አረና 21 ጥያቄዎችን ይዞ የፊታችን እሁድ ጠዋት በመቀሌ ሮማናዊት አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ

(ዘ-ሐበሻ) የትግራይ ክልል ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ አረና ለትግራይ የፊታችን እሁድ ፌብሩዋሪ 28, 2016 በመቀሌ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ:: የክልሉ መንግስት እስካሁን ሰላማዊ ሰልፉን ስለመከልከሉ የሰጠው መመሪያ አለመኖሩም ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ጠቁሟል::

የአረና ፓርቲ እሁድ በሮማናዊት አደባባይ መቀሌ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ 21 ጥያቄዎችን እንደሚያነሳ ከድርጅቱ አመራሮች የተገኙ መረጃዎች አስታውቀዋል:: በዋነኝነትም በቅርቡ በ ኤርትራ መንግስት ከትግራይ ክልል ስልተወሰዱ ኢትዮጵያውያን ጥያቄ እንደሚያነሳ; በኦሮሚያ ክልል ለተነሳው የሕዝብ ጥያቄም መንግስት ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጥ የሚጠይቁ ጥያቄዎች ይነሳሉ ተብሏል::

አረና ፓርቲ እሁድ ይዟቸው የሚወጣቸው 21 ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው::

1ኛ. በሻዕቢያ ስለ ተወሰዱ 85 ዜጎቻችን
2ኛ. ስለ ሕግ መከበርና አብርሃ ደስታ
3ኛ. ስለ ኦሮምያ ዓመፅና የኢትዮጵያ ሰላም
4ኛ. ውሃ መስኖ ና ኢነርጂ ም/ር 105 ለ 0
5ኛ. ስለ መቐለ ውሃ ችግር ና መፍትሔው
6ኛ. ስታድዮም ትግራይና 12ዓመት መጓተት
7ኛ. የመንግስት ሆስፒታሎችና ችግሮቻቸው
8ኛ. ስለ ማረት 18% ወለድ መሰብሰብ
9ኛ. ስለ ራያ እርሻ 15 ዓመት መጓተት
10ኛ. መተማ ላይ ስለ ተዘረፉ 400 ተጋሩ
11ኛ. ጦርነትና የትግራይ ልማት መዘግየት
12ኛ. ትግራይና ትላልቅ ኢንቨስተሮች ችግር
13ኛ. ስለ አጼ ዮሐንስ ሓወልት መሰራት
14ኛ. ስለ ትግራይና ትራንስፎርሜሽን እቅድ
15ኛ. የትግራይ ድርቅ ና ዘላቂ መፍትሔው
16ኛ. የወልቃይት ፀገደ ህዝብና ችግሮች
17ኛ. የተጋሩ ስደትና የልማት ፍላጎቶች
18ኛ. ስለ መሰረት ድንጋይና ተፈፃሚነታቸው
19ኛ. ስለ ወደ ዓፋር በግድ የተካለሉ ቦታዎች
20ኛ. የእግሪ ሓሮባ እና ኣደይ ኣልጋነሽ ፍትሕ
21ኛ. አጠቃላይ ስለ ማህበረ ኢኮኖሚያዊና ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ናቸው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጠ/ሚ/ሩ በፓርላማ “በቀጣይ የሚያሰጋን አዲስ አበባ ነው” በማለት የወለጋን አጄንዳ ለማስቀየር ሞከሩ!!

4 Comments

  1. “19ኛ ስለ ወደ ኣፋር በግድ የተካለሉ ቦታዎች” የሚግርም ጥያቄ ነው። ARENA/TPLF.

Comments are closed.

Share