Hiber Radio: ኢትዮጵያ ከሰሜ ኮሪያ መሳሪያ መግዛት አለመግዛቷን ምርመራ መጀመሩ; እንግሊዝ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የ4.9 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ማቋረጧ; 125 ኢትዮጵያውያን ወደሃገራቸው መላካቸው; የኢትዮጵያን የልብ ትርታ ለማድመጥ ግብፅ የአባይ ወንዝን ለመገደብ ለደቡብ ሱዳን 2 ቢሊዮን ዕርዳታ መመደቧ; ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ለመጠየቅ ቃሊቲ የሔዱ መከልከላቸውና ሌሎችም

/

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
ህብር ሬዲዮ የካቲት 22 ቀን 2007 ፕሮግራም
እንኳን ለ119ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሰዎ

አቶ ኦባንግ ሜቶ በህብር ሬዲዮ 5ኛ አመት እና 119ኛ የአድዋ ድል በዓል በተከበረበት ወቅት በቬጋስ ተገኝተው ያደረጉት ንግግር(ሙሉውን ያዳምጡ )

<...ኢትዮጵያውያን የአድዋን ድል ብቻ መዘከር ሳይሆን በአድዋ ሳቢያ የፋሺስቱ ጣሊያን አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ከ40 ዓመት በኋላ መቶ የጨፈጨፈበትን ንብረት የዘረፈበትንና ያወደመበትን የግፍ ድርጊት በአለም አቀፍ ደረጃ ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኝና የኢትዮጵያም ተገቢውን ካሳ እንድታገኝ የጀመርነውን ጥረት ማገዝ...የተቃውሞ ፊርማውን ...> አቶ ኪዳኔ አለማየሁ የአለም አቀፍ ፍትህ የኢትዮጵያ ጉዳይ ዋና ስራአስኪያጅ ከተናገሩት የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡ )

ስለ ፕሮስቴት ካንሰር ከዶ/ር ሙሉጌታ ካሳሁን ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ
አድዋ ግጥም በመርሻ አያሌው
ጣይቱ ግጥም በሐይማኖት ይመኑ

(ልዩ ዘገባ የሩሲያው የተቃውሞ መሪ መገደልና የቀሰቀሰው አለም አቀፍ ተቃውሞ)
ሌሎችም
ዜናዎቻችን:-
የእንግሊዝ መንግስት ለኢትዮጵያ አገዛዝ የሚያደርገውን የ4.9 ቢሊዮን ዶላር ዕርዳታ ማቋረጡን ገለፀ።

ኢትዮጵያ ማዕቀብ ከተጣለበት ሰሜን ኮሪያ የጦር መሳሪያ ትግዛ ወይም አትግዛ ለማጣራት የተባበሩት መንግስታት ምርመራ ጀመረ

አንድ ከፍተኛ የደቡብ አፍሪካን ዲፕሎማት ከሁለት ዓመት በፊት አዲስ አበባ ላይ ለመግደል በተጠነሰሰ ሴራ እጇ አለበት የተባለችው ሱዳን አቋሟን ገለፀች።

ግብፅ የአባይ ወንዝን ለመገደብ ለደቡብ ሱዳን 2 ቢሊዮን ዕርዳታ መደበች:: የኢትዮጵያን የልብ ትርታ ለማዳመጥ ነው ተብሏል።
የመኢአድ በተለያየ ደረጃ ያሉ ከመጭው የይስሙላ ምርጫ እራሳቸውን ማግለላቸውን ቀጥለዋል ፓርቲው በጉዳዩ ላይ የሰጠው መግለጫ የለም።

125 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከየመንና ከታንዛኒያ ወደአገራቸው እንዲመለሱ ተደረገ።

የአገር ቤቱ አገዛዝ የፖለቲካ ጥገኝነት የሰጣቸው የቀድሞው የየመን ፕሬዝዳንት ቢሊየነር መሆናቸው ተጋለጠ።

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ለመጠየቅ ቃሊቲ የሔዱ ተከለከሉ። በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞችና ጦማሪያን ዛሬም የአገራቸው የነፃነት ጉዳይ እንደሚያሳስባቸው ገለፁ::

“የነፃነት ጥያቄዎች እስኪመለሱ ሙያዊ ነገሮችን ወደ ጎን ማድረግ ያስፈልጋል:
ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ።
በእስር ላይ የሚገኙት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያንና ጋዜጠኞች ዛሬም የአገራቸው የነፃነት ማጣት እንደሚያሳስባቸው ለጥየቃ ለሄዱ ጋዜጠኞች ገለፁ

ተጨማሪ ያንብቡ:  በአሜሪካ ሕግ አጽዳቂዎች ምክርቤት (ሰኔት) 17ኛ ኮንግረስ ተርጓሚ - ጥበቡ ሞላ

1 Comment

  1. ህብር ራዲዮ የሚያቀርበው ዝግጅቶች በይዘቱ በጣም ጥሩ ነው:: ነገር ግን ዜና ሲያነቡ ያልተዘጋጁ ነው የሚመስለው:: ከዝግጅቱ በፊት ቢያንስ ሁለቴ አንብቡት ለአድማጭ ከማቅረባቹ በፊት:: አለበለዚያ ረጋ ብላቹ አንብቡት ቃላቱን ለመለየት ጊዜ እንድታገኙ:: አንዴ መሳሳት ምንም አይደለም ግን ሲደጋገም ጥሩ አይሆንም:: በተለያየ ቀን በመፈጠሩ ብቻ ሳይሆን በአንድ አርስተ ዜና እራሱ የመቸኮልና ቃላትን ለመለየት ሲቸገሩ ማየት እንድ አድማጭ ጆሮ ይኮረኩራል:: በዚህም ምክንያት ይህን አስተያየት ለመስጠት ተገድጃለሁ:: እንደሚስተካከል ተስፋ አደርጋለው:: ዘ-ሓበሻ ከህብር ጋር ቅርበት ስላላቹ ሹክ በሉልን:: ዘ-ሓበሻ ላይ ድግሞ የዜና ምንጭን የመጥቀስ ችግር አልፎ አልፎ ይታያል:: ይሄ ሙያዊ ግዴታ ነው::

Comments are closed.

Share