ከሕወሓት ባለስልጣናት ጋር ባለው ትስስር የከበሩ ማዕድናትን ከዱባይ ወደ አዲስ አበባ ሲያዘዋውር የተያዘው ግለሰብ ተፈረደበት

ከሕወሓት ባለስልጣናት ጋር በፈጠረው ትስስር በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ቦታው ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግቢ ውስጥ የከበሩ ማዕድናትን ያለፈቃድ ሲያዘዋውር ተይዞ ታስሮ የነበረው ግለሰብ በተመሰረተበት ክስ በእስራትና በገንዘብ ተቀጣ፡፡

https://www.youtube.com/watch?v=xfHo-pr6jRQ

ተከሳሽ ክብሮም ተስፋዬ በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 ዓ.ም አንቀጽ 168(1) እንዲሁም የከበሩ ማዕድናትን መቆጣጠር የወጣ አዋጅ ቁጥር 651/2001 አንቀጽ 2/7/ሀ የተመለከተውን በመተላለፍ ክስ የተመሰረተበት ሲሆን የክስ መዝገቡ እንደሚያስረዳዉ ተከሳሽ የከበሩ ማዓድናት ዉጤቶችን ለመነገድ ለመሸጥና ለመያዝ የሚያስችል ህጋዊ ፍቃድ ሳይኖረዉ ሕግን ባልተከተለ መልኩ ከዱባይ ወደ አዲስ አበባ ለማስገባት ሲሞክር ሊያዝ ችሏል፡፡

በወቅቱ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የመንገደኛ ማስተናገጃ ተርሚናል በተደረገ አካላዊ ፍተሻ አቶ ክብሮም የቀረጥ ታክስ መጠኑ ብር 208,222.66 የሆነና 10,967 ግራም የሚመዝን የብር ጌጣ-ጌጥ በለበሰው ጃኬት፣ ሸሚዝና ሱሪ ኪሶች እንዲሁም በሰደሪያ መልክ በተስፉው ኪሶቹ ደብቆ ወደ ሀገር ውስጥ ሊያስገባ ሲሞክር በቁጥጥር ሥር የዋለ በመሆኑ በፈጸመው የኮንትሮባንድ ንግድ ወንጀል ክስ ቀርቦበታል፡፡

ዐቃቤ ህግም የሰውና የተለያዩ ማስረጃዎችን አጠናቅሮ ያቀረበ ሲሆን የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ ወንጀል ችሎትም መዝገቡን መርምሮ በ4 ዓመት ጽኑ እስራትና 4000 ሺህ ብር እንዲቀጣ ወስኗል፡፡

ዱባይ የሕወሓት ባለስልጣናት የኮንትሮባንድ ንግድ ዋና ተርሚናል መሆኗ ይታወቃል:: ከሕወሓት ባለስልጣናት ጋር ትሥስር የነበራቸው ግልሰቦችም በአዲስ አበባ ኤርፖርት እንደማይፈተሹ በተደጋጋሚ ከዚህ ቀደም ሲዘገብ ቆይቷል::

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሩሲያ ጦር በግማሽ ቀን ብቻ ወደዩክሬን ዋና ከተማ መድረሱ ተሰምቷል | በዚህ ጦርነት እነማን ከየትኛው ሀገር ጎን ተሰለፉ?
Share