በአንድ አካባቢ ኢትዮጵያዊያን ላይ  የሚካሄድ ጥቃት በሁሉም ኢትዮጵያዊ ላይ የሚካሄድ ጥቃት ነው!

ጥቅምት 25፣2007 (ኖቨምበር 4፣2014)

ህወሓት/ኢህአዴግ በተለያዩ ኢትዮጵያውያን ላይ ያነጣጠረ የግፍ ተግባር ማካሄድና የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲውን ተግባራዊ ማድረጉን በሰፊው ቀጥሏል::  በዚህ አኳያበሶማሌ፣ በአማራው፣ በኦሮሞ፣ በሲዳማ፣ በአፋር፣….ወዘተ ተወላጆች ላይ የሚያካሂደው እልቂት በቂ መረጃ ነው::

የዚህ ቀጣይ ረገጣ ተከታታይ ዒላማ የሆነው አንዱ የአማራው፡ተወላጅ ነው:: ህወሓት/ኢህአዴግ ከመነሻው የአማራ፡ተወላጁን  በጠላትነት ፈርጆ በተለያየ ደረጃየጥቃት ዒላማ አድርጎታል። በዚህም መሠረት በራሱ ትዕዛዝም ሆነ በተለጣፊ ድርጅቶቹ አማካኝነት እጅግ ዘግናኝ ግፍ የተሞላበት ወንጀል ፈጽሟል። ለዘመናት  ከኖረበት ቦታ “ወደ መጣህበት ሂድ” ተብሎ ንብረቱ ተነጥቆ ባዶ እጁን በግዳጅ እንዲባረር ተደርጓል። ይህ አልበቃ ብሎ ህፃናት ልጆች ሳይቀሩ አሰቃቂ በሆነ ግፍ እንዲታረዱ ዜጎች ወደ ገደል እንዲወረወሩና፣ ቤታቸው ውስጥ እንዳሉ እንዲቃጠሉ ተደርጓል። በአርባ ጉጉ፣ በወተር ፣በአርሲ .ወዘተ የተካሄደው ይህንኑ ነው የሚያሳየው።

ለዚህ ጨካኝና ህገወጥ ተግባርም የህወሓት/ኢህአዴግ ባለሥልጣኖች በቀጥታም በተዛዋሪም ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። በጊዜው ጠቅላይ ሚኒስተር የነበረው ታምራት ላይኔ በአማራው ተወላጅ ላይ የኦጋዴን ህዝብ እርምጃ እንዲወስድ ያካሄደው ግልጽ የሆነ መገፋፋት፣ በአርሲ በተካሄደ እልቂት እነ ኩማ ደመቅሳ ዋና ተዋናን እንደነበሩ፣ መለሰ ዜናዊ ከጉራፈርዳ የተባረሩትንና ለአቤቱታ የመጡን ዜጎች እንኳን አባረሯችሁ የሚል አንድምታ  የሚሰጥ መግለጫ በይፋ መስጠቱ ጥቂቶቹ ማስረጃዎች ናቸው።

ይህ ህወሓት/ኢህአዴግ ሆን ብሎ የሚፈጽመውና የሚያበረታታው ህዝብን እርስ በርስ የማጫረስ ተግባር እጅግ እየሰፋ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከር በአደገኛፍጥነትመም በመቀጠል ላይ ነው።

ትላንት ከትላንት በስቲያ በተለያዩ ቦታዎች እንደተደረገው ሁሉ፣ ባለፉት ጥቂት ሳምንታትም ባለማቋረጥ በጋምቤላ አካባቢ በተመሳሳይ ሁኔታ በዋናነት በዚሁ በአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ የድብደባ፣ የግድያና የማፈናቀል እርምጃ በሰፊው ተካሂዶ በመዠንገር አካባቢ ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሲሞቱ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ቆስለዋል፣ በሽዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ተፈናቅለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከሕወሓት ባለስልጣናት ጋር ባለው ትስስር የከበሩ ማዕድናትን ከዱባይ ወደ አዲስ አበባ ሲያዘዋውር የተያዘው ግለሰብ ተፈረደበት

ይህ ሁሉ ሲሆን፣ የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታ ያለበት መንግሥት መንበር ላይ የተቀመጠው ህወሓት/ኢህአዴግ ሁኔታው እንዳይከሰት ቀድሞ ለመከላከልም ሆነ በጊዜ ለማስቆም የወሰደው ምንም እርምጃ የለም። ችግሩ ከተፈጠረ በኋላም ቢሆን የተጎዱትን ለመንከባከብ፣ ህክምና የሚሹትን ለመርዳት፣ መልሶ ለማቋቋምና ወንጀለኞቹን ለህግ ለማቅረብ የሚያደርገው ይህ ነው የሚባል ሙከራ አይታይም።  ይሀ ሁሉ  የሚያመለክተው ያለው ስርዓት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የዚህ ወንጀል አካል እንደሆነ ነው።

ሸንጎው የኢትዮጵያን ህዝብ አንዱን ከአንዱ በማጋጨት ሥልጣኑን ለማራዘም ህወሓት/ኢህአዴግ የሚያካሂደውን ቀጣይ ሀላፊነት የጎደለው ኢ-ሰብአዊ ግፍ አጥብቆ ያወግዛል። በአማራውም ሆነ በሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ በተከታታይ እየተካሄደ ያለውን የማፈናቀል፣የግድያ፣ የጅምላ እሰራትና  ሌሎች  ወንጀሎች ባስቸኳይ እንዲቆም ያሳስባል። እስካሁን የተፈጸመው ግፍ ሁሉ ብቃት ባለው እና  ከሥርዓቱ ባለሟሎች ነፃ በሆነ አካል እንዲጣራ፤ ወንጀለኞቹም ለፍርድ እንዲቀርቡ ያስገነዝባል።

በኦጋዴን፣ በኦሮሚያ፣ በሲዳማ፣ በአፋር፣ በወልቃይት እንዲሁም በሌሎች የሀገራችን ቦታዎች ውስጥ ይህ  ሥርዓት የሚያካሂደውን ማለቂያ የሌለው ግፍ ሸንጎ አጥብቆ ያወግዛል።

ሰዎችን በትውልዳቸው የተነሳ በጅምላ የጥቃት ሰላባ ማድረግ በዓለምአቀፍ ህግም አስጠያቂ እንደሆነ የዚህ ጥፋት ፈጻሚም አስፈጻሚም የሆኑ ሁሉ እንዲገነዘቡት በድጋሚ ለማሳሰብ እንወዳለን።

የዚህን  የግፍ ሥርዓት መጨረሻ ለማፋጠን ሁሉም ኢትዮጵያዊ አንድነቱን አጠናክሮ እንዲነሳ እናሳስባለን፡  በአንድ አካባቢ ኢትዮጳያዊያን ላይ  የሚካሄድ ጥቃት በሁሉም ኢትዮጵያዊ ላይ የሚካሄድ ጥቃት ነው!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

 

5 Comments

  1. ምን ያደጋል እነሱ ይገድላሉ ያስራሉ ያፈናቅላሉ እኛ ግን ወሬ ብቻ ሆነን ቀረን ለማነው እናውግዛለን እንቃወማለን ብሎ ማለት ወያኔ እንደሆነ ወሬ ብቻ እንደሆንን አውቆ የፈለገውን እይሰራ ነው እኛ ግን መልሰን የተሰራውን ግፍ እናወራለን ቂልን አንዴ ብቻ ስደበው ከዚያ በኋላ እራሱን እይደጋገመ ሲሰድብ ትሰማዋለህ ነው የሚባለው. ስለዚህ ወያኔ ያደረገውን ምልሶ በማውራት ምንም ጥቅም አይገኝም

  2. ለመሆኑ “የዚህን የግፍ ሥርዓት መጨረሻ ለማፋጠን” ሸንጎው ምን እየሰራ ነው ? መግለጫዎችን ከማውጣት የዘለለ ማለቴ ነው!!

  3. አይ ሼንጎ ለምን በኢትዮጵያ ህዝብ ስም ለአማራው ያላዝናል አንደኛውኑ ልክ እንደ ተክሌ የሻው የአማራ ድርጅት ብሎ ቢከፍት አይሻለውም? አምኒስቲ ባለፉት 3 አመታት 5000 ኦሮሞ እስር ቤት ታስረዋል ይላል ሸንጎ የዛሬ 22 አመት የተደረገውን ያራግባል:: ግን መቸ ይሆን ሁሉንም ኢትዮጵያዊ በአንድ አይን ማየት የምትጀምሩት?
    የጋምቤላውን የኦጋዴኑን የሌላውን ብሄር ስም ስታነሱ ለአጃቢነት እንደሆነ ያሳብቅባችሃል? እንጂ አሁን ማድረግ የሚገባችሁ አንገብጋቢው ትኩሱ ዜና የአምኒስቲው ነበር መግለጫ ማውጣት ቢኖርባችሁ የአምኒስቲውን በመደገፍ የወያኔን ግፍ ታጋልጡ ነበር:: እንደ አለመታደል ሆኖ ወደ ጎጣችሁ ገብታችሁ የዛሬ 22 አመቱን ታራግባላችሁ ለምን አንድ ቀን ጎንደር ላይ ሀውልት አትገነቡላቸውም መቸም የእናንተ ሲሆን ቂም አይደለም ታሪክ አይደል የምትሉት?
    ትላንት የኢሳትን እፍታ እያየው ነበር ቅቅቅቅቅቅቅ አላነሱም እንዳይባሉ መጨረሻ ላይ አንስቶ አንዱ የዋህ ተንታኛቸው አምኒስቲ በጣም ተሳስተዋል ለምን የኢትዮጵያ እስረኞች አላለም በጎንደር በጎጃም በትግራይ በጋምቤላ በኦጋዴን በሁሉም እስር ቤት ሁሉም ኢትዮጵያዊ እየታሰረ ነው የሚል እንድምታ ያለው ትንታኔ ሲሰጥ ያየ ሰው ኦኬ ለዚህ ነው በመጨረሻም ተብሎ የገባው ያስብላል
    በእርግጥ ያ መብታችሁ ነው ግን በአንድነት ስም አታወናብዱ እንጂ ዛሬ በኢትዮጵያ አንድነት ስም የሚጮሁ ሚዲያም የፖለቲካ ድርጅት ከልቡ እንዳልሆነ በቀላሉ መታዘብ ይቻላል ቢያንስ ለዚህ የሰብአዊ መብት ረገጣ መግለጫዎችን አውጥቶ ቢያንስ ይህ ዘገባ ልክ ነው ወይም አይደለም ብሎ የሆድን በሆድ ይዞ ሰልፍ መጥራትና ማስተጋባት ሁለት ጥቅም ያለው ይመስለኛል
    1. እግረመንገድን የወያኔን ግፍና ስቆቃ ለማጋለጥ ይረዳል:: ቢያንስ የጠላቴ ጠላት ወዳጄ በሚል የፖለቲከኞች የትግል ስልት
    2. ይህ ልቡ የሸፈተውን የኦሮሞን ህዝብ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር ለአንድ አላማ ማሳለፍ ቢቻል እንጂ አይጎዳም ነበር::
    ግን ዘረኝነት ልባችሁን አሳውሮት ለነገይቷ ኢትዮጵያ የማሰቢያ አንጎላችሁ እንኳን እናይሰራ ልቦናችሁን አጨለማችሁ
    ተጋግዘን ይህችን ሀገር ከምናፈርሳትና በሃላ ከሃላፊነት ከመሸሽ ብናስብበት ሳይሻል አይቀርም
    ቸር ሰንብቱ
    እግዚአብሔር ልቦና ይስጣችሁ

    • What ilma said is defintly correct.Unless we are not united this government will never be overthrown.

Comments are closed.

Share