት በትግርኛ ይመልስላቸዋል። “ሃገር ቤት የቀረጻችሁት ይበቃል” በሚል በተነሳው ግብግብ ካሜራ የያዘው የኢሕ አዴግ ተወካይ ክፉኛ የተደበደበ ሲሆን ካሜራውም ተሰባብሮበታል።
ወዲያውኑ የሴንት ፖል ከተማ ፖሊስ ወደ አካባቢው በመድረስ ጉዳዩን ሊያረጋጋ ሲሞክር ጉዳዩ እየተካረረ መጣ። ከ20 የማያንሱ የፖሊስ መኪናዎች አካባቢውን ወረሩት። ቦንድ ለመሸጥ የመጣም፤ ሊቃወም የመጣም በአካባቢው እንዳይደርስ ፖሊስ ቦታውን ከቦት የዋለ ሲሆን የቦንድ ሽያጩም ሳይጀመር በተነሳው ግብግብ ተበትኗል።
http://youtu.be/b5e59e7u-1Y
የአይን እማኞች ለዘ-ሐበሻ እንደገለጹት የቦንድ ሽያጩን የሚያስተባብሩት ኢሕ አዴጋውያን በሌላ ቦታ ሽያጩን ለማድረግ ቢሞክሩም ሳያሳካላቸው ቀርቷል።
በሚኒሶታ ለአባይ ቦንድ ሽያጭ ስብሰባ ሲጠራ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ከዚህ ቀደምም እንዲሁ የቦንድ ሽያጩ በ0 መጠናቀቁ ይታወሳል።
ይህን ቦንድ ያስተባበሩትን ወገኖች ዘ-ሐበሻ አግኝታ ለማነጋገር ያደረገችው ጥረት ባይሳካም፤ በቀጣይ እድሉን እንዳገኘን ለማቅረብ እንሞክራለን። ለጊዜው ግን ይህን ተቃውሞ ካስተባበሩት አክቲቪስቶች መካከል ከ2ቱ ጋር ዘ-ሐበሻ ቆይታ አድርጋለች ይከታተሉት።
ቃለ ምልልስ ክፍል 1
[jwplayer mediaid=”6706″]

ቃለ ምልልስ ክፍል 2
[jwplayer mediaid=”6700″]

3 Comments

  1. shame that ur proude of ur stupidity …and ur suggesting that u’ll be a better leader than woyanne? no no no ur wrong …ur soooo wrong ur no better than woyanne …may be jealous because ur not sitting on top like those parasites called woyanne …ur even worse …abay is not a property of woyanne …its a gift from God to Ethiopia and ur stupid enough not to know that… shame …i shout out loud for freedom n simultaneously i’ll fight to build the renaissance dam ….we the peoples who are living in Ethiopia don’t need a single penny from the diaspora …keep ur money in ur pants, ur stupidity is limitless

      • am not a woyanne, atleast not yet, but i’m thinking of becoming one, its better than joining u guys …sew hager hono kemichoh ategebe meto yemitagel new yetefaw …rehaben sheshteh aydel ende sew hager hedeh hodehn yemetmolaw? wend kehonk meteh tagel kategebe

Comments are closed.

Previous Story

የድምጽ ቃለምልልስ የሚኒሶታውን የአባይ ቦንድ ሽያጭ ካከሸፉት አክቲቪስቶች ጋር (Audio)

MDG Ethiopia Meles Zena 009
Next Story

በወያኔ “ያደገችዋን” ኢትዮጵያ ዓለም እንዴ ያያታል?- ዶ/ር ዘላለም ተክሉ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop