Hiber Radio: የጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ከአስመራ መልስ ቃለምልልስ…የእንግሊዝ ባለስልጣናት በአንዳርጋቸው ጉዳይ መወዛገባቸው… በአ. አ. ደም መፍሰሱና ቃለምልልስ.. የቱርኩ ፕ/ት በኢትዮጵያ ሃይማኖታዊ ት/ቤቶች እንዲዘጉ መጠየቃቸው… በደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያውያን መደብሮች መመዝበራቸው… እና ሌሎችም

/

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
የህብር ሬዲዮ ጥር 17 ቀን 2007 ፕሮግራም

<<..ድብደባውን የጀመሩት ከኔ ነው ።ራሴን እስክስት ድረስ በርካታ ሰዎች ሲደበደቡ አይቻለሁ... ግራ እጄ ተሰብሯል አሁን ህመም የማይሰማኝ ቦታ የለም…>>

ጋዜጠኛ ስለሺ ሀጎስ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ጋዜጣ አዘጋጅ በአንድነት ሰልፍ ላይ በአገዛዙ ፖሊሶችና ደህንነቶች ከፍተኛ ድብደባ ከደረሰባቸው አንዱ (ሙሉውን ያዳምጡ )

<<...ስድስት ፖሊሶች ከፍተኛ ድብደባ አድርሰውብኛል በሰልፉ ላይ ያልተደበደበ አልነበረም...በዚህ አገር ሰላማዊ ትግል...>> ወይዘሪት መስከረም ያደርጋል የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ጋዜጣ አምደኛ እና የፓርቲው አባል (ሙሉውን ያዳምጡ )

ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ከኤርትራ መልስ ስለ ቆይታው ከሰጠን አጠር ያለ ቃለ ምልልስ (ሙሉውን ያዳምጡ )

<<...የነፃነት ጥያቄ በጉልበት በመሳሪያና በድብደባ ሊፈታ አይችልም...>> አቶ በላይ ፈቃዱ የአንድነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት (ሙሉውን ያዳምጡ )

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

አንድነት ያነሳሁት የፍትሕ ጥያቄ በአገዛዙ ደም የማፍሰስ እርምጃ አይቀለበስም ትግሉ ይቀጥላል አለ

የዘጠኙ ፓርቲዎች ትብብር በአንድነት ዛሬ በአንድነት ፓርቲ ላይ የተፈፀመውን አረመኔያዊ እርምጃ አወገዘ

በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ በርካታ የኢትዮጵያዊያን መደብሮች በወረበላዎች ተመዘበሩ

አንድ ኢትዮጵያዊ ባለሀብት በዘራፊዎች ተገደለ

ፖሊስ ከዘራፊዎች ጎን መቆሙ ቁጣን ቀስቅሷል

የቱርኩ ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ የሚገኙ ሀይማኖታዊ ት/ቤቶች እንዲዘጉ በመጠየቃቸው ተቃዋሚዎች ቁጣቸውን አሰሙ

የእንግሊዝ ባለስልጣናት በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጉዳይ ተወዛገቡ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ
https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-012515-020115

ተጨማሪ ያንብቡ:  በምስራቅ ጎጃም ዞን አርሶ አደሮች በጅምላ እየታሰሩ ነው ተባለ • ዜጎች በፖለቲካ አመለካከታቸው ከቀያቸው እየተፈናቀሉ ነው

1 Comment

Comments are closed.

Share