May 4, 2016
6 mins read

በቓፍታ ሑመራ ከ2 ሺ በላይ ወጣቶች ታሰሩ

(አምዶም ገብረሥላሴ ከመቀሌ እንደዘገበው)

በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ከ2 ሺ በላይ ወጣቶች በፀረ ሽፍታ ልዩ ሃይል ታድነው ታስረዋል።

(ሁመራ ከተማ)
በቓፍታ ሑመራ ከ2 ሺ በላይ ወጣቶች ታሰሩ 1

ከ2 በላይ ወጣቶች ታድነው የታሰሩት በቓፍታ ሑመራ ወረዳ የሚገኙ በባህላዊ መንገድ ወርቅ የሚወጣባቸው ቦታዎች ነው።
የወርቅ የሚወጣበት ቦታ ከዓዲ ጎሹ እስከ ዓደባይ የሚገኝ ሰፊ መሬት ከሸረ ወደ ሑመራ ሲጓዙ ወደ ሰሜን ኣቅጣጫ የሚገኝ ሲሆን እስከ ኢትዮ_ኤርትራ ድንበር የሚያዋስን የተከዘ ዳርቻዎች የተዘረጋ ነው።
ኣፈሳው የተካሄደው በጠበቖ(ኣንድ ወጣት ሙቶ የተገኘበት)ገዛ ግርማይ፣ መቓብር ዓንደማርያም፣ እነይ ቕበፅኒ ከሚባሉ በወርቅ የበለፀጉ የተከዘ ደንደሶች ነው የተያዙት።(ከዚ በፊት 85 ወጣቶች የታገቱበት ቦታ ነው።) በሺ የሚቆጠሩ ወጣቶች ከፀረ ሽፍታ ልዩ ሃል እንዳመለጡ ታውቀዋል።
ቦታው ወርቅ የሚወጣበት ብቻ ሳይሆን ታጣቂዎች ከኤርትራ እየተሻገሩ በሺ የሚቆጠሩ ወጣቶች ኣግተው የሚወስዱበትና የሚገድሉበትም ጭምር ነው።
የፀረ ሽፍታ ሃይሉ በወጣቶቹ ላይ ዘመቻ የጀመረው ከ17 እስከ 20 /08/08 ዓ/ም ሲሆን ከ2 ሺ በላይ ወጣቶች ኣድኖው ከተያዙ በኋላ በሑመራ ከተማና ሌሎች 13 ቀበሌዎች በተሰሩ ግዝያዊ እስር ቤቶች እንዲታሰሩ ኣድርገዋል።
የዞኑ ሃላፊዎች ወጣቶቹ ለመቅጣት በርካታ የዳኞች መድበው በዘወቻ መልክ የተፈረዱባቸው ሲሆኑ እያንዳንዱ ወጣት ከ700 ብር እስከ 1500 ብር እየከፈልክ ልትወጣ ትችላለህ ተብለዋል። ወጣት ገብርሃንስ ይልማና(700 ብር) ሃለቃ ሓጎስ ገብሩ(1000 ብር) እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል።
መክፈል ያልቻሉ ወጣቶች “ከቤተሰቦቻቹ ኣስልኩ ወይም ተበደሩ” እየተባሉ እየተገደዱ ይገኛሉ። ወርቅ በማውጣት ስራ የተሰማሩ ወጣቶች ድሆች ሲሆኑ በኣገራቸው ስራ ለመስራት ዕድል ያላገኙ፣ ወደ ኣውሮፓ ለመኮብለል ቤተሰቦቻቸው ለሕገ ወጥ ደላሎች(የህወሓት ባለስልጣናት ሸሪኮች) ለሚከፈል ብር ኣቅም ያነሳቸው ናቸው።
ወደ ቦታው ሲመጡም ሁለት ዕድል ግምት ውስጥ ኣስገብተው ነው።
ሀ) ወርቅ የማግኘት ተስፋና ወርቁን ሽጠው ራሳቸውና ቤተሰቦቻቸውን መርዳት
ለ) ከኤርትራ በሚሻገሩ ታጣቂዎች ታግተው ወደ ኤርትራ ተወስደው በባርነት መማቀቅ ነበር።
ሌላ ያልጠበቁት ሶስተኛ ኣደጋ ደሞ
፦ በህወሓት መሪዎች ታድነው መያዝ፣ መታሰርና በገንዘብ መቀጣት የሚለውን ነው።
በኣሁኑ ሰዓት የህወሓት መሪዎች ተግባር ወጣቱ ከህገ ወጥ ደላሎች ጋር በመመሳጠር ከመላ ትግራይ ከተሞችና ገጠሮች ወጣቶች እያማለሉ ለሊብያ መላክና ወላጆቻቸው ተገድደው የሚልኩት 14000(መቶ ኣርባሺ ብር) ተካፍለው መብላት ነው።
ሰሞኑ በማይካድራ ያጋጠመ ምሳሌ የህወሓት ባለስልጣናት በዚ ሕገወጥ ተግባር እጅ እንዳለባቸው ያመላከተ ነው። በኮብላይ ወጣቶች ” ልጆቻችን መልስልን ኣለበለዚያ እናጋልጠሃለን” ተብሎ በወላጆች የተደወለለት ብርሃነ ኣሸብር የተባለው ኣስከውላይ “…በሉ እርማቹ ኣውጡ እኔ የትም ኣታገኙኝም። የኔ ብር ያልቀመሰ የትግራይ ባለስልጣን የለም። ስለዚ ኣርፋቹ የሚጠበቅባቹ ብር ክፈሉ። ካልሆነ ልጃቹ ወደ ኩላሊት ነጋዴዎች ይላካል…” ሲል ዝተዋል።
በሉ እዩልኝ ! እነዚህ ባለስልጣናት በትግራይ ያለው ድሃው ወጣትም በ13 ግዝያዊ ማጎርያዎች ኣግተው በመያዝ ያለ ደላላ ብር ውለድ እያሉ እያስጨነቁት ይገኛሉ።
ወጣቱ ትውል እሳት ትርያንግል ሰርቶ እየለበለበው ይገኛል።
የህወሓትና ባለ ስልጣናት=====> ህገ ወጥ ደላሎችና ኩላሊት ነጋዴዎች(ስደት)====> ከኤርትራ የሚሻገሩ ታጣቂዎች ናቸው።
ወጣቶቻችን ከእልቂት እናድን።
ነፃነታችን በእጃችን ነው።

5 Comments

  1. Keftia is not located in Tigre but in Gondar region. Please Zehabesha stop collaborating with the woyane expansion scheme.

  2. Is there a region called Gondar in Ethiopia. I thought Gondar is a name of an old garisson town? kkkk

  3. “እዚያ እሳት እዚህ እሳት!” ለመሆኑ ይች ሀገር ምንድነው የሚበጃት ለመሆኑ ይህ ትውልድ መብቱን ከማስጠበቅ ይልቅ ሀገሩን መልቀቅ የተሻለ አማራጭ ያደረገው እንዴት ነው? የህወሃት ትግልና የደርግ ጥፋት ምን ነበር? ትግሬ ከሥርዓቱ ተጠቀመ ሲባል ከሀር ስለጠፉ ባርያ ስለሆኑና የውስጥ ሆድ እቃቸውን አስቆርጠው በመሽጣቸው ነው? “እንኳንም ከእናንተ ከወርቅ ዘር ተፈጠርኩ እንኳንም ከሌላ አልሆንኩ”የተባለው ሕዝብና በክልል በተራ ድንኳን ተጥሎ ለዕራዩ ደረት የተደቃለት የእርዳታ ስንዴ ንፍሮ የተነፋለት ለዚሁ ነበር? አዳሜ ከጎጥ ክልል ወጥተህ ደርበህ ምታ አትበልና በተናጠል በደቦ ስትወቃ ኑር!!!

  4. the aim of tplf is to endup or clearup the native citizens of welquite and tegedie… so pls help them zehabesha as you can to these people…but humera is not part of tigrai ,it is the place taken from Amhara by the force of tplf…

Comments are closed.

Previous Story

ዶናል ትራምፕ በጸረ- ሙስሊም እና በጸረ-ስደተኛ አቋማቸው ይገፉበት ይሆን? | ዜና ትንታኔ በታምሩ ገዳ (የሚደመጥ)

Next Story

ትክክለኛውን ቴዲ አፍሮን ምን ያህሎቻችን እናውቀዋለን?

Latest from Blog

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት  አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop