October 12, 2015
5 mins read

የአዲስ አበባ የወተት ምርቶች ለጉበት ካንሠር እንደሚያጋልጡ ጥናቶች አመለከቱ

(የቀለም ቀንድ) አዲሱ የዐለም አቀፍ የእስሳት ሐብት ምርምር ኢንስቲትዩት (ILRI) ጥናት ውጤት በሰፊው የአዲስ አበባ ከተማ በሚሰራጩ የወተት ተዋጽኦ ምርቶች ላይ ከፍተኛ የሆነ የጉበት ካንሰር አጋላጭ ‹አፍላቶክሲን› የተባለ ኬሚካል እንዳለባቸው ይፋ አድርጓል፡፡ ጥናቱ ይፋ የሆነው ባለፈው ሐምሌ 2007 ዓ.ም. መጨረሻ አካባቢ ሲሆን የወተት ምርቶቹ ለተጠቃሚዎች ጤና ስጋት እንደሆኑ በሰፊው አትቷል፡፡

በጥናቱ መሠረት አፍላቶክሲን (Aflatoxin) የተባለው ለጉበት ካንሠር አጋላጭ ኬሚካል አራት ምድቦች ሲኖሩት ቢ1፣ ቢ2፣ ጂ1ና ጂ2 በመባል ይታወቃሉ፡፡ አፍላቶክሲን በየዓመቱ 90000 (ዘጠና ሽህ) ያክል ለሚሆኑ በጉበት ካንሠር በሽታ ለሚሞቱ ሰዎች ምክንያት እንደሆነ ጥናቱ አክሎ ገልጧል፤ በተለይ የህጻናትን የበሽታ መከላከል አቅም በማሳነስ የበለጠ ተጠቂ ያደርጋቸዋልም ብሏል፡፡ 

ከአፍላቶክሲን ጋር የተነካካ የእንስሳት መኖ በእንስሳት ምርት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራል፡፡ የወተት፣ የስጋና የእንቁላል ምርቶችን በሚጠቀሙ ሰዎች በተለይም ደግሞ ሕጻናትን ለማይድን ካንሠር ያጋልጣቸዋል፡፡

በኢትዮጵያ ቀደም ብለው በተደረጉ ጥናቶች በጥራጥሬ ምግቦችና በተደቆሰ በርበሬ (ድልህ) አፍላቶክሲን እንዳለ ተረጋግጧል፡፡ አዲሱ በጆርናል ኦፍ ፉድ ኮንትሮል (Journal of Food Control) የታተመው ጥናት ግን በአዲስ አበባ በሰፊው በሚሰራጩ የወተት ምርቶች ላይ ከፍተኛ የሆነ አፍላቶክሲን መገኘቱን አሳውቋል፡፡

ከአለም አቀፉ የእስሳት ሐብት ምርምር ተቋም በተውጣጡ ሳይንቲስቶች ከመስከረም እስከ የካቲት 2007 ዓ.ም ድረስ የተካሄደው ጥናት የአፍላቶክሲንን መገኘቱንና መጠኑም ምን ያክል እንደሆነ በዝርዝር አትቷል፡፡ ተመራማሪዎቹ አዲስ አበባን የመረጡበትን ምክንያት ሲያስረዱ በርካታ በአፍላቶክሲን ጋር ተያያዥነት ያላቸው የጤና እክሎች መገኘታቸው ነው ብለዋል፡፡

በጥናቱ 110 የወተት ናሙና (100 ከወተት ከብት አርቢዎችና 10 ከነጋዴዎች) እንዲሁም 156 የእንስሳት መኖ ናሙና (114 ከገበሬዎችና 42 የእንስሳት መኖ አምራች ተቋማት) ተወስዷል፡፡ 90 በመቶ የሚሆነው የወተት ምርት የአፍላቶክሲን ኬሚካል የተገኘበት ከመሆኑም በላይ የአውሮፓ ሕብረት ካስቀመጠው ስታንዳርድ በ0.05 ማይክሮ ግራም በእያንዳንዱ ሊትር ላይ ጭማሪ አለ፡፡ በእንስሳት መኖው ላይ የተደረገው ጥናት ደግሞ ሙሉ በሙሉ አፍላቶክሲን ሲገኝበት በኪሎ ግራም ከ7 እስከ 419 ማይክሮ ግራም ከመጠን የዘለለ ነው ተብሏል፡፡

ይኸው ጥናት ፋጉሎ የሚመገቡ ከብቶች አፍላቶክሲንን የመያዝ እድላቸው የሠፋ እንደሆነ አትቷል፡፡ በአንድ ኪሎ ግራም ፋጉሎ ውስጥ ከ290 እስከ 397 ማይክሮ ግራም መጠን ያለው አፍላቶክሲን ይገኛል፡፡ ተመራማሪዎቹ የጉበት ካንሠር አምጭ የሆነውን አፍላቶክሲን ለመቀነስ በእንስሳት ምርት ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች ከብቶቻቸውን ከፋጉሎ ውጭ የሆነ መኖ እንዲያቀርቡላቸው አስተያየት አቀርበዋል፡፡ በተጨማሪም አፍላቶክሲንን መከላከል የተመለከተ የግንዛቤ ሥራ መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ አጥኝዎቹ ፖሊሲ አውጭዎችና በልማት ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች ለጤና ስጋት የሆኑ ነገሮችን መረጃ መስጠት ላይ እንዲያተኩሩ በመጠቆም ምርምራቸውን ደምድመዋል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ የኢትዮጵያ የስነ ምግብ ምርምር ተቋምና የጤና ጥበቃ ሚንስቴር በጉዳዩ ላይ ያሉት የለም፡፡ የጉበት ካንሠር የተጠቃ ሰው በህይወት የመቆዬት እድሉ ከ6 እስከ 18 ወራት ብቻ መሆኑን የጤና ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡

Source:c(የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ቅጽ 3፡ ቁጥር 11)

1 Comment

  1. አፍላ ቶክሲን ክ አስፓርጊሉስ በጥራጥሬ ላይ ክርጥበት ጋር በተያያዘ ክመሻከት የሚመጣ ፒልስ አይነት የሚፈጠር መርዝ ነው:: ለምሳሌ ሽካታ እንጀራ: የንጀራ ጉዝጉዋዝ በቆልት መንስዬ ናቸው:: ወፍጮ ቤት ይሚሰሩ ሰራትኞች እዘውትረው ለብናኙ ስለሚጋለጡ በሳንባቸው ወደደም በመግባት የጉበት ካንሰር ተጠቂ ይሆናሉ:: ስለዚህ ክግጦሽ ከሳር መኖ የሚገኝ ወተት ክ እፍላ ቶክሲን የነጻ ነው:: የአበባ ተክል በአዲስ አበባ አካባቢ የሳር መኖ እጥረት ሊያስከትል ስለሚችል ወተቱን ክክተማ ራቅ ካለ እካባቢ ማስመጣቱ ላይ ትኩረት ቢደረግበት ብዙ ህይወት ለማትረፍ ይቻላል:: ሰውም አዲስ አበባ ላይ ክሚረባረብ ሌሎች አማራጭ ከተሞችንም ለመኖርያነት ቢገለገል ሌሎች ገና ካልተገለጡ በሽታዎች ሊጠበቅ ይችላል::

Comments are closed.

Previous Story

በአቃቂ የሞባይል ስልኩ ቻርጅ እያደረገ ሞባይል ሲያናግር የነበረው ግለሰብ በኤሌክትሪክ ተይዞ መሞቱ ተሰማ (Audio)

tplf rotten apple 245x300 1
Next Story

ለማይቀረው እና ለመጨረሻው ትግል ከዚህ ፍሽስት ከወያኔ አገዛዝ ጋር ለሚደረገው ትንቅንቅ እራሳችንን በተገቢው መንገድ እናዘጋጅ !!!

Latest from Blog

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት  አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop