ሪያድ ከተማ በኢትዮጵያውያን የብሄር ግጭት ታመስች ! በግጭቱ ሁለት ኢትዮጵያውያን በጩቤ ተወግተው ሲሞቱ 4 ቆስለዋል።

ሰሞኑንን በሪያድ ከተማ ልዩ ስሙ መንፉሃ እይተባለ የሚጠራ አካባቢ በኢትዮጵያውያን መሃከል በተቀሰቀሰ የእርስ በእስር ግጨት ህይወት መጥፋቱን ምንጮች ገለጹ። ግጭቱ ካገረሽ ወዲህ በተለይ የዛሬ ሳምንት አርብ ምሽት በተጠቀሰው አካባቢ ከ 10 የሚበልጡ ሳንጃ የታጠቁ ኢትዮጵያውያን «ሻራ ኢሽሪን » እየተባለ በሚጠራ መንገድ ዳር ወደ ሚገኝ የቴለፎን ማስደወያ ማዕከል በማቅናት ላይ በነበሩ 4 ባላጣዎቻቸው ላይ ጥቃት ለመፈጸም ባደረጉት ሙከራ በተከስተ ትንቅንቅ በአካባቢው በተነሳ ሁከት አንድ እድሜው በ 30 ዎቹ የሚገመት ወጣት አንገቱ ላይ በሳንጃ ተወግቶ ወዲያ ሲሞት ሆዱ ላይ የተወጋ ኢትዮጵያዊ ወጣት ነፍሱን ለማዳን በተደረገ ርብረብ ወጣቱ በክፉኛ ሁኔታ ተጎድቶ ስለነበር ሆስፒታል እንደደረሰ ህይወቱ ማለፉን ለማወቅ ትችሏል።

ይህ በዚህ እንዳለ አካባቢው ፈጥነው በደረሱ የሳውዲ ፖሊሶች ቁጥጥር ስር የዋሉ በእርስ በእርስ ግጨቱ የተሳታፊ 4 ኢትዮጵያውያን በሰውነታቸው ላይ ከደረሰው መለስተኛ ጉዳት አገግመው በአሁኑ ሰዓት ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ ። በኢትዮጵያኑ መሃከል በሚከስት ግጨት በደም የተጨማለቀ በጠራራ ፀሃይ በሳንጃ አንጀቱ የተዘረገፈ ሬሳ መንፉሃ ውስጥ ማየት የተለመደ መሆኑን የሚገልጹ የአይን እማኞች የዛሬ አመት የሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች በኢትዮጵያኑ ላይ በወሰዱት እርምጃ በጉሩፕ ይከስት የነበረ የዕለት ተዕለት ዘግናኝ ትእይንት ለወራት ጋብ ብሎ ቢቆይም ሰሞኑንን በአዲስ መልክ በማገርሸቱ የአካባቢውን ነዋሪ ክፉኛ አስደንግጦል ብለዋል።

 

በሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን መሃክል በሚከስት ግጨት ህይወቱ የሚያልፈውን ወገን ለማታደግ የአካባቢው የሃይማኖት አባቶች እና የሃገር ሽማግሌዎች በሪያድ ከኢትዮጵያ ኤንባሲ ጋር በመተባበር ከአመት በፊት የጀመሩት ጥረት በአምባሳደር መሃመድ ሃሰን ድክመት መስተጓጎሉ የሚናገሩ ውስጥ አዋቂ ምንጮች በአሁኑ ሰዓት ጭካኔ የተሞላበት የኢትዮጵያውያኑ የእርስ በእርስ ግጨት ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ በመምጣቱ መንፉሃ በሚኖሩ ሰላማዊ ኢትዮጵያውያን ላይ ስጋት መደቀኑ ይነገራል። ቀደም ብሎ ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሃገራቸው ከተመለሱ በመቶሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከግማሽ በላይ በባህር አቋርጠው ወደ ሳውዲ አረቢያ መግባታቸውን የሚናገሩ ወገኖች መንፉሃ እንደወትሮው በኑሮ ውድነት ሃገራቸው ውስጥ መኖር ተስኗቸው መሄጃ ባጡ ኢትዮጵያውያን ዳግም መጨናነቋን ይናገራሉ።
እልባት ያላገኘው ይህ የኢትዮጵያኑ የብሄር ግጨት በሰላማዊ ወገኖቻችን ላይ የሚያደርሰውን ተጽእኖ ግምት ወስጥ በማስገባት በዚህ ዙሪያ በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰንን ሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ስልክ በመደውል ለማግኘት ያደረኩት ሙከራ ባይሳካም አባሳደር መሃመድ ሃሰን አፈጉባኤ አብዱላ ገመዳ ወደ ሳውዲ አረቢያ ለጉብኝት ከመግባታቸው በፊት ከስልጣናቸው ተነስተው ወደ ሃገር መመለሳቸውንና ኤንባሲው በግዜያዊነት በዲያስፖራው ሃላፊ አቶ ተመስገን ኡመር እይተመራ መሆኑን አንድ ስማቸውን መጥቀስ ፈቃደኛ ያልሆኑ የኤንባሲው  ሰራተኛ ከስጡኝ መረጃ ማረጋጋጥ ፡ተችሏል።
Ethiopian Hagere Jed Bewadi ይህ ሰሞኑንን ሪያድ መንፉሃ እና አካባቢውን ሲያብጥ የከረመው ዘግናኝ የብሄር ግጭጥ ተዕይንት ነው ። ማሳሰቢያ ለዝግጀት ክፍሉ  ከዚህ በላይ ተያያዥ የሆነው የፍቶ መረጃ ቀደም ካለ የተወሰደ ሲሆን በቴክኒክ ምክንያት ከዚህ ዜና ጋር አባሪ በማደረግ መላክ ባለማቻላችን ይቀራት እየጠየቀን በወቅቱ የተከስተውን የቪድዮ ምስል በፊስ ቡክ የውስጥ መስመራችሁ መላኩን እንገልጻለን

 Video

ተጨማሪ ያንብቡ:  Tonight what heights we'll hit, on with the show this is it

7 Comments

  1. ዸደብ ሃበሻ ሲጠግብ ……በሳውዲ ይገደላል…..ካልሆነ በሃበሻ. ይገደላል ካልሆነ ደግሞ እንደ አጼ ቴድሮስ እራሱን ይገድላል ይሄ ሁሉ ጥጋብ ነው….

  2. ግጭቱ የተከሰተው በየትኞቹ ብሄሮች መካከል እንደሆነ የዚህ ጽሁፍ እቅራቢ የገለጸው ነገር የለም..ትንሺ ቢብራራ?
    in between which tribes the conflict has been erupted? a bit brief please..!

  3. Not a complete report. Which ethnics are involved in the conflict? Who started it? You need to answer these two questions in your report.

  4. Conflict is between Tigre & Oromo. But it can also be between any tribe. Ethiopians in Saudi are crazy & idiot. Smoke shisha, girls do prostitution( mind you z prostitution here is different type than the one in Ethiopia), drug & alcohol sellers etc. Habesha becomes koshasha in Saudi.

  5. እናንተ ምን አለባቹ, ስደቡአችው:: What is new?We, humans tend to blame the weak and the helpless.

Comments are closed.

Share