መነሻውን ከህውሃት ጉያ ውስጥ ያደረገው የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ታሪክ መፅሃፍና አነጋጋሪው ክህደት

በሰሜን አሜሪካና በተቀረው ዓለም የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ህብረት

የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል በሃሰት ውንጀላ በጅምላ ወደ ህውሃት ማጐሪያ እንዲጋዝ ከተደረገና በኋላም በጨፍጫፊነት ተፈርጆ በአዋጅ ከስራ ውጪ እንዲሆን የፈረደበትን ግንቦት 1983 ዓ/ምን እሳቤ በማድረግ ከምስረታው እስከ አሳዛኝ ብተናው ድረስ የነበረውን ታሪክ በመፅሃፍ መልክ ለማዘጋጀት የተደረገው ጥረት አስርተ ዓመታትን አስቆጥሯል።

በቅብብሎሽ አንዱ በፃፈው ላይ ሌላኛውም እያከለ የተቋሙን ታሪክ ወደ ሙሉዕነት ለመቀየር ከፍተኛ ድካም ተደክሞበታል ። መፅሃፉን አንድ ሰው ያሳተመው ይምሰል እንጂ ባለቤትነቱ በህብረት ነው ።

ከእዚህ ወደ እዚያ ሲንከባለል የቆየው የመፅሃፍ ዝግጅት መነሻ አየር ኃይሉ በደረሰበት ዕጣ ፈንታ በእጅጉ በመቆጨት –

1. የአገር አንድነትን ለማስከበር የተሰዋበትን
2. በአኩሪ ታጋድሎውም በህዝብ ዘንድ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ አክብሮት የተቸረበትን ፣
3. በአሳዛኝ መልኩ ስመጥር ታሪኩን በሬት በመለወስ በትውልድ እንደ ጨፍጫፊና ወንጀለኛ እንዲቆጠር የተደረገበት ሁኔታ ሌት ተቀን እንቅልፍ የነሳቸው የሰራዊቱ አዛውንት አባላት ተሰባስበውና ተማክረው እውነተኛውን ገፅታ ለማቅረብ ጊዜአቸውንና ሃብታቸውን መስዋዕት አድርገዋል ።

ይህንን በጐ ዓላማ ይዞ የተነሳው የታሪክ መፅሃፍ ታትሞ አደባባይ ከመውጣቱና በዚያ ታላቅ የሃገር ሃብት የሆነ የመከላከያ ተቋም ላይ የተወሰደው ፖለቲካዊ ብያኔ የእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ስሜትና ቀልብ እንደሚስብ ፣ ሃላፊነት የጐደለውም ፍርደ ገምድላዊ ብያኔ ምን ያክል አገር የማፍረሱ አካል መሆኑን ቁልጭ አድርጐ በማሳየት በስልጣን ላይ ያለውን ዘረኛ ስርዓት ከማሳጣቱ በፊት ፖለቲካዊ ማድበስበስ ተደርጐ ለዳግም ክህደት ተዳርጓል ።

የተቃውሞው መነሻ –

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ሙሉዕ ታሪክ ተፅፎ ለትውልድ ቢተላለፍ የሚጠላ አንድም ኢትዮጵያዊ እንደማይኖር ሁሉ ታሪኩ ጐዶሎና በፖለቲካዊ ደባ የተንሸዋረረ እንዲሆን ሲፈረድበት ዝም ብሎ መመልከት ደግሞ ለአገራቸው መስዋዕት የሆኑ ዛሬ ግን እራሳቸውን ሊከላከሉ የማይችሉትን ሰማዕታትንም አገርንም መክዳት ነው ።
የአየር ኃይል ታሪክ በቀዳማዊ ኃ/ስላሴ ዘመነ መንግስት መመስረቱ ብቻ ሳይሆን በዘመነ ህውሃት/ኢህአደግ ዘመን በውርደት መፍረሱን ፣ በአባላቱም ላይ የደረሰው ወደር የለሽ ሰቆቃና እንግልት ፣ እስርና ረሃብን የማይገልፅ የታሪክ መፅሃፍ ሙሉዕነቱ የተጓደለ ብቻ ሳይሆን እውነትን ፈፅሞ ለመጋፈጥ የሸሸ አሳዛኝ አድርባይነት ይሆናል ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከቤሩት የተሰማ አሰቃቂ መረጃ (ይህን ቪድዮ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ እንዲያዩት አይመከርም)

የአየር ኃይሉን አመሰራረትና የስልጠና ታሪክ ማሳየት ብቻ ሳይሆን አኩሪ ታሪክ የፈፀሙ ጀግኖች እኩሌታው በአሳዛኝ ሁኔታ ከአገር እንዲሰደዱ ተደርጐ ፣ ቁጥሩ ቀላል ያልሆነው ደግሞ በፍርደ ገምድልነት የሞትና የእድሜ ይፍታህ ፍርደኛ ሆነው በመካከላችን ቆመው በሉበት ሁኔታ ፤ ከሁሉም በላይ ድሃዋ ኢትዮጵያ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ የደከመችበትንና የሃገር ሃብት የፈሰሰበትን ፣ ሃላፊነት በጐደለው ስርዓት ገደል እንዲገባ የተደረገበትን እንዳላየና እንዳልሰማ በዳሰሳ ብቻ ማለፍ ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል ነው ።

ለመሆኑ በወንጀለኝነትና በጨፍጫፊነት ተወንጅሎ ለነጋሪ እንዳይተርፍ ሆኖ በጅምላ ታስሮ ፣ በሞትና በእድሜ ልክ እስረኝነት ፍርድ የተፈረደበት የአየር ኃይል ታሪክ መነሻውን ከህውሃት ቤተመንግስት እንዴት አደረገ ?

እንዲህ የሚከበርና ለአገርም አለኝታ እንደነበረ የሚተረክለት አየር ኃይል ስለምንስ ዛሬ ድረስ በጅምላ ወንጀለኛ የሚለውን ስም እንዲሸከም ተደረገ ? እንዴትስ አባላቱ የሞትና የእድሜ ልክ ፍርደኛ ሆነው ሊቀሩ ቻሉ ? በምንስ መመዘኛ አየር ኃይሉ በጅምላ ይህንን ያክል ፍዳና መከራ ሲሸከምና ሲከፍል ከዳር ሆነው የተመለከቱት የህውሃት/ኢህአዴግ ባለስልጣናት መፅሃፉ ሲመረቅ በክብር እንግድነት ተስተናገዱ ? ጥቂት ከዘረኛው ስርዓት ጋር የደም ትስስርና ዝምድ ካላቸው የቀድሞው ሰራዊት አባላት በስተቀረ ብዙሃኑ ተወንጃይ የአየር ኃይል አባላትስ የታሉ ? እንዴትስ የዚህ የተወነጀለው አየር ኃይል አባላትና የቀድሞው ስርዓት ጀነራል መኰንኖች የቤተ መንግስት ደጃፍ ያለከልካይ ክፍት ሆነላቸው ?

እነዚህን የመሳሰሉትን ሁሉ ያላገናዘበና ምላሽ ያልሰጠ ፣ ይልቁንም ዘረኛው ስርዓት በጐ እንደሚሰራ ለማስመሰል የሚደርግ ርካሽ የልወደድ ባይነት የተንፀባረቀበት ሆኖ አግኝተነዋል ።

አሁንም ታሪኩ ለትውልድ እንዲተላለፍ የሚደረገውን ጥረት እያደነቅን ነገር ግን ምስረታውንና እድገቱን ለመዘከር የደፈርነውን ያክል በአሳዛኝና ኃላፊነት በጐደለው መልኩም እንዲፈርስና እንዲወድም መደረጉንም ለመግለፅ ድፍረቱ ያስፈልገናል እያልን የህውሃትን ቡራኬ ለማግኘት ሲባል ብቻ ይህንን ታላቅ ዓላማና ስራ ወስዶ ህውሃት ጫማ ስር ማዝረክረኩን አጥብቀን እየተቃወምን ይህ የማይሆን ከሆነ ግን የቀድሞውን የኢትዮጵያ አየር ኃይል አባላት ያላማከረና ያልወከለ ተግባር በመሆኑ አጥብቀን እናውግዛለን ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የታከለ አስደንጋጭ ዝርፊያ ሲጋለጥ! - እናኑ ጥላሁን

በሰሜን አሜሪካና በተቀረው ዓለም የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ህብረት

4 Comments

  1. Hi. I am writing in behaf of concerned former Ethiopian Air Force. I saw an article posted in your website regarding the new coming book of story of Ethiopian Air Force. I have the privilege to read the book and found it very interesting. I don’t think the person who posted the article read the book. I want Ze-habesha editor read the book first and has his own judgement before posting the biased article and coming from un recognized and unknown association. This will undermine the website, if it’s a one sided and biased
    Regards

  2. Sunday, May-24-15

    ህወሃት ጉያ ተፃፈ ስለተባለው የቀድሞ አየር ሃይል ታሪክ ለተፃፈው ተቃውሞ የግል አስተያየት፤

    በመጀመሪያ ደረጃ እስከ ዛሬ ድረስ በታሪክ ተመዝግቦ የተቀመጠ የአንድ ድርጅት ታሪክ ለምን ተፃፈ ብሎ ተቃውሞ ያስነሳ ጉዳይ ስለመኖሩ አልሰማሁም።እርግጥ ዘርን፤ ፆታን ፤የሃገር ሚስጢርን በተመለከት ስለሚፃፉ ነገሮች ዲሞክራቲክ በሆኑ አገሮች ተቆጣጣሪ እና ጉዳዩን ወደ ህግ የሚያደርስ ተቋም ስላለ እዳው ገብስ ነው ።ለነገሩ አሳታሚ ድርጅቶችም ራሳቸው እንደዚህ አይነቱን ሁኔታ በማተም የራሳቸውንም ሆነ የንግድ ተቋማቸውን አደጋ ውስጥ አይከቱም።
    አሁን ሰሞኑን ተፃፈ የተባለው መፅሃፍ ለጊዜው ግማሹንም ቢሆን ለማንበብ እድል አግኝቻለሁ።መፅሃፉ በመጀመሪያ ገፁ ላይ በተደጋጋሚ ለአምስት ጊዜ ያህል ተሞክሮ እንደ አለመታደል ሆኖ ሞካሪዎቹ በሙሉ ፍፃሜውን በህይወት ቆመው ማየት ስላልቻሉ የመፅሃፉን መጨረሻ ማየት እሰክ አሁኑ ሰሞን ድረስ አልተቻለም ነበር።ይን በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቁን ድርሻ የሚይዘው እንኳን አባላቶቹ የውጪው ሰው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁሉ የሚኮራበት የአየር ሃይላችን ታሪክ ተፅፎ መውጣቱ ብዙውን ሰው በተለይም እኛ አባላቶቹን ያኮራናል ብየ ገምቼ ነበር።
    በተቃራኒው ግን ያየሁት ነገር አንድ ራሱን አድራሻውን ወይንም የድህረ ገፅ ቦታውን ፈልጎ ለመሞገት ከዚህ ባነሰ መልኩም ቢሆን የስልክ እንኳ የመገኛ አድራሻ የሌለው አለም አቀፋዊ ስፋት ያለኝ ድርጅት ነኝ የሚል ድርጅታዊ አርማም ሆነ ድርጅታዊ መተዳደሪያ ደንብ የሌለው (ቢኖረው ለማወቅ እድሉ ሊኖረኝ ይገባ ነበር ብየ አምናለሁ)አንድ አካል ስለ መፅሃፉ እርስ በርሱ የተጣላ አነስተኛ መጣጥፍ ፅፎ ማየቴ ገርሞኛል አሳዝኖኛል በመጨረሻም አፍሬያለሁ።
    የመፅሃፉን ሙሉ ጭብጥ ወደፊት የምመለስበት ቢህንም አሁን በግርድፉ ላይ ላዩን እንዳየሁት ፀሃፊውም ክስማቸው ጎን እንዳስቀመጡት መፅሃፉ ከ1921-1928 ያለውን ታሪኩን ነው የሚተነትነው፤ ይህ በአስራ አምስት ምእራፍ ተከፋፍሎ የተዘጋጀ መፃሃፍ ከምስረታው ጀምሮ እስከ አየር ሃይሉ እሰከፈረሰበት ድረስ ያለውን ታሪክ፤ ከዘመቻ ግዳጅ ጀምሮ የአየር ሃይሉን አሰራር ከዚህ በፊት በስማ በለው ይሰማ ከነበረው የበለጠ ዘርዘር አድርጎ ፅፏል።ዝርዝር ሁኔታ ላይ ስህተት ካለ ወይም የተጋነነ ነገር ካለ ወይም በአንድ በኩል ወገናዊነት ካለው መፅሃፉ ከወጣ በኋላ ህዝቡ ካነበበው በኋላ መነጋገር ሲቻል ገና መፅሃፉ ህዝብ እጅ ላይ ሳይደርስ የፀሃፊው የኮለኔል አስፋው አየልኝ እና አጋሮቻቸው(የኮሚቴአቸው) ፍላጎት መልክት ምን እንደሆን ሳይታወቅ በጥቅሉ ህወሃት ጉያ የታተመ መፅሃፍ ነው ብሎ መደምደም አንድ ፊደል ቆጥሬያለሁ ከሚል አልፎም አየር ሃይል የሚያክል ተቋም ውስጥ ከፊደል ሌላ ሙያ ተምሬያለሁ የሚል ግለሰብም ይሁን ቡድን ማየቴ ገርሞኛል።ለነገሩ የመፅሃፍ መታተሚያው ጉያ የት እንደሆነ እኔ አላውቅም ።መፅሃፍ የሚታተመው ማተሚያ ቤት ነው አራት ነጥብ።
    ከዚህ በፊት በግል ጉዳያችን በምናወራበት መድረክ የዋሽንግተን ዲሲው የቀድሞው አየር ሃይል ማህበር ባዘጋጀልን መድረክ ላይ ስንወያይ የጠየቅናቸው ጥያቄዎች ነበሩ።ፀሃፊውም በግል የመፅሃፉ ሽያጭ ወደ ፊት እናቋቁማለን ለሚሉት የቀድሞው አየር ሃይል ቬተራን አሶስየሽን መገንቢያ እንደሚሆን የተናገሩ ይመስለኛል።ይህን ማህበር በተመለከተ የተጠየቁ ጥያቄዎች አሁንም አየር ላይ ሲሆኑ መፅሃፉን ግን በተመለከተ ሙሉ ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።ከዚህ መፅሃፍ ህወሃት የተባለው ቡድን ጥቅም ያገኛል ብለን የምናምን ከሆነ ፓለቲካውም፤ የሂሳብን ቁጥርም ወይም በአየር ሃይል ቋንቋ “ኤቲክሱ” አልገባንም ማለት ነው ።መልቲ ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንዳለው በአደባባይ የሚናገር ድርጅት መፅሃፍ ፅፌ አተርፋለሁ ብሎ የሚለፋ አይመስለኝም።
    ይልቁኑም ቤቱ ትኋን አለው ብሎ ራሱ ቤቱን እንዳቃጠለው ጅል ሰውየ ፤ይህን የሚያክል የተድከመበት መጽሃፍ እንደ አልባሌ ነገር ባለቤት እንደሌለው የመንገድ ላይ እቃ በነፃ በኢንተርኔት ላይ መልቀቅ ትልቅ ስህተት ነው ።ለነገሩ ነውር ማለት ክዚህ ሌላ ተቀራራቢ ትርጉም ሊኖረው የሚገባ አይመስለኝም(ይህን ያደረጉ ሰዎች ስለ ክብራችን ሲሉ እንዲያነሱት እጠይቃለህ፤እለምናለሁ)።አየር ሃይልነታችንም የትም ቦታ እንደዚህ አይነቱን ነገር አስተምሮናል ብየ አልገምትም።አለመግባባቱ እንዳለ ሆኖ መከባበሩ ዘላለማዊ ነው ብየ የማምን ሰው ነበርኩ። አሁን ግን ጥርጣሬ ገብቶኛል።ያ ካኪ የደበቀው ፀባያችን ከሩብ ምእተ አመት በኋላ ድንገት ብልጭ ማለቱ አሳዝኖኛል፤ለካንስ አንተዋወቅም ነበር።
    በመጨረሻም ይህን መፅሃፍ በተመለከት አውቀንም ይህን ሳናውቅ በአደባባይ ላይ የፃፍነው ነገር እንዲነሳ እየጠየቅሁ፤ስለመጽሃፉ ጠቅላላ መልክት ብዙሃኑ ካነበበው በኋላ ወደ ውይይት ብንሄድ መልካም ነው በማለት ከ1983 በኋላ ላለው ታሪክ ደግሞ አየር ሃይሉ ከፈረሰ በኋላ እንደ አዲስ ተቋቋመ ካሉን ጊዜ ጀምሮ ግልጋሎት ሲሰጡ የነበሩ ግለሰቦች ውስጡ የነበረውን አስራር በቀጣይ ይጽፍልን ዘንድ ምኞቴ መሆኑን እገልፃለሁ።
    ከታዛቢ

  3. First of all, the comment was not written by the Association of the former memebrs of the ETAF, it was written by a single person who has an ulterior motives. The book as it shows on the front page encompasses the history of Ethiopian air force from 1921 to 1983 (Ethiopian Calendar). And the book was organized by highly educated and professional air force members. All of them have track record to show who they are, they served their country from young age through old age, and they sacrificed their entire life to safe guard and protect Ethiopia. The full book review will come soon but for now everybody has to know that there is a conspiracy going on for the book not to be distributed among the Ethiopian people. Anybody with the right mind would not believe the clam that “Woyane wrote the book” How can Woyane write good things about the Former Ethiopian Air Force? Is the writer trying to tell us Woyane is now telling the true history of Ethiopia? In time everything will come out including the writer’s background and his motives.
    I wish ECADFORUM at least verify the truth before posting such lie. Just read the book and judge for yourself. I had the priviledge to read the book and found it fascinating. Once you start reading, you wouldn’t put it down, over 700 pages of 70 years history and how it was destroyed overnight by Woyane.

  4. ከላይ የተሰጠውን አስተያየትና ዋናውን መግለጫ አነበብኩት ፥ በኋላም ሃሳብ የሰጡትን ሰው ማንነት እራሱ ጽሁፋቸው ውስጥ አገኘሁትና ያለማፈራቸው እኔን አሳፈረኝ ፡፡
    ዋናው መግለጫ ሁለት መሰረተ ሃሳቦችን በግልጽ አስቀምጧል ፡፡
    1- የአየር ሃይሉ ታሪክ መጻፉን እንደግፋለን ይላል ፡፡ እንዴት ታሪክ እንዳይጻፍ ያከላክላሉ የሚለው ሰንካላ ሃሳብ በመሆኑ መልስ አይገባውም ፡፡
    2- ሁለተኛው ሃሳብ ውሃ ይቋጥራል ፡፡ ለምን አየር ሃይልን የሚያክል ብሄራዊ የመከላከያ ተቋም እንዲገደል ፥ እንዲሰደድ ያደረጉ የህውሃት ባለስልጣኖች እግር ስ ወደቀ ነው ፡፡ ይሄንንም እንደክህደት የክህደቱም ፊታውራሪዎች ደም ከውሃ የወፈረባቸው ምንደኞች ናቸው ይላል ፡፡

    በእኔ አስተሳሰብ ገዳይ ካሳ እንዲቀበል ሲፈረድበት ማየት ያማል ፡፡ ነገሩን እየተቃወሙ ያሉትን ጊዜ ሰጥቶ ማዳማዳመጥ ሳይበጅ አይቀርም ፡፡

    አባ

Comments are closed.

Share