1 የኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዞና የህዝባዊ አመፅ እንድምታዎች (ያሲን መ. ያሲን)

5 መሆኑ እሙን ነው ከእነዚህ ሁለት አበይት ተግዳሮቶች በመንደርደር ኢህአዴግ በምንም መልኩ የቀድሞ የህወሃት አሻንጉሊት ሆኖ ሊቀጥል ወደማይችልበት ደረጃ መሸጋገሩን መገመት አይከብድም ግዑዝ አካል እንጂ ማንም ህይወት ያለው ፍጡር ከእነዚህ ሁለት አንኳር አስፈንጣሪ ግፊቶች በኋላ መልኩና ይዘቱን አይለውጥም ብሎ መገመት የሚያዳግት ይመስላል ህወሃት የጀመርኩትን የሀዲድ መስመር ለቅቄ አልወርድም ካለ አገሪቷን መበተን ብቻም ሳይሆን መሰረቴ የሚለውን የትግራይ ህዝብንም ከከባድ እልቂት ለመታደግ እንደሚያዳግተው ከወዲሁ የተገነዘበ ይመስላል በመሆኑም ብቸኛ አማራጩ ላለፉት 25 ዓመታት ያካበተውን አእምሮአዊ እና ቁሳዊ ሃብት ተመስገን ብሎ በማጣጣም ቀሪውን ጊዜ ከሌሎች የኢህአዴግ ድርጅቶች ጋር ተመጣጣኝ በሆነ የወሳኝነት ሚና ራሱን ገድቦ በሂደትም ድርጅቶቹን ርዕዮተ ዓለም ላይ የተመረኮዘ ህብረ ብሔራዊ ቅርፅ እያላበሰ መሄድ የግድ የሚል ይሆናል ይህ ሂደት ድህረ ታጋይ መለስ ህልፈት እንደተመለከትነው የአገሪቷ የፖለቲካ ስልጣን የህወሃት ከሌሎቹ አባል ድርጅቶች ጋር ተካፍሎ እየመራ እንደመሆኑ በቀጣይ የኢህአዴግ የለውጥ ሂደት ደግሞ የመከላከያና የደህንነት ተቋማት ድርሻውንም ተመጣጣኝ ማድረግ እንዲሁም የሲቪል ሰርቪሱን ከፍ ሲል ሙያና ብቃትን መሰረት ባደረገ ቢያንስ ደግሞ ሁሉም የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ተመጣጣኝ ድርሻ እንዲኖራቸው ማድረጉ አስገዳጅ ይመስላል ይህ የኢህአዴግ የውስጥ ለውጥ ለቀጣይ የዴሞክራሲ እድገትና ቱርፋቶች በር ከፋች ብቸኛ መንገድ ይሆናል ፍጥረታት ሙሉ ልውጠተ ቅርፅ ለማገባደድ የግድ ማለፍ እንደሚገባቸው egg – larva – Pupa – Adult የሚባሉት ደረጃዎች ሁሉ ኢትዮጵያም አሁን ባለችበት ነባራዊ ሁኔታ አንፃር አይቀሬ የሚባሉ እርከኖችን ዘላ በህዝብ እንቢተኝነትና አመፁ ብቻ በቀጥታ ወደ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር መግባቱ አዳጋችና የማይታሰብ እንደሚሆንባት ማመኑ የግድ ይላል አገሪቷ አሁን ባለችበት የዲሞክራሲ እድገት ደረጃ ሰላማዊውም ሆነ ሌላው አይነት ትግል ለለውጡ አጋዥ ኃይል ከመሆን ያለፈ አስተዋፅኦ ይኖራቸዋል ብሎ መከራከር ጉንጭ አለፍ ከመሆን አይዘልም በእርግጥ አገራችን ወደ ዴሞክራሲያዊ ቱርፋት ለመዝለቅ ይህን ያክል ረጅም ጉዞ ለምን አስፈለጋት ብሎ መቆጨትና መንገብገብም ማንም ሊረዳው የሚችል መሆኑ ባይከብድም ጊዜ ወሳጅ መሆኑን መገንዘብ ግን ግድ የሚል ይመስላል እርግጥ ነው ብዙ አቋራጭ መንገዶች ተዘግተውብን በረጅሙ መንገድ መንጓተታችን አይካድም የሩቁን እንኳን ትተን ምናልባትም ንጉሱ ወራሽ አግኝተው የፊውዳል ትድድሩን ወደ Constitutional Monarchy እና ኢኮኖሚውን ከፊዳላዊ ቀንበር አላቀውት ቢሆን ኖሮ ህዝባችን የተራዘመ የኮሚኒዝም ስርዓት ገፈት ቀማሽ ባልሆነ ነበር ከዚያም አልፎ ደርግ በአገሪቷ በየአቅጣጫው የተነሱትን የማንነት ጥያቄዎች እራሱ ባቋቋመው የብሄረሰብ ጥናት ኢንስቲትዩት ሙህራን ካቀረቡለት አማራጮች በአንድነት ጥላ ስር የማንነት ጥያቄዎችን መመለስ ቢቻል ኖሮ ህወሃት ጠልፎ የሚያጮኸው አጀንዳ ሊያጣ ይችል ነበር ይህ ቢሆን አገሪቷ ላለፉት 25 ዓመታት ያየችውን የአንድ ብሔር የሁሉ ጠቅል ፖሊሲ ትግበራ ያልተወራረደ ሂሳብ ባልተሸከመች ነበር እንደዚህ እንደዚህ እያልን ማለቂያ ወደሌለው ቢሆን ኖሮዎች ውስጥ ከመዘፈቅ ወሳኙ ነገር አሁን ካለንበት ነባራዊ ሁኔታ አንፃር በየትኛው ሂደት መታለፍ እንዳለበት መመራመር
6 ለተግባራዊነቱም ከታክቲካል ወዳጅነት ያለፍ ስትራቴጂያዊ ውህደቶችን መፍጠሩ የግድ የሚል ይመስላል ኢህአዴግ ከእንግዲህ የቀድሞ ኢህአዴግ እንደማይሆን ጥርጥር የለውም ኢህአዴግ ይለወጣል ወይም ይፈርሳል አገሪቷ አሁን በያዘችው የፖለቲካ ቅርፅ ኢህአዴግ መፍረሱ ለህልውናዋ አደጋ ነው ከተባለ ትክክለኛ የእድገት እርከኖችን ጠብቆ ኢህአዴግ መለወጥ ይኖርበታል ሲጀመር አራቱ ድርጅቶች ተመጣጣኝ ስልጣን በፖለቲካ፣ መከላከያ፣ ደህንነትና የኢኮኖሚ አውታሮች ውስጥ ሊቀዳጁ ይገባል በመቀጠልም ኢህአዴግ አይዲዮሎጂ ተኮር ህበረ ብሔር ሊሆን የግድ ይለዋል ዛሬ ፌዴራሊዝሙ መጣላችሁ የተባሉ ጋምቤላ ይሁን ሱማሌ ፣ አፋር ይሁን ሐረሪ የኢህአዴግ አባል ሊሆኑ ባለመቻላቸው ብቻ ምንም እንኳን አገሪቷን የመምራት ብቃት ቢኖራቸውም ከማህበራዊ ጉዳዮች ፣ ባህልና ቱሪዝምና መሰል የሚኒስቴር መ/ቤቶች የዘለለ ወሳኝ የፖለቲካ ቢሮዎች ጋር መጠጋት አይቻላቸውም ይህ በንጉሱም ሆነ በደርግ ስርዓት ያልታየ ግልጽ የሁለተኛ ዜግነት ኢፍትሃዊ ጭቆና ነው እነዚህ በተለምዶ አጋር የተባሉት ከኢህአዴግ አባልነት የተገፉ ብሔሮች ከዚህ በላይ ሊጨቆኑ የሚችሉበት መሳሪያ የለም በገዛ አገራቸው በባህል ሙዚቃዎቻቸው ከመጨፈርና ከመዝለል ያላለፉ ባይተዋሮችና የበይ ተመልካቾች ተደርገዋል ኢህአዴግ በአባል ድርጅቶች መካከልም ሆነ ከአጋሮቹ ጋር ባለው ጤናማ ያልሆነ ስርዓተ ትድድር ከዚህ በላይ መቀጠል ስለማይኖርበት ብቻም ሳይሆን ስለማይችል ወደ ህብረ ብሔራዊ ድርጅት ከተለወጠ የመከላከያና የደህንነት መዋቅሮች ጭምር አብረው ይለወጣሉ ያኔ ነው የህዝብ እምቢተኝነትና አመፅ ቀጥተኛ ተፅዕኖ መንግሥት ላይ ማሳረፍ የሚቻላቸው አንድን አምባገነን ስርዓት ለመጣል በስርዓቱ ያኮረፈ ወሣኝ ቦታዎችን የተቆናጠጠ ባለስልጣን ፣ የጦር መሪ ፣ የደህንነት መዋቅር እንዲሁም ወገኔ ላይ አልተኩስም የሚል ህብረ ብሔር ጦር የግድ ይላል በመሆኑም የሰሞኑ ትኩሳቶች ተጠናክረውና ተደራጅተው ኢህአዴግን መልክና ይዘቱን እንዲለውጥ ማስገደድ ይኖርባቸዋል ትግሉን በተቀናጀና በተደራጀ መልኩ መምራትና ከአጉል ተስፈኝነት የዘለለ ምክንያታዊና እርከናዊ ውጤቶችን አልሞ መጓዙን ከልሂቃኑ የሚጠበቅ ብቻም ሳይሆን ጊዜው የሚጠይቀው ወሳኝ ጉዳይ ሆኗል ከማይጨበጥ ህልም ዓለም ተወጥቶ መሬት ላይ ካለው እውነታ ጋር መታረቁ በኢህአዴግም ሆነ በተቃዋሚው ጎራ ላሉት ቡድኖች አማራጭ የለሽ መሆኑን በፅኑ መገንዘብ ይኖርባቸዋል ኢህአዴግ እራሱን ከጎጥ አስተሳሰብ አላቆ ወደ ህብረ ብሔራዊና ርዕዮተ ዓለማዊ ፓርቲነት እስካለወጠ ድረስ አደጋው ለአገሪቷ ህልውና ብቻም አይደለም ዛሬ በየክልሉ የሚገኙ ገዢ መደቦች እና በመከላከያ ተቋማት ውስጥ የተፈጠሩት ማፍያ መሰል ቡድኖች ነገ የወለዳቸውን ድርጅት ተብትበው ላለመጣላቸው እርግጠኛ መሆን አይቻልም ባቄላዋ ስትከርም ባረጀው የኢህአዴግ ጥርስ አለመታኘኳ እሙን ነውና በተመሳሳይ መልኩ የተቃዋሚ ጎራውም ኢህአዴግን ከማስወገድ የዘለለ ጥልቀት ያለው የአስተሳሰብ እምርታ ማድረግን ግድ የሚል ይመስላል በምኒሊክ ጊዜ የደነቆረ አይነት እንዳይሆን ራሳቸውን መሬት ላይ ካለው ከተጨባጩ ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ማላመዱን ከወዲሁ ቢያያዙት ይመረጣል በአገሪቷ ህዝቦች መካከል ያሉት የማያግባቡ የታሪክም ሆነ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ የአስተሳሰብ ልዩነቶች በጥልቀት እያጠኑ፣ እየተወያዩ የድርጅታቸውንም ሆነ የአመራር ልሂቃኑን አመለካከቶች ወደ መሐል መንገድ ማሸጋገርና ማቀራረብ እጅግ ወሳኝ ነጥብ ሆኗል በሁሉም አቅጣጫዎች ይህን መሰል እርከናዊ እርምጃዎችን መኬድ ካልተቻለ የሰሞኑ እንቅስቃሴ እንደከዚህ ቀደሞቹ የህዝብ መሪዎችን፣ ወጣቱን እናም ሚዛን አጋደለ ብሎ ከህቡ ይፋ የሚወጡትን ዜጎች በአዞ አስበልቶ ተመላሽ ሽንቁር ጀልባ እንዳይሆን መጠንቀቁ ሳይበጅ አይቀርም አዲሱ ዓመት በሁሉም አቅጣጫ እርከናዊ ሽግግር ጅማሮ ይሆንልን ዘንድ እንትጋ ! እንታገልም! መቼም እንፀልይ ብዬ አልቀልድምና::

ተጨማሪ ያንብቡ:  በኢትዮጵያ የጦር አበጋዝ መንግሥቶች አንድ ሽህ አንድ የድንበርና ወሰን ግጭቶች ሃገሪቱን ወደ ማያባራ ጦርነቶች ከቷል!!

ራሚደስ ጷጉሜ 5 ቀን 2008 ዓ.ም

2 Comments

 1. Dear Editor
  How to stop ” mekera ” ?
  talk with leaders to ask question ” what is the probleme ”
  killing not solution
  and ask the protesters ” what is your question ? “

 2. Dear Editor

  Having checked with the same article published by ECADF, half of this article is missing or is not published. There must have been some kind of posing mistake which requires correction.

  With regards,

  Solomon

Comments are closed.

Share