January 18, 2015
2 mins read

መንግስት የሕወሓት አባሉን ዳኛ ልኡል ገ/ማርያም በከፍተኛ ወጪ እያሳከመ ነው

(ከኢየሩሳሌም አርአያ)

ልኡል ገ/ማርያም የተባለ የሕወሐት አባልና ዳኛ በከፍተኛ ወጪ በመንግስት እየታከመ መሆኑ ታውቋል። በዶ/ር ታዬ ወ/ሰማያት፣ በቅንጅት አመራሮችና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ እድሜ ልክና ሞት የፈረደ ነው።

ዙቤር የተባለ ሃብታም የገዛ ጓደኛውን በውሻ እያስነከሰ በጥይት ደብድቦ ከገደለው በኋላ ጉዳዩ የቀረበው ልዑል ዘንድ ነበር። የፈርደበት 6 አመት በማለት ሲሆን ከፍተኛ ገንዘብ ተቀብሎ ይህን ፍርድ ተብዬ እንዳስተላለፈ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ ያስታውሱታል።

ይግባኝ የተጠየቀበት ዙቤር 22 አመት ፍርድ እንደተላለፈበትም ይታወሳል። ገዢው ፓርቲ ፖለቲካዊ ነክ ክሶችን በቀጥታ የሚመራው ወደ ልዑል ሲሆን አስቀድሞ ምን ፍርድ መስጠት እንዳለበት ተያይዞ ይነገረዋል። ዳኛ ተብዬው ልዑል ገ/ማርያም በልጆቹ እናት ላይ 5 ሴቶች በመወሸሙ ባለቤቱ ፍቺ ፈፅማለች። ባለፈው አመት በጠና በመታመሙ ወደ ደቡብ አፍሪካ ተልኰ ከፍተኛ ህክምና የተደረገለት ሲሆን ለህክምናው 550ሺህ ዶላር ወጪ እንደተደረገ ተረጋግጧል። የስኳር ህመምተኛ የሆነው ልዑል በዘመኑ በሽታ ሳይለከፍ አይቀርም የሚሉ የቅርብ ምንጮች ቀደም ሲል የተደረገለት ህክምና በቂ ለውጥ ሊያመጣለት ባለመቻሉ በአሁኑ ወቅት ታይላንድ ባንኮክ በህክምና ላይ እንደሚገኝ ማረጋገጥ ተችሏል።

በባንኮክ 7 ወሩ ሲሆን እስከአሁን 4ሚሊዮን 200ሺህ ብር ወጪ እንደተደረገለት ታውቋል። መንግስት አንድ የጠ/ፍ/ቤት ዳኛ እንኳ በአገር ውስጥ እንደማያሳክምና እንደማይረዳ እናውቃለን ያሉ የቅርብ ወገኖች ለሙሰኛውና ፍርደ ገምድሉ ልዑል ገ/ማርያም ይህን ያክል ወጪ መደረጉ አሳዛኝ ነው ብለዋል።

3 Comments

  1. A worthless person, a wicked man, goes about with crooked speech, winks with his eyes, signals with his feet, points with his finger, with perverted heart devises evil, continually sowing discord; therefore calamity will come upon him suddenly; in a moment he will be broken beyond healing. There are six things that the Lord hates, seven that are an abomination to him:
    (proverbs 6:12-16)
    you reap what you saw

  2. ሞት ለፍርደ ገምድል ልዑል እንደ ጌታው ግራዚያኒ ዱቼ መለስ ዜናዊ!!!!!!!

Comments are closed.

arbegnoch
Previous Story

የኢ.ሕ.አ.ግ. ዓለም አቀፍ ኮሚቴ እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት

Next Story

Hiber Radio: የአፋር ነፃ አውጭ ግንባር ማስጠንቀቂያ… የኤርትራና የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች በአስመራና በአዲስ አበባ… አንድነትና መኢአድ ምርጫ ቦርድን መክሰሳቸው… ኢሳያስ አንድ የሱዳን ጀነራል ኢትዮጵያን አጥፋ ብሎኝ ነበር ስለማለታቸው… ሌሎችም

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop