August 18, 2015
2 mins read

የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ እድር ላይ ጥያቄ አነሳህ ተብለው ታሰሩ

(ነገረ ኢትዮጵያ) በባሌ ዞን ሰልጣ ቀበሌ፣ ሲናና ወረዳ የሰማያዊ ፓርቲ የፓርላማ ዕጩ ተወዳዳሪ የነበሩት አቶ ወርቅነህ ጋድይ አያና የእድር ስብሰባ ላይ ጥያቄ ጠይቀሃል ተብለው መታሰራቸውን የሰማያዊ ፓርቲ የዞኑ አስተባባ አቶ ደመላሽ በቀለ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ በተለይ ከምርጫው በኋላ ካድሬዎች አቶ ወርቅነህ እድርን ጨምሮ ከማህበራዊ ጉዳዮች እንዳይሳተፉ ጫና ሲያደርጉባቸው እንደነበረም ተጠቅሷል፡፡

ሆኖም የአካባቢው ህዝብ ‹‹በፖለቲካ መሳተፍ ህገ መንግስታዊ መብቱ ነው፡፡ እድር ደግሞ ማህበራዊ መብቱ በመሆኑ መሳተፍ አለበት›› በማለቱ እስካሁንም የእድር አባል ሆነው ቢቀጥሉም በእድሩ አካሄድ ጥያቄ አለኝ በማለታቸው ‹‹ለምን ጥያቄ ትጠይቃለህ?›› ተብለው እንደታሰሩ አስባባሪው ገልፀዋል፡፡ አቶ ወርቅነህ ጋድይ በአሁኑ ወቅት በሲናና ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንደሚገኙ ታውቋል፡፡

በሌላ በኩል የአስተዳደር አካላት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ላይ በሚፈፅሙት በደል ምክንያት ከትግል ውጭ ፍትህ እናገኛለን ብለው እንደማያምኑ አቶ ደመላሽ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

Previous Story

ዛሬ የአጼ ምኒልክ ልደት ነው

Benishangul Gumuz
Next Story

በቤንሻንጉል ጉሙዝ የተገደሉት 11 ሰዎች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊጨምር እንደሚችል ነዋሪዎች ተናገሩ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop